የዘላለም ሕይወትአዲስ
የዘላለም ሕይወት ምንድነው?
የዘላለም ሕይወት የጊዜ ወሰን በሌለው ሁኔታ ውስጥ ለዘላለም መኖር ብቻ አይደለም፤ ያልዳኑ ሰዎችም ቢሆኑ “በእሳት ባሕር” ውስጥ በሥቃይ የሚኖሩት “ለዘላለም” መሆኑ ተነግሯል፤ “ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ” ይባላሉ (ማቴ.25፡41)። “በዘላለም ጥፋት ይቀጣሉ” (2ተሰ.1፡10፤ ማቴ.25፡46)፣ እንዲሁም “ለዘላለምም እስከ ዘላለም ቀንና ሌሊት ይሣቀያሉ” (ራእ.20፡10) ተብሎ ተጽፏል፡፡ “የዘላለም ሕይወት” ሲባል ግን በዘመን ሳይገደቡ ለዘላለም መኖር ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔርን በማወቅ ከእርሱ ጋር ለዘላለም በኅብረት መኖር ነው፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ >>>አራቱ ወንጌላት
መግቢያ
ወንጌል የሚለው ቃል በቅድሚያ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰበከውን መልካም የምሥራች ያመለክታል(ኢሳ.61፡1፤ ሉቃ.4፡19፤ ማቴ.4፡23፤ 9፡35) በመቀጠልም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚሰበከውን መልካም የምሥራች ያመለክታል (ሮሜ.1፡1-4፤ ሉቃ.2፡10፤ የሐዋ.ሥ.8፡35) ክርስቶስን በተመለከተ የሚሰበከው ወንጌል ከይዘቱ አንጻር በ5 ዓይነት መልኩ ተገልጿል፤ ይኸውም፡-
ተጨማሪ ያንብቡ >>>መጽሐፍ ቅዱስ ምንድነው?
መጽሐፍ ቅዱስ የብዙ ቅዱሳት መጻሕፍት ስብስብ ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙት መጻሕፍት በሮሜ1፡1 እና በ2ጢሞ.3፡15 ላይ «ቅዱሳን መጻሕፍት» ተብለው ተጠርተዋል፤ እንዲሁም በብዙ ስፍራ «መጻሕፍት» (ማቴ.22፡29፤ ሉቃ.24፣27ና45፤ ዮሐ.5፡39ና 47፤7፡15፤ የሐ.ሥ.17፡2ና11፤18፡28፤ ሮሜ.5፡4) ተብለው መጠራታቸውን እናስተውላለን፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ >>>1. የመንፈስ ቅዱስን ስጦታ መቀበል (ሐ.ሥ.2፡38)
የተሰበከለትን ወንጌል ተቀብሎ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ከልቡ ያመነ ማንኛውም ሰው ይህን እውነተኛ እምነቱን ተከትሎ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ይቀበላል፡፡ ‹‹የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ›› የሚለው ይህ ቃል ከዚህ ከሐ.ሥ.2፡38 ሌላ በሐ.ሥ.10፡45 ላይ የሚገኝ ሲሆን ቃሉ የሚያመለክተው የጸጋ ስጦታዎችን ሳይሆን መንፈስ ቅዱስ ራሱ ለአማኙ የተሰጠ ስጦታ መሆኑን ነው፡፡ ምክንያቱም ቃሉ
ተጨማሪ ያንብቡ >>>የእግዚአብሔር ቃል እውቀት
የምንኖርባት ምድር ታሪክ ተገባዶ ሁሉም የሰው ልጅ ዘር በማይቀረው የነጩ ዙፋን ፍርድ ፊት በቆመ ጊዜ በታላቁ የሕይወት መጽሐፍ ስማቸው ከማይገኘውና ወደ እሳት ባህር ውስጥ ከሚጣሉት ብዙዎች ሰዎች ውስጥ ምናልባትም አብዛኛዎቹ የእግዚአብሔር ቃል እውቀት ያልነበራቸው ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ >>>ከጠማማ ትውልድ መዳን
“በብዙ ሌላ ቃልም መሰከረና። ከዚህ ጠማማ ትውልድ ዳኑ ብሎ መከራቸው። ቃሉንም የተቀበሉ ተጠመቁ፥ በዚያም ቀን ሦስት ሺህ የሚያህል ነፍስ ተጨመሩ” (የሐ.ሥ.2፡38-40)
ተጨማሪ ያንብቡ >>>መትጋት
“ቃሉንም የተቀበሉ ተጠመቁ፥ በዚያም ቀን ሦስት ሺህ የሚያህል ነፍስ ተጨመሩ፤ በሐዋርያትም ትምህርትና በኅብረት እንጀራውንም በመቍረስ በየጸሎቱም ይተጉ ነበር።" (ሐ.ሥ. 2:41-42)
ተጨማሪ ያንብቡ >>>አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስን በክርስቶስ ማወቅ
ክፍል 1 - የኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት>
ኢየሱስ የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ ከሴት ከመወለዱ/ገላ4፡4) በፊትም እንደነበረ የሚከተሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች በግልጽ ይናገራሉ፡፡ዮሐ.1፡15፣27 “ዮሐንስ ስለእርሱ መሰከረ፤ እንዲህም ብሎ ጮኸ፤ ከእኔ በኋላ የሚመጣው እርሱ ከእኔ በፊት ነበረና ከእኔ ይልቅ የከበረ ሆኗል ስለእርሱ ያልሁት ይህ ነበረ፡፡”ዮሐ.8፡58 “ኢየሱስም እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ አብርሃም ሳይወለድ እኔ አለሁ አላቸው”
ተጨማሪ ያንብቡ >>>አምስቱ ስጦታዎች
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ የዋጃት ቤተክርስቲያን የእርሱ አካል መሆንዋን ማሰብ ነፍስን በመለኮታዊ ሐሴት እና ውስጥን በሚያረሰርስ እርካታ ይሞላል፡፡ አማኝ በዚያች የክርስቶስ አካል ውስጥ ብልት መሆኑን ሲያሰላሰል የሚያገኘው ደስታ እጅግ ከፍ ያለ ከመሆኑም በላይ ማንም ከዚያ የብልትነት ስፍራ ሊያወጣው የማይችል ስለመሆኑ ማሰብም በጣም ያስደንቀዋል፡፡ ራስ ከሆነው ከክርስቶስ ዘንድም የሚያገኘውን መንፈሳዊ መግቦት በደስታ ይቀበላል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ >>>የክርስቲያኖች ማንነት
አማኞች ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲመስሉ የእግዚአብሔር ውሳኔ ነው፡፡ ጳውሎስ ስለዚህ ጉዳይ ሲጽፍ «ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ወስኗልና» ብሏል/ሮሜ.8፡29/፡፡ በመሆኑም አማኞች ስለማንነታቸው ለሚጠይቋቸው ሰዎች ኢየሱስ ስለማንነቱ በተጠየቀ ጊዜ የሰጠውን ዓይነት መልስ ሊመልሱ ይገባቸዋል፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ >>>