Aclesia  


የእግዚአብሔር ቃል እውቀት

የምንኖርባት ምድር ታሪክ ተገባዶ ሁሉም የሰው ልጅ ዘር በማይቀረው የነጩ ዙፋን ፍርድ ፊት በቆመ ጊዜ በታላቁ የሕይወት መጽሐፍ ስማቸው ከማይገኘውና ወደ እሳት ባህር ውስጥ ከሚጣሉት ብዙዎች ሰዎች ውስጥ ምናልባትም አብዛኛዎቹ የእግዚአብሔር ቃል እውቀት ያልነበራቸው ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ዛሬ በዓለማችን በሃይማኖት ሽፋን ሕሊናን በመሸንገል ለሚመጣው መራራ ቅጣት ራስን የማዘጋጀት ዝንባሌ የሚታየው በእውቀትና በመረዳት ሳይሆን ከእግዚአብሔር ቃል ውጭ በሆነ ከንቱ ሐሳብ በመመራት እንደሆነ ይታያል፡፡ አንዳንድ ጊዜም የተሳሳተ የሃይማኖት ትምህርትን በእግዚአብሔር ቃል ለመደገፍ የሚደረገው ጥረትም ቃሉን ካለመረዳት የመነጨ መሆኑን እናስተውላለን፡፡

ብዙ ዓመታት ያስቆጠረ ውሸት እውነት ሊመስል ቢችል እንኳ ውሸትነቱ መገለጡ አይቀሬ ነው፤ ለዚህም ደግሞ እውነት የሚመስለውን ነገር ሁሉ መርምሮ ለማረጋገጥ ብቸኛው መሣሪያ ጊዜ የማይለውጠው ሕያው የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው፤ እርሱ ለእኛ እንደ ወንፊት ነው፤ እንክርዳድ የሞላበትን የፈጠራ ትምህርት እንለይበታለን፤ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ቃል የያዘ ብቸኛና ታላቅ መጽሐፍ ነው፤ ይኸም መጽሐፍ የአባቶቻቸውን የቆየና የተሳሳተ መንገድ እንደ ጽድቅ ቆጥረው በመመካት ይጓዙ ለነበሩት የእስራኤል አዲስ ትውልድ ሲናገር «በአባቶቻችሁ ሥርዓት አትሂዱ፣ ወጋቸውንም አትጠብቁ፣ በጣዖቶቻቸውም አትርከሱ» በማለት ያስጠነቅቃል /ሕዝ.20፡18/፡፡

ጌታችን ኢየሱስ የእግዚአብሔርን ቃል ዕውቀት ወደ ጐን በመተው የሰውን ሥርዓት በመጠበቅ ለእርሱ የሚቀኑ የሚመስላቸውን ሰዎች ደጋግሞ ገሥጿል፤ ባሕልና ወግን የሚሰብኩትን የሕግ መምህራንንም «የሰውም ሥርዓት የሆነ ትምህርት እያስተማሩ በከንቱ ያመልኩኛል»/ማቴ.15፡9፣ ማር.7፡1-3/ በማለት ተናግሯል፡፡ ይህም ንግግሩ እግዚአብሔርን እንደሚገባ ሳያውቁ የሚቀርብ አምልኮ ከንቱ መሆኑን ያስረዳል፡፡

እርግጥ ነው ለሰዎች ዓይን «መልካም የምትመስል መንገድ አለች፤ ፍጻሜዋ ግን ሞት ነው» እንደተባለው ከጥንት የኖረም ቢሆን እንደ እግዚአብሔር ቃል ያልሆነ መንገድ ሁሉ ፍጻሜው «ሞት» ብቻ ነው /ምሳ.16፡25/፡፡ ነገር ግን ሰው በጌታ በኢየሱስ ብቸኛ አዳኝነት ካመነ ከቀድሞ አባቶቹ ከወረሰው ከንቱ ኑሮ ይድናል፤ ጴጥሮስ ስለዚህ ነገር ሲጽፍ «ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን ነውርና እድፍ እንደሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደተዋጃችሁ ታውቃላችሁ» /1ጴጥ.1፡19/ ብሏል፡፡

የእግዚአብሔር ቃል እውቀት ጥቅሞች

የእግዚአብሔር ቃል በሰው አንደበት ተነግረው የማያልቁ ብዙ ጥቅሞች እንዳሉት ቃሉን የሚጠቀሙበት ሁሉ ያውቁታል፡፡

የእግዚአብሔር ቃል አስተዋይ ለመሆን /መዝ.118፡98፣104/፣ ጌታን ላለመበደል /መዝ.118፡11/፣ በሥራችን መከናወንን ለማግኘት /ኢያ.1፡7-9/፣ የልብ ደስታን ለማግኘት /ኤር.15፡16/፣ ለበጎ ሥራ ለመዘጋጀት /2ጢሞ.3፡15/፣ ለትምህርታችን /ሮሜ.15፡3-4/፣ የክፋት መንፈሳዊ ሠራዊትን ለመዋጋት /ኤፌ.6፡10/፣ ይጠቅማል፡፡ እንደዚሁም የእግዚአብሔር ቃል እውቀት በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ቀጥሎ በዝርዝር የምንመለከታቸው ሌሎች ጥቅሞችም አሉት፡፡

    1. ላለመሳሳት ይጠቅማል

ሁላችንም የሔዋን መሳሳት እንዴት እንደነበረ እናውቃለን፤ የሔዋንም የመጀመርያ ጥፋቷ ፍሬ ቆርጣ መብላቷ አልነበረም፤ ቀዳሚው ጥፋቷ ከፈጣሪ ቃል ይልቅ የፍጥረትን ድምፅ ማዳመጧ ነበር፡፡ ይህም ድምፅ ፍጹም ወዳጅና ተቆርቋሪ ከሚመስል ጠላት የመጣ ነበር፡፡ ማስጠንቀቂያ ከታከለበት የጌታ ቃል ይልቅ ማባበያ የተሞላው የፍጥረት ድምፅ አሳታት፡፡ ዛሬም ጠላት በምንም ዓይነት ጽድቅን ፊት ለፊት ተቃውሞ አይሰብክም፡፡ ግማሽ እውነት ግማሽ ውሸት በዘመኑ የሚሠራበት የሰይጣን ብልሃት መሆኑ ከታወቀ ውሎ አድሮአል፤ አንድ የቲያትር ተዋናይ/አርቲስት/ ገጸ ባሕርይውን መስሎ ለመታየት ብዙ ነገሮችን ሊያደርግ ይችላል፤ ለምሣሌ ሰው ሰራሽ ፂም ሊያደርግ ረዥም ቀሚስ ሊለብስ ይችላል፤ አስመስሎም ይናገራል፤ ነገር ግን ያንን የወከለውን ነገር መሆን አይችልም፤ ከለበሳቸው አልባሳት ውስጥ ያለው ራሱ ነውና፡፡ በመሆኑም እንዲህ ካለው የሰይጣን ማታለል ለመዳን የሚቻልበት ብቸኛው መሣሪያ የእግዚአብሔር ቃል እውቀት ነው፡፡ ሰዎችም ቢሆኑ በተመሣሣይ መንገድ የክርስትናን መልክ ተላብሰው ሊያታልሉ ሲሞክሩ አሁንም መፍትሔው ያው የእግዚአብሔር ቃል እውቀት ነው፡፡

ሁላችንም የሔዋን መሳሳት እንዴት እንደነበረ እናውቃለን፤ የሔዋንም የመጀመርያ ጥፋቷ ፍሬ ቆርጣ መብላቷ አልነበረም፤ ቀዳሚው ጥፋቷ ከፈጣሪ ቃል ይልቅ የፍጥረትን ድምፅ ማዳመጧ ነበር፡፡ ይህም ድምፅ ፍጹም ወዳጅና ተቆርቋሪ ከሚመስል ጠላት የመጣ ነበር፡፡ ማስጠንቀቂያ ከታከለበት የጌታ ቃል ይልቅ ማባበያ የተሞላው የፍጥረት ድምፅ አሳታት፡፡ ዛሬም ጠላት በምንም ዓይነት ጽድቅን ፊት ለፊት ተቃውሞ አይሰብክም፡፡ ግማሽ እውነት ግማሽ ውሸት በዘመኑ የሚሠራበት የሰይጣን ብልሃት መሆኑ ከታወቀ ውሎ አድሮአል፤ አንድ የቲያትር ተዋናይ/አርቲስት/ ገጸ ባሕርይውን መስሎ ለመታየት ብዙ ነገሮችን ሊያደርግ ይችላል፤ ለምሣሌ ሰው ሰራሽ ፂም ሊያደርግ ረዥም ቀሚስ ሊለብስ ይችላል፤ አስመስሎም ይናገራል፤ ነገር ግን ያንን የወከለውን ነገር መሆን አይችልም፤ ከለበሳቸው አልባሳት ውስጥ ያለው ራሱ ነውና፡፡ በመሆኑም እንዲህ ካለው የሰይጣን ማታለል ለመዳን የሚቻልበት ብቸኛው መሣሪያ የእግዚአብሔር ቃል እውቀት ነው፡፡ ሰዎችም ቢሆኑ በተመሣሣይ መንገድ የክርስትናን መልክ ተላብሰው ሊያታልሉ ሲሞክሩ አሁንም መፍትሔው ያው የእግዚአብሔር ቃል እውቀት ነው፡፡

የእግዚአብሔር ቃል እውቀት የሌላቸው ሰዎች ትክክለኛው መንገድ /ሃይማኖት/ የቱ እንደሆነ መጠየቃቸው የተለመደ ነው፤ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥም የየትኛውም የሃይማኖት ድርጅት ስም ባለመጻፉ የትኛው ሃይማኖት ትክክል እንደሆነ ለማወቅ በመፈለግ ግራ ይጋባሉ፡፡ ነገር ግን ይህ ጥያቄም ሆነ ግራ መጋባት ሊመጣ የሚችለው የእግዚአብሔርን ቃል በጥልቀት ካለመረዳት ነው፤ ምክንያቱም እንደ እግዚአብሔር ቃል ስናስብ እግዚአብሔር ሰዎችን ሁሉ የሚጠራው ልጁን አምኖ ወደመከተል እንጂ ወደ የትኛውም የሃይማኖት ጎራ አይደለምና፡፡

መጽሐፍ ቅዱስን ወደ ጎን ትቶ ሰዎች የጻፉአቸውን የፈጠራ ድርሰቶች፣ የትውልድ ታሪኮች የሚከተል /1ጢሞ.4፡7/ ሰው የእግዚአብሔር ቃል እውቀት ሊኖረው አይችልም፤ ከዚህም የተነሣ በዕለታዊ ኑሮውም ሆነ በእምነት ነገር ይስታል፡፡ እንዲህ ያለው ሰው ከሳተበት ነገር ለመዳን ከሃይማኖት ቡድናዊ ስሜት ተላቆ መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ በማንበብና በመረዳት የእግዚአብሔርን ቃል ሊያውቅ ይገባል፡፡

ሰው ላለመሳሳት ከፈለገ ዛሬም ያለው አማራጭ የእግዚአብሔርን ቃል ማወቅና የተጻፈውን ሁሉ አንድም ሳይቀር አምኖ መቀበል ብቻ ነው፤ ይህ ካልሆነ ግን «መጽሐፍ ቅዱስ አለኝ፤ ከቤቴም አኑሬዋለሁ» ማለቱ ብቻውን ከስህተት አያድንም፤ ክብር ይግባውና ጌታ ኢየሱስም መጻሕፍቱ እያሏቸው በእምነት ነገር የሳቱ ፈሪሳውያንን «መጻሕፍትንና የእግዚአብሔርን ኃይል አታውቁምና ትስታላችሁ» ብሎአቸው ነበር፤ /ማቴ.22፡29፣ ማር.12፡24/፡፡

በዕለታዊ ኑሮም ቢሆን ከስህተት የምንጠበቀው የእግዚአብሔር ቃል እውቀት ሲኖረን ነው፤ መዝሙረኛው ዳዊት ስለዚህ ሲናገር «ጐልማሳ መንገዱን በምን ያነፃል? ቃልህን በመጠበቅ ነው» /መዝ.118፡9/፣ «አንተን እንዳልበድል ቃልህን በልቤ ሰወርኩ /ቊ.11/፣ «ሕግህ ለእግሬ መብራት ለመንገዴ ብርሃን ነው» /ቊ.105/ «ከቃልህ የተነሣ አስተዋልሁ፣ ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ጠላሁ»/ቊ.104/ ብሏል፡፡

    2. ላለመጥፋት ይጠቅማል

በጥንት ዘመን እንደነበረ በመጽሐፍ የተመዘገበለት ነገር ግን በአሁን ጊዜ የሌለ የቀደመው ዓለም የጠፋው የእግዚአብሔር ቃል እውቀት ስላልነበረው ነው፤ ከጥፋት ውኃ በፊት የነበረው ያ ዓለም ከሌሎች ሰባት ጋር ጽድቅን የሚሰብከውን ኖኅን ሊሰማው አልቻለም ነበር /2ጴጥ.2፡5/፤ «በዚህም ምክንያት ያን ጊዜ የነበረው ዓለም በውኃ ሰጥሞ ጠፋ» /2ጴጥ.3፡6/፤ ምክንያቱም አላዋቂነትን ወደው ነበርና /ምሳ.1፡22/፡፡ ግለሰብም ሆነ ሕዝብ እንዲሁም አገር የሚጠፉበት ዋነኛው ምክንያት የእግዚአብሔርን ቃል ካለማወቅ የተነሣ በሚፈጸሙ መንፈሳዊና ሥጋዊ በደሎች ነው፡፡ ሰው የጌታን ቃል ካላወቀ መጥፋቱ አይቀሬ ነው፡፡ በዚህ መልኩ ከበደሉ የተነሣ በእግዚአብሔር ፍርድ የሚጠፋ ሁሉ አስቀድሞውኑ የእግዚአብሔር ቃል እውቀት ማጣቱ ከእግዚአብሔር ፊት ያጠፋው/ያራቀው/ መሆኑ ግልጥ ነው፤ ከዚህም አንጻር ስለጠፉት ቤተ እስራኤል «ሕዝቤ ዕውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአልና» ተብሎ ተነግሯል /ሆሴ.4፡6/፡፡ እዚህ ላይ ሕዝበ እስራኤልን የሚያስተምር ሰው አልነበረምን? ብሎ መጠየቁ መልካም ነው፤ እስራኤል የሚያስተምሯቸው መምህራን፣ መሥዋዕት የሚያቀርቡላቸው ካህናት፣ ትንቢት የሚናገሩላቸው ነቢያት እንደዚሁም የሚያነቧቸው ቅዱሳት መጻሕፍት ነበሯቸው፡፡ ችግሩ ግን ነቢያት የሚናገሩትንና መጻሕፍት የሚመሰክሩትን የእግዚአብሔርን ቃል አውቀው አለመታዘዛቸው ነው፡፡ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም ስለ አንድ ባለጠጋ ሰውና ስለደሃው አልዓዛር የተናገረው ታሪክ ሰው በእጁ ያሉትን መጻሕፍት በመጠቀም ከፍርድ የሚድንበትን የእግዚአብሔር ቃል እውቀት መያዝ እንደሚኖርበት ያስረዳል /ሉቃ.16፡27-31/፡፡ እንግዲህ ላለመጥፋት ከተፈለገ መፍትሔው የእግዚአብሔርን ቃል አውቆ መገኘት ብቻ ነው፡፡

    3. ለሚጠይቁን ለመመለስ ይጠቅማል

ብዙውን ጊዜ የእግዚአብሔር ቃል እውቀት በሚገባ ሳይኖር ሲቀር በእምነት ነገር አላዋቂ ከሆኑ ወይም ከማያምኑ ሰዎች ለሚቀርቡ ጥያቄዎች አጥጋቢ መልስ መስጠት አይቻልም፡፡ ማንኛውም አማኝ ስለሚያምነው ነገር በተጠየቀ ጊዜ መልስ መስጠት ይችል ዘንድ የእግዚአብሔር ቃል ዕውቀት በሙላት ሊኖረው ይገባል፤ ስለዚህም መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር «የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ» ይላል /ቈላ.3፡16/፤ እንደዚሁም በሌላ ስፍራ «በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያት ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት የተዘጋጃችሁ ሁኑ» ይላል /1ጴጥ.3፡15/፤ ዳግመኛም «ለሚጠይቅህም እውነትን ቃል መመለስ ይቻልህ ዘንድ በምክርና በዕውቀት የከበረን ነገር አልፃፍሁልህምን?» የሚል እናነባለን /ምሳ.22፡21/፡፡

የቃሉ እውቀት አስተማሪ

ብዙዎች እንደሚያስቡትና እንደሚናገሩት መጽሐፍ ቅዱስ የተደበቀና የተሸሸገ ምሥጢር አይደለም፤ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ «የአፌ ቃላት ሁሉ ጽድቅ ናቸው፤ ጠማማ ዘወርዋራም አይደሉም፤ እነርሱ በሚያስተውሉ ዘንድ የቀኑ ናቸው፤ ዕውቀትንም ካገኙአት ሰዎች ጋር የተስማሙ ናቸው» ተብሎ ተነግሮአል /ምሳ.8፡8/፤ ስለዚህ እያንዳንዱ ሰው እግዚአብሔርን በሚፈልግ እውነተኛ ልብ ሆኖ ቢያነበው የቃሉን እውቀት በመንፈስ ቅዱስ አስተማሪነት ይማራል /ዮሐ.14፡26/፤ ይህ አስተማሪም ሁሌ ከተማሪው አይለይም፤ በየትኛውም ሰዓትና ጊዜ እንዲሁም ቦታ ይህ አስተማሪ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያነቡትን ሁሉ ሲረዳ ይኖራል፤ እርሱ የሚመጣና የሚሄድ አይደለም፤ ስለእርሱም «አስተማሪህ ከአንተ ከእንግዲህ አይሰወርም ... ጆሮችህ በኋላህ መንገድህ ይህች ናት በእርስዋም ሂድ የሚለውን ቃል ይሰማሉ» ተብሏል /ኢሳ.30፡21/፡፡ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም ለጃንደረባው እንዳደረገው መንፈስ ቅዱስ ለአንባቢው መጻሕፍትን በማብራራት የሚመራውን ሰው ይልክለታል /ሐዋ.ሥራ8፡29-35/፡፡

ምንም እንኳ መታዘዝ ስለማንችል አእምሮአችን እንዳይወቅሰን መጽሐፍ ቅዱስን ባናነብ ይሻለናል የሚሉ ሰዎች ቢኖሩም ያለእግዚአብሔር እውቀት መኖራቸው ከተጠያቂነት ስለማያድናቸው መልካም አይሆንላቸውም፤ ምክንያቱም «ነፍስ ዕውቀት የሌላት ትሆን ዘንድ መልካም አይደለም» ተብሎአልና /ምሳ.19፡2/፡፡

ይ ቀ ጥ ላ ል........


Amharic Bible-|- The Holy Bible [King James Version]