የእውነትን ቃል በአግባቡ መለየት
የእውነትን ቃል በአግባቡ መለየት

መግቢያ

መጽሐፍ ቅዱስን የሚያነቡና የሚማሩ ወገኖች ሁሉ፣ ለማወቅ የሚናፍቁትን የእውነትን ቃል ሊያገኙ በሚችሉበት ሁኔታ ውስጥ ናቸው ለማለት ይቻላል፤ ምክንያቱም ትክክለኛው እውነት የሚገኘው የእግዚእብሔር የቃል መዝገብ በሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብቻ ነውና፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጨረሻው ጸሎቱ ውስጥ ሲናገር፣ «... በእውነትህ ቀድሳቸው፣ ቃልህ እውነት ነው፣» ብሏል /ዮሐ.17፡17/፡፡ ስለሆነም አማኞች ለእግዚአብሔር የተቀደሱ ወይም የተለዩ የሚሆኑት በቃሉ በኩል ነው፡፡

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚሰሙት ሁሉ የእውነትን ቃል ያቀርብ የነበረው ቅዱሳት መጻሕፍትን በማስረጃነት እየጠቀሰ ነበር /ዮሐ.5፡39-47፤ ሉቃ.24፡27 እና 32፤/፡፡ «አይሁድም ይህ ሰው ሳይማር መጻሕፍትን እንዴት ያውቃል? ብለው ይደነቁ ነበር» /ዮሐ.7፡14/፡፡ የቃሉ መልእክተኞች የሆኑት ሐዋርያትም የእውነትን ቃል ሲናገሩ ቅዱሳት መጻሕፍትን መሠረት ማድረግ ስለላባቸው፣ «መጻሕፍትን ያስተውሉ ዘንድ አእምሮአቸውን ከፈተላችው»/ሉቃ.24፡45/፡፡ ጌታችን ካረገ በኋላም ወንጌልን ለእስራኤልና ለአሕዛብ በሰበኩበት ወቅት እንዲሁም መሠረታዊ የክርስትና ትምህርቶችን በሚያስተምሩበት ጊዜ እና አማኞች በስህተት ትምህርቶች እንዳይታልሉ ሲያስተምሩም ሆነ ሲጽፉ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን እየጠቀሱ ያስረዱ ነበር /ሐዋ.1፡20፤ 2፡16፣25፣35፤ 13፡33፣40፣47፤ 15፡15፤ 17፡2፤ 28፡23-28/፡፡ በተለይም በመልእክታት ውስጥ ለተጻፉት የክርስትና እውነቶች ቅዱሳት መጻሕፍት በመረጃነት ተጠቅሰው እናገኛለን፡፡

በዘመናት ሁሉ እግዚአብሔር ሕዝቡን የሚመራው እርሱ በመንፈሱ ባስጻፋቸው ቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በሚገኝ የእውነት ቃል ነው፤ ስለሆነም ለእምነታችንም ሆነ ለአምልኮአችን እንዲሁም ለተግባራዊ ሕይወታችን በቅዱሳት መጻሕፍት የተነገረውን የእውነት ቃል መሠረት ልናደርግ የተገባ ነው፡፡ እያንዳንዱን ርእሰ-ጉዳይ እንደ እግዚአብሔር ቃል ብቻ ልንመለከተው ያስፈልጋል፤ ለሌሎችም ሰዎች ስንናገር እንደ እግዚአብሔር ቃል መናገር ይጠበቅብናል፤ በቃሉ ውስጥ የተጻፈውን እውነት ሳንጨምር እና ሳንቀንስ በቅንነት ብንናገር የምንናገረው ቃል ፍሬያማ ሊሆን ይችላል፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ በሚጽፍለት ጊዜ፣ «የእውነትን ቃል በቅንነት /በአግባቡ/ የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ» /2ጢሞ2፡15/ ብሎታል፡፡

በምንኖርበት በዚህ ዘመን መጽሐፍ ቅዱስ በዓለም ባሉ በብዙ ሺዎች በሚቆጠሩ ቋንቋዎች ተተርጉሞ በመነበብና በመሰበክ ላይ ይገኛል፡፡ ይሁን እንጂ የያዘውን እያንዳንዱን የእውነት ቃል ሐሳቡ ከሚመለከታቸው ሰዎች፣ ከተነገረበት ጊዜ፣ ከተነገረበት ምክንያት፣ ወዘተ አንጻር በአግባቡ ካለመለየት የተነሣ በክርስቲያኑ ዓለም ውስጥ ብዙ የተዛቡና ያለቦታቸው እየገቡ የሚነገሩ ትምህርቶች ይሰማሉ፡፡ ለምሳሌ እግዚአብሔር በዘመነ ሕግ የሠራበትን አሠራር ለቤተክርስቲያን ዘመን በመጠቀም፣ አሁን ክርስቶስ የሚያምኑትን ሁሉ ከሕግ እርግማን ለመዋጀት በመስቀል ላይ አንድ ጊዜ ሞቶ ሳለ፣ «የሕግን ሥራ ካልሠራችሁ አትድኑም» እየተባለ የሚነገር ስብከት አለ፡፡ እንዲሁም ለአፍ አማኞች የተሠጡ ማስጠንቀቂያዎችን ለእውነተኛ አማኞች እንደተነገሩ በማድረግ አማኞች በክርስቶስ ሥራ በኩል ያገኙትን ዘላለማዊ ዋስትና እንዲጠራጠሩና መልካም ፍሬ እያፈሩ እንዳይኖሩ የሚያደርጉ ትምህርቶች ይደመጣሉ፡፡ በተጨማሪም በእግዚአብሔር ዘንድ ያለው የእስራኤልና የቤተክርስቲያን አንጻራዊ ስፍራ እና የግንኙነት ይዘት በትክክል ተለይቶ ካለመታወቁ የተነሣ ለእስራኤል የተሠጡ ተስፋዎችን ወደ ቤተክርስቲያን ዘመን በማምጣት፣ ቤተክርስቲያን የምድራዊ በረከት ምንጭ እንደሆነች የሚናገሩ ትምህርቶችም አሉ፡፡ አሁን የምንገኘው እንደዚህ ዓይነት ብዙ የተዛቡ ነገሮች በሚሰሙበት ወቅት ላይ ነው፡፡

ስለሆነም የእውነትን ቃል በትክክል ለመረዳትና ለመናገር ያስችል ዘንድ፣ መሠረታዊ እና ዋና ዋና የሆኑ ርእሶችን የሚያስተምሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ከብሉይ ኪዳንና ከአዲስ ኪዳን በማውጣጣት የተዘጋጁ ጽሑፎች አስፈላጊነታቸው አጠያያቂ አይደለም፡፡ ስለአይሁድ፣ ስለአሕዛብ እና ስለቤተክርስተያን መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን ማወቅ፣ የምናነባቸው ጥቅሶች ስለ የትኛው ሕዝብ እንደተነገሩ ለመረዳት ያስችለናል፤ በይበልጥ ደግሞ እግዚአብሔር በተለያዩ ክፍለ ዘመናት ከሰው ጋር የሚገናኝበትን መርህ መረዳት፣ ያነበብናቸው ክፍሎች በዚህ ዘመን ለምንኖር ያላቸውን ትርጉም እንድናውቅ ይረዳናል፡፡ እንደዚሁም የሕግንና የጸጋን መርህ፣ የጌታ ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም የመምጣቱ ዓላማ፣ የማዳን ሥራውን፣ አሁን ያለውን የሊቀካህንነት አገልግሎቱን፣ ዳግመኛ ተመልሶ መምጣቱን፣ ስለ ልዩ ልዩ ፍርዶችና ስለትንሣኤዎች እንዲሁም፣ ስለ ዘመን ፍጻሜ በተመለከተ በቅዱሳት መጻሕፍት የተነገረውን ቃል በአግባቡ መረዳትና መናገር ያስፈልጋል፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረው ሁሉ እውነት ስለሆነ፣ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገር ሰውም የእውነትን ቃል ሊናገር ይችላል፡፡ ስለሆነም አማኞች መጽሐፍ ቅዱስን በትክክል ተረድተው የእውነትን ቃል መናገር ይችሉ ዘንድ እንዲረዳቸው ታስቦ በተለያዩ ርእሶች በአጫጭሩ የተዘጋጁትን መጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች የያዘው ይህ ጽሑፍ ተዘጋጅቶ ቀርቦአል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስን በሚገባ ለመረዳት የሚያስችል መሪ ሐሳብ እናገኝ ዘንድ እግዚአብሔር ይርዳን፡፡

1. አይሁድ፣ አሕዛብ፣ እና የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን

ዓቢይ ምንባብ፣ 1ቆሮ.10፡32

የመጽሐፍ ቅዱስ አንባቢ የሆነ አንድ ሰው፣ ከመጽሐፉ እኩሌታ በላይ ይዘቱ የሚመለከተው አንድን ሕዝብ - ማለት እስራኤላውያንን - መሆኑን ማስተዋል አይሣነውም፡፡ ደግሞም፣ ይኸው ሰው እነርሱ በእግዚአብሔር ዕቅድና ምክር ውስጥ በጣም ለየት ያለ ስፍራ እንዳላቸው ይገነዘባል፡፡ ከብዙኃኑ የሰው ዘር ተለይተው በያህዌ ቃል ኪዳን ውስጥ እንዲገቡ ተደርገዋል፣ እርሱም ለእነርሱ ብቻ የሆኑና ሌሎችን ሕዝቦች የማይመለከቱ ተስፋዎች ሰጥቷቸዋል፡፡ በብሉይ ኪዳን ትረካዎችና ትንቢቶች ውስጥ የተነገረው የአይሁድ ታሪክ ብቻ ነው፤ ሌሎች ሕዝቦች የተጠቀሱት ከእነርሱ ጋር ባላቸው የተያያዘ ነገር አንጻር ብቻ ነው፡፡ እንዲያውም እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር እንደ ሕዝብ ያደረጋቸው ግንኙነቶች ምድርን ባጠቃላይ የሚመለከቱ ይመስላል፡፡ በቀደመው ኪዳን ውስጥ፣ እነሱ ታማኝና ታዛዥ ቢሆኑ፣ ምድራዊ ታላቅነት፣ ባለጠግነትና ኃይል እንደሚሆንላቸው ቃል ተገብቶላቸዋል፤ ባይታመኑና ታዛዥ ባይሆኑ ደግሞ፣ «ከምድር ዳር እሰከ ዳርቻዋ ድረስ ወዳሉ አሕዛብ ሁሉ» /ዘዳ.28፡64/ እንደሚበተኑ ተገልጾአል፡፡ እንደ ሥጋ ትውልድም ከእነርሱ ወገን እንደሚመጣ የተነገረው የመሢሑ ተስፋም ለ«ምድር ነገዶችም ሁሉ» በረከት የሚሆን ነው፡፡

የመጽሐፍ ቅዱሱ ተማሪ ምርመራውን ሲቀጥል፣ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በብዛት የተጠቀሰች ሌላ ለየት ያለች አካል ያገኛል፡- እርሷም የእግዚአብሔር ቤተ-ክርስቲያን ተብላ ተጠርታለች፡፡ ይህችም አካል ከእግዚአብሔር ጋር በዓይነቱ የተለየ ግንኙነት አላት፤ እንዲሁም እንደ እስራኤል ሁሉ፣ ለእርሷ ብቻ የሆኑ ተስፋዎችን ከእርሱ ተቀብላለች፡፡ ነገር ግን ከእስራኤል ጋር ያላቸው ተመሳሳይነት በዚሁ ብቻ ያበቃና፣ ጉልህ የሆነው ልዩነታቸው ይጀምራል፡፡ ይህች አካል ከአብርሃም የሥጋ ተወላጆች /ዝርያዎች/ ብቻ የተመሠረተች ከመሆን ይልቅ፣ እንዲያውም በእርሷ ውስጥ በአይሁድና በአሕዛብ መካከል ያለው ልዩነት አክትሟል፡፡ ግንኙነቱ በቃል ኪዳን ላይ ብቻ የተመሠረተ ሳይሆን፣ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አዳኝና ጌታ በመቀበል በሚገኘው በዳግም ልደት ላይ ነው፡፡ ቤተክርስቲያን፣ በመታዘዝ ምድራዊ ታላቅነትንና የሀብትን ብድራት ከማግኘት ይልቅ፣ ምግብና ልብስ ካገኘች ኑሮዬ ይበቃኛል እንድትልና፣ ስደትንና መጠላትን እንድትጠብቅ ትምህርት ተሰጥቹታል፤ እንዲሁም እስራኤል በልዩ ሁኔታ ከምድራዊና ጊዜያዊ ነገሮች ጋር እንደተያያዘች ሁሉ፣ ቤተክርስቲያንም እንዲሁ ከመንፈሳዊና ከሰማያዊ ነገሮች ጋር በልዩ ሁኔታ ተያይዛለች፡፡

በተጨማሪም፣ መጽሐፍ ቅዱስ እስራኤልም ሆነች ቤተክርስቲያን ከዘላለም ጀምሮ ሕልውና እንዳልነበራቸው ለአንባቢው ያሳየዋል፡፡ ሁለቱም በውል የሚታወቅ ጅማሬ አላቸው፡፡ አንባቢው መጽሐፍቅዱስን ሲያጠና የእስራኤል ሕልውና የሚጀምረው በአብርሃም መጠራት መሆኑን የሚረዳ ሲሆን፣ የቤተክርስቲያንን የልደት ቀን ሲያፈላልግ ደግሞ፣ ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ምድራዊ ሕይወት ወቅትም ሆነ ከዚያ በፊት እንዳልነበረች ይረዳል፤ ምክንያቱም ክርስቶስ ስለ ቤተክርስቲያኑ ገና ወደፊት እንደምትሆን አድርጐ ሲናገር ይገኛልና/ማቴ16፡18/፡- «በዚችም ዓለት ላይ ቤተክርስቲያኔን እሠራለሁ፡፡» ይላል፡፡

«ሠርቻለሁ፣» አሊያም «እየሠራሁ ነው፣» አይደለም የሚለው፤ ነገር ግን «እሠራለሁ፣» ነው፡፡

በመቀጠልም ከኤፌሶን 3፡5-10 ውስጥ ቤተክርስቲያን በብሉይ ኪዳን ትንቢት ውስጥ አንድም ጊዜ እንኳ እንዳልተጠቀሰች፣ ይልቁኑም በእነዚያ ዘመናት «በእግዚአብሔር ... የተሰወረች» እንደነበር ይገነዘባል፡፡ /አንዳንድ ሰዎች በተሳሳተ ሁኔታ አዳምና ሌሎቹ የብሉይ ኪዳን አበው በቤተክርስቲያን ውስጥ እንዳሉ ይናገራሉ፤ ይህ ግን ስሕተት ነው፡፡/ ከመጽሐፍ ቅዱስ አኳያም የቤተክርስቲያን ልደት በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 2 ውስጥ /መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ/፣ በምድር ላይ ያላትን ፍጻሜዋን ደግሞ በተሰሎንቄ መልእክት ምዕራፍ 4 ውስጥ /የመነጠቅ ጊዜን ይመለከታል/ ያገኘዋል፡፡

ደግሞም ተማሪው፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ የሰው ዘር ክፍፍል አንጻር፣ በመጠኑ የተጠቀሰና በሁሉም መልክ ከእስራኤልም ሆነ ከቤተክርሰቲያን ልዩ የሆነ ሌላ ወገን ያገኛል - ይህም አሕዛብ ነው፡፡ የአይሁድ ፣የአሕዛብ እና የቤተክርስቲያን አንጻራዊ ስፍራ አጠር ባለ መልክ በሚከተሉት ምንባባት ውስጥ ይገኛል፡፡

  • አይሁድ - ሮሜ.9፡4-5፤ ዮሐ.4፡22፤ ሮሜ3፡1-2
  • አሕዛብ - ኤፌ.2፡11-12፤ ማር.7፡27-28
  • ቤተክርስቲያን ( ኤፌ5፡29-33፤ 1ጴጥ.2፡9

ስለ እስራኤልና ስለ ቤተክርስቲያን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተባለውን ሲያነጻጽር፣ በአጀማመር፣ በጥሪ፣ በተስፋ፣ በአምልኮ፣ በሥነ-ምግባር መመሪያ እና በወደፊት ግባቸው የተለያዩ ሆነው ያገኛቸዋል፡፡

በጥሪ

እስራኤል

  • እግዚአብሔር አብራምን አለው፡- ከአገርህ፣ ከዘመዶችም፣ ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ፡፡ ዘፍ12፡1፡፡
  • አምላክህ እግዚአብሔር ወደ መልካም ምድር፣ ከሸለቆና ከኮረብታ የሚመነጩ የውሃ ጅረቶችና ፈሳሾች ምንጮችም ወዳሉበት ምድር ስንዴ ገብስም ወይንም በለስም ሮማንም ወይራም ማርም ወደ ሞሉባት ምድር፡-... ያገባሃል፡፡ ዘዳ.8፡7-9፡፡ እርሱም አለ፡- እኔ የአብርሃም ሎሌ ነኝ፡፡ እግዚአብሔርም ጌታዬን እጅግ ባረከው አገነነውም፤ በጎችንና፣ ላሞችን፣ ብርንም፣ ወርቅንም ወንዶች ባሪያዎችን፣ ሴቶች ባሪያዎችን፣ ግመሎችንም አህዮችንም ሰጠው፡፡ ዘፍ.24፡34-35፡፡
  • እርሱም አለ፡- እኔ የአብርሃም ሎሌ ነኝ፡፡ እግዚአብሔርም ጌታዬን እጅግ ባረከው አገነነውም፤ በጎችንና፣ ላሞችን፣ ብርንም፣ ወርቅንም ወንዶች ባሪያዎችን፣ ሴቶች ባሪያዎችን፣ ግመሎችንም አህዮችንም ሰጠው፡፡ ዘፍ.24፡34-35፡፡
  • እግዚአብሔር በላይህ የሚቆሙትን ጠላቶችህን በፊትህ የተመቱ ያደርጋቸዋል፤ በአንድ መንገድ ይመጡብሃል፣ በሰባትም መንገድ ከፊትህ ይሸሻሉ፡፡ ዘዳ.28፡7፡፡
  • እግዚአብሔር ራስ ያደርግሃል እንጂ ጅራት አያደርግህም፤ ሁል ጊዜም በላይ እንጂ በታች አትሆንም፡፡ ዘዳ.28፡13፡፡

ቤተክርስቲያን

  • ከሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች ....፡፡ ዕብ3፡1፡፡
  • እኛ አገራችን በሰማይ ነውና ...፡፡ ፊል3፡20፡፡
  • ኢየሱስም፡- ለቀበሮዎች ጉድጓድ ለሰማይም ወፎች መሳፈሪያ አላቸው ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም አለው፡፡ ማቴ8፡20፡፡
  • ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ እድፈትም ለሌለበት፡- ለማያልፍም ርስት... ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል፡፡ 1ጴጥ1፡4፡፡
  • እስከዚህ ሰዓት ድረስ እንራባለን፣ እንጠማለን፣ እንራቆታለን፣ እንጐሰማለን፣ እንከራተታለን ... ፡፡ 1ቆሮ4፡11፡፡ እግዚአብሔር በእምነት ባለጠጎች እንዲሆኑ ለሚወዱትም ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድሆች አልመረጠምን? ያዕ.2፡5፡፡
  • ከምኩራባቸው ያወጡአችኋል፤ ከዚህ በላይ ደግሞ የሚገድላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እንደሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል፡፡ ዮሐ16፡2፡፡
  • እንግዲህ እንደዚህ ሕፃን ራሱን የሚያዋርድ ሁሉ በመንግሥተ ሰማያት የሚበልጥ እርሱ ነው፡፡ ማቴ18፡4፡፡

በእርግጥ እንደ እግዚአብሔር ሐሳብ የሚኖር አይሁድ በሞት ሲለይ ወደ ሰማይ/ገነት አይሄድም አልተባለም፡፡ ልዩነቱ፣ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ማለትም እንደ እግዚአብሔር ሐሳብ መኖር ለአይሁድ የነበረው ብድራት፣ ምድራዊ እንጂ ሰማያዊ ሽልማት አለመሆኑ ላይ ነው፡፡ አሁን በያዝነው የጸጋ ዘመነ-መግቦት አይሁድም ሆኑ አሕዛብ የሚድኑት፣ ዳግመኛ በሚወለዱበት /ዮሐ.3፡3-16/ እና «ቤተ-ክርስቲያን» /ኤፌ.1፡22-23/ በምትሆን በዚያች «አንድ አካል» /1ቆሮ.12፡13/ ውስጥ በሚጨመሩበት፣ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ባለ እምነት ብቻ መሆኑ የሚያጠያይቅ አይደለም፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ በአይሁድና በአሕዛብ መካከል ያለው ልዩነት ይጠፋል /1ቆሮ12፡13፣ ገላ3፡28፣ ኤፌ2፡14፣ ኤፌ2፡11/፡፡ «አስቀድሞ አሕዛብ የነበራችሁ»፣ /1ቆሮ.12፡2/ «አሕዛብ ሳላችሁ ... »፣ የሚሉት አባባሎች የሚያስረዱን በትውልዳቸው አሕዛብም ሆነ አይሁድ የነበሩ ሰዎች፣ ወደ ቤተክርሰቲያን ሲመጡ፣ በመካከላቸው ያለው ልዩነት ጠፍቶ ሁለቱም በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት የሆኑ ክርስቲያኖች ብቻ እንደሚሆኑ ነው፡፡

በእስራኤልና በቤተክርስቲያን መካከል ያለው ልዩነት፤ ለእያንዳንዳቸው በተሰጣቸው የሥነ-ምግባር መመሪያዎች ውስጥም በተጨማሪ ይታያል፡፡ የሚከተለውን አነጻጽር፡-

በሥነ ምግባር

እስራኤል

  • አምላክህ እግዚአብሔር ልትወርሳት ወደምትገባባት ምድር ባመጣህ ጊዜ ከፊትህም ብዙ አሕዛብን፣... በመታሃቸውም ጊዜ፣ ፈጽመህ አጥፋቸው ከእነርሱም ጋር ቃል-ኪዳን
  • አታድርግ አትማራቸውም፡፡ ዘዳ.7፡1-2፡፡
  • ዓይን በዓይን ጥርስ በጥርስ እጅ በእጅ እግር በእግር መቃጠል በመቃጠል ቁስል በቁስል ግርፋት በግርፋት ይከፈል፡፡ ዘጸ.21፡ 24-25፡፡ እንዲሁም፣ ዘዳ21፡18-21፡፡

ቤተክርስቲያን

  • ጠላቶቻችሁን ውደዱ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፣ ለሚጠሉአቸሁም መልካም አድርጉ ስለሚያሳድዷችሁም ጸልዩ፡፡ (ማቴ5፡44)
  • ሲሰድቡን እንመርቃለን፣ ሲያሳድዱን እንታገሣለን፣ ክፋ ሲናገሩን እንማልዳለን፡፡ 1ቆሮ 4፡12፡13፡፡
  • እኔ ግን እላችኋለሁ ክፋውን አትቃወሙ ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት፡፡ ማቴ5፡39፡፡ ሉቃ15፡20-23፡፡

በአምልኮ ሁኔታዎች ውስጥም ልዩነት እናያለን፡፡ እስራኤላውያን ማምለክ የሚችሉት በአንድ ስፍራ እና ከእግዚአብሔር ራቅ ብለው ብቻ ነበር፤ ወደ እርሱ የሚቀርቡትም በካህን አማካኝነት ብቻ ነበር /ማለትም፣ ሁሉም ሕዝበ እስራኤል ካህን ስላልነበር ወደ እግዚአብሔር መቅረብ የሚችሉት በተለዩ የካህናት ወገኖች አማካኝነት ብቻ ነበር/፡፡ ቤተክርስቲያን ግን ሁለት ወይም ሦስት በሚሰበሰቡት በማንኛውም ስፍራ ማምለክ ትችላለች፤ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የመግባት ድፍረት አላት፤ እንዲሁም ሁሉም አባላት /አማኞች/ ካህናት ናቸው፡፡

ዘሌ.17፡8-9ን
እነዚህን አነጻጻር፡-
ከማቴ.18፡20/ ጋር
ሉቃ.1፡10ንከዕብ.10፡19-20 ጋር
ዘኁ.3፡10ን ከ1ጴጥ.2፡5 ጋር

በተስፋ

የእስራኤልና የቤተክርስቲያንን የወደፊት ሁኔታዎች አስመልክቶ በተነገሩ ትንበያዎች /ትንቢቶች/ ውስጥም ያለው ልዩነት አስደናቂ ነው፡፡ ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ ከምድር ወደ ሰማይ የምትወሰድ ሲሆን፣ ወደ ቀድሞ ስፍራዋ የምትመለሰው እስራኤል ግን ገና እጅግ ታላቅ ምድራዊ ባለጠግነትና ኃይል ይጠብቃታል፡፡ ይህን ተመልከት፤

ቤተክርስቲያን

  • በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፣ እንዲህስ ባይሆን ባልኊችሁ ነበር ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኊለሁ፡፡ ዮሐ.14፡2-3፡፡
  • በጌታ ቃል የምንላችሁ ይህ ነውና እኛ ሕያዋን ሆነን ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር ያንቀላፉትን አንቀድምም፤ ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ ከዚያም በኊላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን፡፡ 1ተሰ4፡15-17፡፡
  • እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፣ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስን እንጠባበቃለን፤ እርሱም ሁሉን እንኳ ለራሱ ሊያስገዛ እንደሚችልበት አሠራር ክቡር ሥጋውን እንዲመስል የተዋረደውን ሥጋችንን ይለውጣል፡፡ ፊል3፡20-21፡፡
  • ወዳጆች ሆይ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፡- ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም፡፡ ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን፡፡ 1ዮሐ3፡2፡፡
  • የበጉ ሠርግ ስለደረሰ ሚስቱም ራስዋን ስላዘጋጀች ደስ ይበለን ሐሴትም እናድርግ ክብርንም ለእርሱ እናቅርብ ... ያጌጠና የተጣራ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ እንድትጐናጸፍ ተሰጥቶአታል፡፡ ቀጭኑ የተልባ እግር የቅዱሳን ጽድቅ ሥራ ነውና፡፡ እርሱም ወደ በጉ ሠርግ እራት የተጠሩ ብፁዓን ናቸው ብለህ ጻፍ አለኝ፡፡ ራእ19፡7-9፡፡
  • በፊተኛው ትንሣኤ ዕድል ያለው ብፁዕና ቅዱስ ነው፤ ሁለተኛው ሞት በእነርሱ ላይ ሥልጣን የለውም፡፡ ዳሩ ግን የእግዚአብሔርና የክርስቶስ ካህናት ይሆናሉ፤ ከእርሱም ጋር ይህን ሺህ ዓመት ይነግሣሉ፡፡ ራእ20፡6፡፡

እስራኤል

  • እነሆም ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ስሙንም ኢየሱስ ትይዋለሽ፡፡ እርሱም ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፤ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘላለም ይነግሣል፤ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም፡፡ ሉቃ1፡31-33፡፡
    /ለማርያም ከተሰጡት ከእነዚህ ሰባት ተስፋዎች መካከል፣ የመጀመሪያዎቹ አምስቱ ቃል በቃል ተፈጽመዋል፡፡ ታዲያ ቀሪዎቹ ሁለቱ አይፈጸሙም ልንል የምንችለው፣ የትኛው የአተረጓጐም ሕግ በሚሰጠን ሥልጣን ነው᐀/
  • እግዚአብሔር ለስሙ የሚሆንን ወገን ከአሕዛብ ይወስድ ዘንድ አስቀድሞ እንዴት እንደጐበኘ ስምዖን ተርኮአል፡፡ ከዚህም ጋር የነቢያት ቃል ይስማማል እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፡ ከዚህ በኊላ ... እመለሳለሁ የወደቀችውንም የዳዊትን ድንኳን እንደገና እሠራታለሁ እንደገናም አቆማታለሁ ...» የሐዋ.ሥ.15፡14-16፡፡
  • እንግዲህ፡- እግዚአብሔር ሕዝቡን ጣላቸውን᐀ እላለሁ አይደለም እኔ ደግሞ እስራኤላዊና ከአብርሃም ዘር ከብንያምም ወገን ነኝና ... እንግዲህ፡- የተሰናከሉ እስኪወድቁ ድረስ ነውን᐀ እላለሁ፡፡ አይደለም ነገር ግን እነርሱን ያስቀናቸው ዘንድ በእነርሱ በደል መዳን ለአሕዛብ ሆነ፡፡ ... አንተ በፍጥረቱ የበረሀ ከነበረ ወይራ ተቈርጠህ እንደ ፍጥረትህ ሳትሆን በመልካም ወይራ ከገባህ ይልቁኑስ እነዚያ በፍጥረታቸው ያሉት ቅርንጫፎች በራሳቸው ወይራ እንዴት አይገቡም᐀ ወንድሞች ሆይ ልባሞች የሆናችሁ እንዳይመስላችሁ ይህን ምሥጢር ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ፤ የአሕዛብ ሙላት እስኪገባ ድረስ ድንዛዜ በእስራኤል በአንዳንድ በኩል ሆነባቸው፤ እንደዚሁም እስራኤል ሁሉ ይድናል፤ እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ፡- መድኃኒት ከጽዮን ይወጣል ከያዕቆብም ኃጢአተኛነትን ያስወግዳል፡፡ ሮሜ11፡1፣ 11፣ 24-26፡፡
  • > >በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል የቀረውን የሕዝቡን ቅሬታ ... ይመልስ ዘንድ ጌታ እንደገና እጁን ይገልጣል፡፡ ለአሕዛብም ምልክትን ያቆማል ከእስራኤልም የተጣሉትን ይሰበስባል ከይሁዳም የተበተኑትን ከአራቱም የምድር ማዕዘኖች ያከማቻል፡፡ ኢሳ11፡11፣12፡፡
  • > >እግዚአብሔርም ያዕቆብን ይምረዋል እስራኤልንም ደግሞ ይመርጠዋል በአገራቸውም ያኖራቸዋል መጻተኛም ከእርሱ ጋር ይተባበራል ከያዕቆብም ቤት ጋር ይጣበቃል፡፡ ኢሳ14፡1፡፡
  • ስለዚህ እነሆ፡- የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ ምድር ያወጣ ሕያው እግዚአብሔርን ዳግመኛ የማይባልበት ዘመን ይመጣል ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን፡- የእስራኤልን ልጆች ከሰሜን ምድር ካሳደዳቸውም ምድር ሁሉ ያወጣ ሕያው እግዚአብሔርን ይባላል፤ እኔም ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኊት ምድራቸው እመልሳቸዋለሁ፡፡ ኤር16፡14-15፡፡
  • እነሆ ለዳዊት ጻድቅ ቊጥቋጥ የማስነሣለት ዘመን ይመጣል ይላል እግዚአብሔር እርሱም እንደ ንጉሥ ይነግሣል ይከናወንለታልም በምድርም ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል፡፡ በዘመኑም ይሁዳ ይድናል እስራኤልም ተዘልሎ ይቀመጣል የሚጠራበትም ስም፡- እግዚአብሔር ጽድቃችን ተብሎ ነው፡፡ ኤር.23፡5-6፡፡
  • እነሆ በቊጣዬ በመዓቴ በታላቅም መቅሠፍቴ እነርሱን ካሳደድሁባት አገር ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ ወደዚህም ስፍራ እመልሳቸዋለሁ ተዘልለውም እንዲኖሩ አደርጋለሁ፣ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ፡፡ ኤር32፡37-38፡፡
  • የጽዮን ልጅ ሆይ ዘምሪ እስራኤል ሆይ እልል በይ፣ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ በፍጹም ልብሽ ሐሤት አድርጊ ደስም ይበልሽ፡፡ እግዚአብሔር ፍርድሽን አስወግዶአል ጠላትሽንም ጥሎአል የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር በመካከልሽ አለ ከእንግዲህ ወዲህ ክፉ ነገርን አታዪም ሶፎ3፡14-15፡፡

የቤተክርስቲያንን እድገት ከማጓተት፣ ተልዕኮዋን ከመበረዝ እንዲሁም መንፈሳዊ ነገሯን ከማጥፋት አንጻር፣ ሌሎች ምክንያቶች በአንድ ላይ ተደምረው ካደረሱባት ጥፋት ይልቅ፣ ለእርስዋ አይሁዳዊ ጠባይ መስጠቱ /የእስራኤል ምትክ አድርጎ መውሰዱ/ የከፋ ጉዳት አድርሶባታል፡፡ አሁን «ቤተ ክርስቲያን» ነን እያሉ እራሳቸውን የሚጠሩት የተለያዩ አካላት፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእውነተኛዋ ቤተክርስቲያን የተሰጣትን የመለየት /Separation/፣ የመሰደድ፣ በዓለም የመጠላት፣ የድህነት እና አፀፋን ያለመመለስ መንገድ ፈጽሞ እየተከተሉ አይደለም፤ ነገር ግን እነርሱ፣ ለአይሁድ ማለትም ለእስራኤል የተሰጡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ለቤተክርስቲያን እንደተሰጡ አድርገው በመውሰድ፣ ዓላማቸውን ወደ ዓለም ሥልጣኔ፣ ሀብት /ንዋይ/ ወደ ማጋበስ፣ ሥርዓቶችን ወደ መደንገግ፣ ትላልቅ «የአብያተ ክርስቲያናት» ሕንጻዎችን ወደ መገንባት፣ የእግዚአብሔርን ቡራኬ በአገሮች መካከል በሚከሰቱ የጦርነት ግጭቶች ላይ ወደ መጋበዝ፣ እንዲሁም በእግዚአብሔር ፊት እኩል የሆኑ ወንድማማቾችን «ካህን» እና «ምዕመን» ብሎ ወደ መለያየት ዝቅ ለማድረግ እየተጠቀሙባቸው ይገኛሉ፡፡


2. ሰባቱ ዘመናተ-መግቦት /Dispensations/

የሚታወቁት፣ የሁለቱን ማለትም የኃጢአትንና ሰው የተጣለበትን ኃላፊነት የሚመለከቱትን ጥያቄዎች በተመለከተ፣ እግዚአብሔ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ጊዜ የተለያየ ርዝማኔና ባሕርያት ባላቸው ሰባት ወቅቶች ተከፋፍሎ እናገኘዋለን /ጊዜ ስንል ከአዳም መፈጠር ጀምሮ በራእ21፡1 ውስጥ እስካለው «አዲስ ሰማይና ምድር፣» መምጣት ድረስ ያለውን ጠቅላላ ወቅት ማለታችን ነው/፤ እነዚህም የጊዜ ክፍልፋዮች በተለምዶ ዘመናተ-መግቦት (Dispensations) ተብለው ይጠራሉ፤ /በእርግጥ እነዚህ ወቅቶች፣ «ዘመናት» /ኤፌ. 2፡7/፣ «ቀናት» ወዘተ... ተብለውም ተጠርተዋል/፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እነዚህ ዘመናት አንዱ ከሌላው ተለይተው ር ከጠቅላለው የሰው ልጅ ወይም ከተወሰኑ የሰው ልጅ ክፍሎች ጋር ባለው ግንኙነት ላይ በሚያደርገው ለውጥ ነው፡፡ እያንዳንዱ ዘመነ-መግቦት ለተፈጥሮአዊው ሰው እንደ አንድ አዲስ መፈተኛ ጊዜ /Probationary Period/ ተደርጐ ሊወሰድ ይችላል፤ እያንዳንዳቸውም ደግሞ የሚጠናቀቁት የዚህኑ ፍጥረታዊ ሰው ፍጹም ውድቀት በሚያመለክቱ ፍርዶች ነው፡፡

ከእነዚህ ዘመናተ-መግቦት ወይም ክፍለ ጊዜያት መካከል አምስቱ አስቀድመው ተፈጽመዋል፤ አሁን ያለነው በስድስተኛው፣ /ምናልባትም በእርሱ መገባደጃ/ ላይ ነው፤ ሰባተኛውና የመጨረሻው ዘመነ-መግቦት የሆነው የሺህ ዓመቱ መንግሥት ደግሞ ከፊታችን ይገኛል፡፡

1. ሰው መልካምና ክፉን ከማወቁ በፊት /መልካምና ክፉን ያለማወቅ ዘመነ-መግቦት/ - Dispensation of Innocence

ይህ ዘመነ-መግቦት በዘፍ2፡7 ውስጥ ካለው ከአዳም መፈጠር ጀምሮ፣ በውድቀቱ ምክንያት እርሱ ከኤደን ገነት እስከተባረረበት ድረስ ያለውን ጊዜ የሚያጠቃልል ሲሆን ቆይታው ከጥቂት ቀናት የበለጠ አልነበረም/ዘፍ2፡7-3፡24/፡፡ ንጹሕ እና መልካምና ክፋን የማያውቅ ሆኖ የተፈጠረው አዳም ኑሮውን ከሚስቱ ከሔዋን ጋር በኤደን ገነት የአትክልት ስፍራ ውስጥ እንዲያደርግና በዚያ ሲኖርም መልካምንና ክፉን ከሚያሳውቀው የዛፍ ፍሬ እንዳይበላ በሚያግደውና ኃላፊነትን በሚጠይቀው ትእዛዝ ሥር እንዲመላለስ ተደረገ፡፡ መልካምና ክፉን ያለማወቅ ዘመነ-መግቦት ውጤትም፣ የመጀመሪያ የሆነው እና፣ ሁሉን ነክ ተፅዕኖ ያደረገው ከተፈጠሮአዊው ሰው ውድቀቶች ሁሉ እጅግ የከፋ የሆነው ውድቀት ሆነ፤ በዚህም የተነሣ ፍጥረት በሙሉ በኃጢአትና በመበስበስ ጥፋት ቀንበር ሥር ወደቀ/ሮሜ5፡12-21፤8፣19-23/፡፡ በመጨረሻም፣ «ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክ ከዔደን ገነት አስወጣው» በሚለው ፍርድ ተጠናቀቀ፡፡ እነዚህን ተመልከት ዘፍ1፡26፤ 2፡16፣17፤ 3፡6፤ 3፡22-24፡፡

2. ሰው በሕሊና ሥር /የሕሊና ዘመነ-መግቦት/ - Dispensation of Conscience

ዘፍ3፡1-8፡14፡፡ አዳምና ሔዋን በሠሩት ኃጢአትና ያንንም ተከትሎ በመጣው ውድቀት የተነሣ፣ መልካምና ክፉን ማወቅን አገኙ፤ ወደ ትውልዳቸውም አስተላለፉት፡፡ ይህም ለሰው ሕሊና ወይም ልቡና ትክክለኛ የሥነ-ምግባር ፍርድን/ውሳኔን/ የማድረግ መሠረትን ሰጠው፤ በዚህም የተነሣ ትውልዱ፣ መልካምን የማድረግ ከክፉም የመራቅ የኃላፊነት መለኪያ ሥር ሆነ፡፡ የሕሊና ዘመነ-መግቦት ርዝማኔ ወይም ቆይታ 1656 ዓመታት /ዘፍ5፡1-29፤7፡11/ ሲሆን፣ ውጤቱም እንደሚከተለው ነበር፤ «ሥጋን የለበሰ ሁሉ በምድር ላይ መንገዱን አበላሽቶ ነበርና፣» «የሰው ክፋት በምድር ላይ ... በዛ፣ የልቡ አሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ... ሆነ፤» እናም እግዚአብሔር ለተፈጥሮአዊው ሰው ሁለተኛ የሆነውን የመፈተኛ ወቅት በጥፋት ውኃ ፍርድ ዘጋው፡፡ የሚከተሉትን ተመልከት፤ ዘፍ3፡7፣22፤ 6፡5፣11፣12፤ 7፡11፣12፣23፡፡

3. ሰው ምድርን በማስተዳደር ሥልጣን /የሰው መንግሥት ዘመነ-መግቦት - Dispensation of Human Government

ዘፍ8፡15-11፡9፡፡ ከአስፈሪው የጥፋት ውኃ ፍርድ መካከል እግዚአብሔር ስምንት ሰዎችን አዳነ፤ ውኃው ከደረቀ በኋላም እርሷን ከማስተዳደርና ከመግዛት ትልቅ ሥልጣን ጋር በፍርድ የነጻችውን ምድር/Purified Earth/ ሰጣቸው፡፡ ይህንንም የማድረግ ኃላፊነት የኖህና የእርሱ ተወላጆች /ትውልዶች/ ነበር፡፡ የሰው ልጅ መንግሥት ዘመነ-መግቦት የቆየው ለ427 ዓመታት /ዘፍ11፡10-12፡9/ ያህል ሲሆን፣ ውጤቱም በሰናዖር ሜዳ ላይ የሰው ልጆች ከእግዚአብሔር ፈጽሞ በመለየት ራሳቸውን ችለው ለመኖር ያደረጉት ክፉ ሙከራ ሆነ፤ ይህ ዘመን የተጠናቀቀውም ቋንቋዎችን በመደበላለቅ ፍርድ ነው፡፡ እነዚህን ተመልከት፤ ዘፍ9፡1፣2፤ 11፡1-4፤ 11፡5-8፡፡

3. ሰው ምድርን በማስተዳደር ሥልጣን /የሰው መንግሥት ዘመነ-መግቦት - Dispensation of Human Government

ዘፍ8፡15-11፡9፡፡ ከአስፈሪው የጥፋት ውኃ ፍርድ መካከል እግዚአብሔር ስምንት ሰዎችን አዳነ፤ ውኃው ከደረቀ በኋላም እርሷን ከማስተዳደርና ከመግዛት ትልቅ ሥልጣን ጋር በፍርድ የነጻችውን ምድር/Purified Earth/ ሰጣቸው፡፡ ይህንንም የማድረግ ኃላፊነት የኖህና የእርሱ ተወላጆች /ትውልዶች/ ነበር፡፡ የሰው ልጅ መንግሥት ዘመነ-መግቦት የቆየው ለ427 ዓመታት /ዘፍ11፡10-12፡9/ ያህል ሲሆን፣ ውጤቱም በሰናዖር ሜዳ ላይ የሰው ልጆች ከእግዚአብሔር ፈጽሞ በመለየት ራሳቸውን ችለው ለመኖር ያደረጉት ክፉ ሙከራ ሆነ፤ ይህ ዘመን የተጠናቀቀውም ቋንቋዎችን በመደበላለቅ ፍርድ ነው፡፡ እነዚህን ተመልከት፤ ዘፍ9፡1፣2፤ 11፡1-4፤ 11፡5-8፡፡

4. ሰው በተስፋ ቃል /የተስፋ ዘመነ-መግቦት/ - Dispensation of Promise

ዘፍ11፡10-ዘጸ12፡51፡፡ የባቢሎንን ግንብ በመገንባታቸው ምክንያት እንዲበታተኑ ከተደረጉት ሰዎች ትውልድ መካከል፣ እግዚአብሔር አብርሃም የተባለ አንድን ሰው ጠራ፤ የተስፋ ቃል ሰጠው፤ ከእርሱም ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፡፡ ለአብርሃምና ለትውልዶቹ ከተሰጡት የተስፋ ቃላት መካከል አንዳንዶቹ ፍጹም በጸጋ የሆኑና ከምንም ቅድመ ሁኔታ ጋር ያልተያያዙ ነበሩ፡፡ ከእነዚህም ከፊሎቹ ቃል በቃል ተፈጽመዋል፤ ቀሪዎቹ ደግሞ ወደፊት የሚፈጸሙ ናቸው፡፡ ሌሎቹ የተስፋ ቃላት ደግሞ የእስራኤላውያንን ታማኝነትና መታዘዝ እንደ ቅድመ-ሁኔታ የሚጠይቁ ነበሩ፡፡ እነዚህም ቅድመ-ሁኔታዎች በፍጹም ባለመከበራቸው /በመጣሳቸው/ ምክንያት የተስፋ ዘመነ-መግቦት ውጤት፣ የእስራኤል ፍጹም መውደቅ ሆነ፤ በግብፅ ውስጥ በባርነት በመታሰር ፍርድም ተዘጋ፡፡ የዚህ ዘመን ርዝማኔ 430 ዓመታት ነው /ዘጸ12፡40፤ ገላ4፡30/፡፡

«በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ» በሚል ኃይለ-ቃል የተጀመረው የኦሪት ዘፍጥረት መጽሐፍ መደምደሚያው «በግብፅ ምድር በ-ሬሣ- ሳጥን ውስጥ...» በሚሉ ቃላት የተዘጋ ነው፡፡ የሚከተሉትን ተመልከት፤ ዘፍ.12፡1-3፤ 15፡5፤ 26፡3፤ 28፡12፣13 እና 13፡14-17፤ ዘጸ1፡13፣14፡፡

5. ሰው በሕግ ሥር /የሕግ ዘመነ-መግቦት/ - Dispensation of Law

ዘጸ13፡1-ማቴ4፡1፣ 11፡11፣ ሉቃ16፡16፡፡ ረዳት አልባ የሆነውን ሰው ለመርዳትና የተመረጠውን ሕዝብ /ሕዝበ እስራኤልን/ ከአስጨናቂዎቹ መዳፍ ለመቤዠት፣ የእግዚአብሔር ጸጋ አሁንም ዳግም መጣ፡፡ በሲና ምድረ በዳ ውስጥ የሕጉን ቃል-ኪዳን ሐሳብ አቀረበላቸው፡፡ እነርሱም በቀጣይ በጸጋ ላይ የተመሠረተ ግንኙነት እንዲኖር በትሕትና ከመለመን ይልቅ፣ «እግዚአብሔር ያለውን ሁሉ እናደርጋለን፣» ብለው በልበ-ሙሉነት መለሱ፡፡ ይህ ዘመን የቆየው ከ1700 ዓመታት በላይ ነው /ከሙሴ እስከ ክርስቶስ ድረስ/፡፡ በምድረ በዳው ውስጥም ሆነ ወደ ርስታቸው ከገቡ በኋላ፣ እግዚአብሔር ሰውን ሕግ በመስጠት መፈተኑን በፍርድ ዘጋው፤ እናም በመጀመሪያ እስራኤል፣ ቀጥሎም ይሁዳ ከርስታቸው ተባርረው ተበታተኑ፡፡ በዕዝራና በነህምያ አማካኝነትም ከዚያ በኋላ ጥቂት ቅሬታዎች ተመለሱ፣ ከእነርሱም ወቅቱ ሲደርስ ክርስቶስ «ከሕግ በታች ሆኖ ከሴት ተወለደ፡፡» እርሱንም ለመስቀል፣ አይሁድም አሕዛብም በአንድነት አሤሩበት፡፡ እነዚህን ተመልከት፤ ዘጸ19፡1-8፤ 25፡1-11፤ ሮሜ10፣5፤ ገላ3፡10፤ ሮሜ3፣19፣20፤ 2ነገሥ17፡1-18፤ 25፡1-11፤ ሐዋ.2፡22፣23፤ 7፡51፣52፡፡

6. ሰው በጸጋ ሥር /የጸጋ ዘመነ-መግቦት/ - Dispensation of Grace

ማቴ4፡1-ራእ19፡21፤ ዮሐ1፡17፡፡ የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የመሥዋዕትነት ሞት፣ መዳንን ማለትም የዘላለም ሕይወትን ምንም ሳይታከልበት በጸጋ ብቻ የሚገኝበትን ዘመነ-መግቦት አበሰረልን፤ ይህም፣ በሕጉ ጊዜ እንደነበረው እግዚአብሔር ከሰዎች ጻድቅ መሆንን የሚጠይቅበት ሳይሆን፣ ነገር ግን እርሱ ራሱ ጽድቅን ለሰዎች እንዲሁ የሚሰጥበት መንገድ ነው፡፡

አሁን ባለንበት በዚህ የጸጋ ዘመነ-መግቦት፣ መዳን ፍጹምና ዘላለማዊ ሆኖ በአንድ የእምነት ቅድመ ሁኔታ ብቻ ለአይሁድም ሆነ ለአሕዛብ በነጻ ቀርቧል፡፡

  • ላችኋለሁ በእኔ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፡፡ ዮሐ6.47፡፡
  • እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፣ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም፡፡ ዮሐ5፡24፡፡
  • በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል፤ እኔም የዘላለም ሕይወትን እስጣቸዋለሁ ለዘላለምም አይጠፉም፡፡ ዮሐ1ዐ፡27፣28፡፡
  • ጸጋው በእምነት አድኗችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም፡፡ ኤፌ2፡8፣9፡፡

እንደሌሎቹ ዘመናተ-መግቦት ሁሉ፣ ሰው በጸጋ የተፈተነበት የዚህ ዘመነ-መግቦት ውጤትም፣ በማያምነው ዓለምና በከዳተኛዋ «ቤተክርስቲያን» ላይ የሚደረገው ፍርድ እንደሚሆን ተተንብዮአል፡፡ እነዚህን ተመልከት፤ ራእ3፡15፣16፤ ሉቃ18፡8፤ 17፡26-30፤ እና 2ተሰ.2፡7-12፡፡

የዚህ ዘመን ርዝማኔ ከመጀመሪያው የክርስቶስ ምጽአት-ከድንግል ተወልዶ በሥጋ የመጣበት- እስከ ሁለተኛው ምጽአት ያለውን ጊዜ የሚያጠቃልል ሲሆን፣ አሁን እስከምንገኝበት ወቅት ድረስ 2000 ዓመታት ያህል ቆይቶአል፡፡ በዘመነ-መግቦቱ መዝጊያ/መጨረሻ/ ላይ የሚሆነው የመጀመሪያው ክስተት፣ የጌታ ከሰማይ ለቅዱሳኑ መውረድ ነው፤ በዚያን ጊዜም ያንቀላፉት ቅዱሳን ከሌሎቹ ሙታን ተለይተው ይነሣሉ፤ እናም በሕይወት ከሚገኙ አማኞች ጋር በአንድነት «ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁል ጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን፡፡» /1ተሰ.4፡16-17/

በመቀጠል፣ «ታላቁ መከራ» የሚባለው አጭር ጊዜ ይከተላል፡፡ እነዚህን ተመልከት፤ ማቴ24፡21፡22፤ ሶፎ1፡15-18፤ ዳን12፡1 እና ኤር3ዐ፡5-7፡፡

ከዚህ በኋላም የሚከሰተው የጌታ በኃይልና በታላቅ ክብር ሆኖ በአካል ወደ ምድር መምጣት እንዲሁም፣ የሰባተውኛውና የመጨረሻው ዘመነ-መግቦት መጀመሪያ ላይ የሚሆኑት ፍርዶች /በሕይወት በሚገኙ ሕዝቦች ላይ የሚደረግ፣ ማቴ25፡31-46/ መፈጸም እና የሰይጣን በጥልቁ ውስጥ ለሺህ ዓመት መታሠር ነው፡፡ የሚከተሉትን ተመልከት፤ ማቴ24፡29፣3ዐ፤ 25፡31-46፡፡

7. ሰው በክርስቶስ በሚገዛው መንግሥት ሥር /የሺህ ዓመቱ ዘመነ-መግቦት/ - Dispensation of Divine Government, or Millennium

ራእ20፡1-10፡፡ ክርስቶስ በአካል ወደ ምድር ሲመለስ ከሚሆኑት የማጽዳት ፍርዶች በኋላ፣ እርሱ ወደ ቀድሞ ስፍራዋ በተመለሰችው እስራኤልና በምድር ላይ ሁሉ ለአንድ ሺህ ዓመት በይፋና በአካል ይነግሣል፡፡ ይህ፣ «አንድ ሺው ዓመት /Millennium/» እየተባለ የሚጠራው ዘመን ነው፡፡ የመንግሥቱ መቀመጫ የምትሆነውም አሁን በእስራኤል አገር ያለችው ምድራዊቷ ኢየሩሳሌም ከተማ ናት፤ እንዲሁም በጸጋ ዘመነ-መግቦት የዳኑትን ማለትም ቤተ ክርስቲያንን ጨምሮ ያሉት የብሉይ ኪዳን ቅዱሳን በሰማይ ሆነው የክብሩ ተባባሪዎች ይሆናሉ፡፡ ይህም ዘመን ለሕዝበ-እስራኤል በቀደመው ኪዳን ውስጥ ቃል የተገባላቸው የተትረፈረፈ በረከት፣ ብልጽግና እና ሰላም የሚፈጸምበት ነው፤ በረከቱም ለምድር፣ ለምድር ሕዝቦች እና ለፍጡራን በሙሉ ይተርፋል፡፡ እነዚህን ተመልከት ሐዋ15፣14-17፤ ኢሳ2፡1-4፤ ራእ19፡11-21፤ 2ዐ፡1-6፤ ኢሳ11ን በሙሉ፡፡

ነገር ግን ከዚያ በኋላ ሰይጣን «ለጥቂት ጊዜ ሲፈታ»፣ የተፈጥሮአዊው ሰው ልብ እንደወትሮው ሁሉ በቀላሉ ሊስት የሚችል ሆኖ ያገኘዋል፤ እናም አሕዛብን፣ በጌታ እና በቅዱሳኑ ላይ ለጦርነት ይሰበስባቸዋል፤ ይህ የመጨረሻ የሆነው ዘመነ-መግቦትም እንደ ሌሎቹ ሁሉ በፍርድ ይዘጋል፡፡ «ታላቁ ነጭ ዙፋን» ይሰየማል፤ ኃጥአን /ማለትም በክርስቶስ ኢየሱስ አምነው ያልዳኑ/ ሙታን ከየመቃብሮቻቸው ይነሣሉ፤ በመጨረሻም ይፈርድባቸዋል፤ ከዚያም «አዲስ ሰማይ እና አዲስ ምድር» ይመጣሉ፤ በዚያም፣ «ጊዜ /time/» ያበቃና፣ «ዘላለም /eternity/» ይጀምራል፡፡ የሚከተሉትን ተመልከት፤ ራእ2ዐ፡3፣7-15፤ 21 እና 22ን በሙሉ፡፡

3. ሁለቱ የክርስቶስ ምጽአቶች

ዐቢይ ምንባብ፣ 1ጴጥ1፡11

ማንም ሰው የብሉይ ኪዳንን ትንቢቶች በጥንቃቄ ሲያጤን፣ የመሢሑን ምጽአት በተመለከተ ሁለት የተለያዩና ተቃራኒ የሚመስሉ የትንቢት መስመሮች/አቅጣጫዎች/ ማጋጠማቸው የማይቀር ነው፡፡ አንደኛው የትንቢት ክፍል እርሱ በድካምና በውርደት፣ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ፣ ከደረቅ መሬት እንደሚወጣ ሥር የሆነ፣ መልክና ውበት የሌለው፣ ይወደድም ዘንድ ደም ግባት የሌለው ሆኖ እንደሚመጣ የሚናገር ነው፤ እንዲሁም፣ እጆቹና እግሮቹ እንደሚቸነከሩ እና መቃብሩም ከክፉዎች ጋር እንደሚሆን ይናገራል፡፡ እነዚሀን ተመልከት፤ /ኢሳ53ሙሉው ምዕራፍ፤ 7፡14፤ መዝ22፡1-18፤ 9፡26፤ ዘካ13፡6፣7፤ ማር14፣27/፡፡

ሌላኛው የትንቢት አቅጣጫ ደግሞ፣ ምድርን አስፈሪ በሆኑ ፍርዶች ስለሚያነጻ፣ የተበታተኑትን የእስራኤል ወገኖች ዳግም ስለሚሰበስብ፣ ከሰሎሞን ውበት በሚበልጥ ሁኔታ የዳዊትን ዙፋን ስለሚያስመልስ፣ እንዲሁም ታላቅ ሰላምና ፍጹማዊ የሆነ ጽድቅ ያለበትን መንግሥት ስለሚመሠርት፣ ድንቅና የሚቋቋመው ስለማይኖረው ልዑል የሚናገር ነው፡፡ እነዚሀን እንደ ምሳሌ ተመልከት፤ ኢሳ11፡1፣2፣1ዐ-12፤ ዘዳ3ዐ፡1-7፤ ኢሳ9፡6፣7፤ 24፡21-23፤ 40፡9-11፤ ኤር23፡5-8፤ ዳን7፡13፣14፤ ሚክ5፡2፤ ማቴ1፡1፤ 2፡2፤ ሉቃ1፡31-33፡

መሢሑን የሚመለከቱት ትንቢቶችም ወቅታቸውን ጠብቀው በኢሳይያስ ትንቢት መሠረት በድንግሊቱ ልጅ መውለድ፣ እንዲሁም በሚክያስ ትንቢት መሠረት ደግሞ ይኸው ነገር /ማለትም የድንግሊቱ መውለድ/ በቤተልሔም ውሰጥ በመፈጸም ተጀምሮ በመቀጠል፣ የመሢሑን መዋረድ /ዝቅ ማለት/ በሚመለከት የተተነበዩት ትንቢቶች በሙሉ ቃል በቃል ተፈጽመዋል፡፡ ነገር ግን «ትሑት ሆኖ በአህያም፣ በአህያይቱ ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ»፣ የመጣውን ንጉሣቸውን አይሁድ አልተቀበሉትም፤ ይልቁንም ሰቀሉት፤ ዘካ9፡9ን ከማቴ21፡1-5 ወዘተ ጋር አነጻጽር፤ ዮሐ19፡15፣16፡፡

ይሁን እንጂ ግን፣ የሰው ክፋት እግዚአብሔር ሆነ ብሎ ያቀደውን ነገር አዛብቷል ብለን መደምደም የለብንም፤ ምክንያቱም፣ ምድራዊ ሥቃዩን የሚመለከቱት ትንቢቶች እንደተፈጸሙ ሁሉ፣ የመሢሑን ምድራዊ ክብር የሚመለከቱት ትንቢቶችም ቃል በቃል የሆነ ፍጻሜ የሚያገኙበት የልጁ ሁለተኛ ምጽአት በእግዚአብሔር ምክር ውስጥ ተካቷልና፡፡ እነዚሀን ተመልከት፤ ሆሴ3፡4፣5፤ ሉቃ1፣31-33 /ቊ.31 አስቀድሞ ቃል በቃል ተፈጽሞአል/፤ ሐዋ1፡6፣7፤ 15፡14-17፤ ማቴ24፡27-3ዐ፡፡

አይሁድ መሢሐቸው ስለሚቀበለው መከራና ሥቃይ፣ ነቢያት የተናገሩትን በሙሉ ለማመን ልባቸው የዘገየ ነበር፤ እኛ ደግሞ ስለ እርሱ ክብር የተናገሩትን ለማመን ልባችን የዘገየ ሆኖአል፡፡ /ይህም፣ ለእርሱ ዳግመኛ ምጽአት ናፍቆት አልባ በመሆናችንና እንዲሁም በአንዳንዶችም ዘንድም ይህንን ትምህርት በማዛባት የሚገለጥ ነው፡፡/ በእርግጥ የሚበልጥ ነቀፋ የሚያስከትለው የእኛ ነው፤ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ቤተልሔሙ ሕፃንና እንደ ናዝሬቱ አናፂ ሆኖ መምጣቱን ከማመን ይልቅ፣ «በሰማይ ደመና በኃይልና በታላቅ ክብር» እንደሚመጣ ማመን ይቀላልና፡፡ በእርግጥ እኛ የመጀመሪያውን ያመንነው ነቢያት ስለተናገሩት ሳይሆን፣ ስለተፈጸመ ነው፤ እናም አይሁድን ስለ አለማመናቸው ምክንያት መንቀፍን ማቆም ይገባናል፡፡ ለእነዚህ በርካታ ለሆኑና ለማያጠራጥሩ ትንቢቶች ግልጥ ትርጉም እንዴት ሊታወሩ ቻሉ የሚል ጥያቄ ቢነሣ፣ መልሱ እነርሱ የታወሩት፣ ልክ ብዙ ክርስቲያኖች፣ ስለ እርሱ ምድራዊ ክብር ለሚናገሩትና ከእነዚያ የበለጠ ቊጥር እና እንደነሱ ግልጥ ትርጉም ላላቸው ትንቢቶች እንደታወሩት ዓይነት ነው፣ የሚል ነው፤ ይህም ሊሆን የቻለው በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ላሉ ምንባቦች አጉል የሆነ «መንፈሳዊ ትርጓሜ» በመስጠት ነው፡፡ በሌላ አባባል ልክ አሁን አንዳንድ ዘመናዊ ጸሐፊዎች ስለመሢሑ ምድራዊ ክብር የሚናገሩት ትንቢቶች ቃል በቃል (Literally) መተርጐም የለባቸውም ብለው ለሕዝቡ እንደሚያስተምሩት ሁሉ፣ የድሮዎቹ ጸሐፊዎችም ስለ መሢሑ ሥቃይና መከራ የሚናገሩት ትንቢቶች ቃል በቃል (Literally) መተርጐም የለባቸውም እያሉ ለሕዝቡ ይናገሩ ነበር፡፡

ነገር ግን ሁለተኛው ምጽአት ለቤተክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ለአይሁድም ጭምር የተሰጠ ተስፋ ነው፡፡

ጌታችን የመስቀሉን መሥዋዕትነት ከመፈጸሙ በፊት ግራ ለተጋቡትና አዝነው ለነበሩት ደቀመዛሙርቱ ከተናገረው የመጨረሻ የማጽናኛና የምክር ቃላት መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡

  • ልባችሁ አይታወክ፤ በእግዚአብሔር እመኑ፤ በእኔም ደግሞ እመኑ፡፡ በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤ እንዲህስ ባይሆን ባልኋችሁ ነበር ስፍራ አዘጋጅላቸው ዘንድ እሄዳለሁና፣ ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፣ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ፡፡ ዮሐ14፡1-3፡፡

እዚህ ስፍራ ጌታ ስለ ዳግም ምጽአቱ የተናገረው ልክ ስለ መሄዱ በተናገረባቸው ዓይነት ቃላት ነው፡፡ ሁለተኛው፣ ማለትም መሄዱ አካላዊ እና በሚታይ ሁኔታ የተፈጸመ መሆኑን እናውቃለን፡፡ ምጽአቱ «መንፈሳዊ» እንጂ አካላዊ የሆነ አይደለም ካልን፣ በሌላ የቅዱሳት መጻሕፍት ምንባቦች ላይም እንዲህ ያለውን ተለጥጦ የመጣ ትርጉም የግድ ማግኘት አለብን፡፡ ነገር ግን እንዲህ ያሉ ምንባቦች ከቶ አይገኙም፡፡

ነገር ግን በእንዲህ ዓይነቱ ወሳኝ ነጥብ ላይ አጠራጣሪ ነገር ውስጥ እንድንገባም ሆነ የራሳችንን አመለካከት እንድናስቀምጥ አልተተውንም፡፡ ልክ ጌታ በዕርገቱ ጊዜ ከደቀመዛሙርቱ እይታ በተሰወረበት ቅጽበት፣ «ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች በአጠገባቸው ቆሙ፤» ደግሞም «የገሊላ ሰዎች ሆይ፣ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ስለምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፣ እንዲሁ ይመጣል፡፡» ሐዋ1፡11፡፡ 1ተሰ4፡16፣17ም ተመሳሳይ አባባል አለው፡፡

  • ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፣ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤ ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን፡፡
  • የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፣... ቲቶ2፡13፡፡
  • እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፣ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን፤ እርሱም ሁሉን እንኳ ለራሱ ሊያስገዛ እንደሚችልበት አሠራር፣ ክቡር ሥጋውን እንድንመስል የተዋረደውን ሥጋችንን ይለውጣል፡፡ ፊል3፡2ዐ፣21፡፡
  • ወዳጆች ሆይ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፣ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም፡፡ ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን፡፡ 1ዮሐ3፡2፡፡
  • እነሆ በቶሎ እመጣለሁ፣ ለእያንዳንዱም እንደሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ፡፡ ራእ22፡12፡፡

እነዚህ ሁሉ የቅዱሳት መጻሕፍት ክፍሎች የሚያሳዩን፣ ዳግም ምጽአቱ አካላዊና በሚታይ መልክ የሚፈጸም መሆኑን ነው፤ እና ስለዚህም የአማኝ ሞት፣ የኢየሩሳሌም መፍረስ /መውደም/፣ በጴንጠቆስጤ ወቅት የሆነው የመንፈስ ቅዱስ መውረድ፣ ወይም ደግሞ የክርስትናም ቀስ በቀስ መስፋፋት፣ ዳግም ምጽአቱን የሚተኩ አይደሉም፤ ነገር ግን ዳግም ምጽአቱ ለቤተክርስቲያን «የተባረከ ተስፋ» ሲሆን፣ ያንቀላፉ ቅዱሳን የሚነሡበትና በዚያን ወቅት በሕይወት ከሚገኙትና «ከሚለወጡት» /1ቆሮ15፡51፣52/ ቅዱሳን ጋር፣ ከጌታ ጋር ለመገናኘት የሚነጠቁበት ጊዜ ነው፤ እኛ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች የሆንነው እርሱን የምንመስልበት እንዲሁም ታማኝ የሆኑቱ ቅዱሳን ከደኅንነታቸው በኋላ ስለስሙ ብለው ለሠሩት መልካም ሥራ የሚሸለሙበት ጊዜ ነው፡፡

የሚከተሉትም የቅዱሳት መጻሕፍት ክፍሎችም በሁለቱ የጌታችን ምጽአቶች መካከል ያለውን ልዩነት በደንብ ያሳያሉ፡፡ b¥nÚ[R XNmLk¬cWÝ(

የመጀመሪያው ምጽአት

  • በዚያም ሳሉ የመውለጃዋ ወራት ደረሰ፣ የበኲር ልጅዋንም ወለደች፣ በመጠቅለያም ጠቀለለችው፤ በእንግዶችም ማደሪያ ስፍራ ስላልነበራቸው በግርግም አስተኛችው፡፡ ሉቃ2፡7፡፡
  • አሁን ግን በዓለም ፍጻሜ ራሱን በመሠዋት ኃጢአትን ሊሽር አንድ ጊዜ ተገልጦአል፡፡ ዕብ9፡26፡፡
  • የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአልና፡፡ ሉቃ19፡1ዐ፡፡
  • ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር ወደ ዓለም አልላከውምና፡፡ ዮሐ3፡17፡፡
  • ዓለምን ላድን እንጂ በዓለም ልፈርድ አልመጣሁምና ቃሌን ሰምቶ የማይጠብቀው ቢኖር እኔ አልፈርድበትም፡፡ ዮሐ12፡47፡፡

ሁለተኛው ምጽአት

  • በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ ይታያል፣ በዚያን ጊዜም የምድር ወገኖች ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ፣ የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር በሰማይ ደመና ሲመጣ ያዩታል፤ ማቴ24፡3ዐ፡፡
  • እንዲሁ ክርስቶስ ደግሞ፣ የብዙዎችን ኃጢአት ሊሸከም አንድ ጊዜ ከተሠዋ በኋላ፣ ያድናቸው ዘንድ ለሚጠባበቁት ሁለተኛ ጊዜ ያለ ኃጢአት ይታይላቸዋል፡፡ ዕብ 9፡28
  • ጌታ ኢየሱስ ከሥልጣኑ መላእክት ጋር ከሰማይ በእሳት ነበልባል ሲገለጥ፣ ... መከራንም ለምትቀበሉ ከእኛ ጋር ዕረፍትን ብድራት አድርጎ እንዲመልስ በእግዚአብሔር ፊት በእርግጥ ጽድቅ ነውና፡፡ እግዚአብሔርን የማያውቁትን ለጌታችንም ለኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የማይታዘዙትን ይበቀላል፤ 2ተሰ2፡7፣8፡፡
  • ቀን ቀጥሮአልና፣ በዚያም ቀን ባዘጋጀው ሰው እጅ በዓለሙ ላይ በጽድቅ ሊፈርድ አለው፤ ስለዚህም እርሱን ከሙታን በማሰነሣቱ ሁሉን አረጋግጦአል፡፡ ሐዋ17፡31፡፡

አንባቢው እነዚህን መሰል ንጽጽሮች በብዛት ማውጣት ይችላል፡፡ ይሁንና አሁን እዚህ ለእስራኤልም ሆነ ለቤተክርስቲያን የተሰጡት የተስፋ ቃላት እውን ይሆኑ ዘንድ የጌታ ወደ ምድር መመለስ የግድ እንደሚያስፈልግ ለማሳየት ከላይ የቀረቡት ጥቅሶች በቂ ናቸው፡፡

(ማሳሰቢያ፡- ለመጽሐፍ ቅዱስ ጀማሪ አጥኚዎች፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነውን ክርስቶስ ዳግመኛ በአካል የመምጣቱን ትምህርት በመቃወም በተለያዩ ስፍራዎች የቀረቡትን መላምቶች በመጠኑ መመልከቱ ለግንዛቤ ያህል ሊረዳ ይችላል፡፡)

በእርግጥ አሁን በያዝነው ዘመነ-መግቦት መጨረሻ ላይ፣ ጌታ በሚታይ ሁኔታና በአካል ስልሚገለጥበት ሁኔታ የሚናገሩት የቅዱሳት መጻሕፍት ምንባባት፣ ስለ እርሱ ሁሉን አዋቂነትና በአንድ ጊዜ በሁሉም ስፍራ መገኘት ስለሚችልበት መለኮታዊ ባሕርያቱ ከሚናገሩት ምንባባት /ለምሳሌ ማቴ18፡20 እና ማቴ28፡20/፣ ተለይተው መታየት ያለባቸው መሆኑ ግልጥ ነው፡፡ በዚህም ሁኔታ ደግሞ እስከ ዓለም -ዘመን- መጨረሻ ድረስ እርሱ ከእኛ ጋር መሆኑ የተባረከ እውነት ነው፡፡

ነገር ግን አሁን «ሰው የሆነው ክርሰቶስ ኢየሱስ» በአካል የሚገኘው በእግዚአብሔር ቀኝ ነው ፡፡

  • መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ ወደ ሰማይ ትኲር ብሎ ሲመለከት የእግዚአብሔርን ክብር ኢየሱስንም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየና፡- እነሆ ሰማያት ተከፍተው የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ አለ፡፡ ሐዋ7፡55፣56፡፡
  • ... ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፡፡ ዕብ1፡3፡፡
  • እንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ፣ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ፡፡ ቈላ3፡1፡፡

ይህን ሁኔታ በሚከተለው ምሳሌ ለማብራራት ይቻላል፤ በፍራንኮ-ፕሩሺያ /በፈረሳይና ጀርመን/ ጦርነት ወቅት ቮነ ሞልትኬ የተባለው ታዋቂው የጀርመን ጦር አዛዥ፣ በአካልና በሚታይ ሁኔታ ምንም እንኳ በበርሊን ከተማ በነበረው ቢሮው ውስጥ የነበረ ቢሆንም፣ ነገር ግን በጥበቡና በክህሎቱ/በችሎታው እንዲሁም በቴሌግራም መስመሮች መረብ አማካኝነት በእያንዳንዱ የጦር ሜዳዎች ላይ በእርግጥ ይገኝ ነበረ፡፡ በኋላ ላይም፣ ጦር ሠራዊቱ ፓ¬ሪስ ከመድረሱ በፊት ቀድሞአቸው በመገኘት ከእነርሱ ጋር ተቀላቀለ፤ ከዚያን ጊዜ ጀምሮም በአካል እዛው ከእነሱ ጋር መሆን ጀመረ፡፡ እንደዚሁም ሁሉ፣ ጌታችንም በመለኮታዊ ማንነቱ/ባሕርያቱ አማካኝነት አሁንም ከቤተክርስቲያኑ ጋር በእርግጥ ያለ ቢሆንም፣ በዳግም ምጽአቱ ወቅት ግን በሚታይ ሁኔታና በአካል በምድር ላይ ይሆናል/ይገኛል፡፡

የሚከተሉትን ነጥቦች ልብ እንበል፡-

    የጌታን ምጽአት የሚመለከቱት ትንቢቶች በበዓለ ሃምሳ ቀን በሆነው የመንፈስ ቅዱስ መውረድ፣ እንዲሁም በኃይለኛ መነቃቃቶችና የጸሎት ጉባኤዎች ወቅት በሚሆነው የእርሱ መገለጥ፣ ፍጻሜን አላገኙም /አልተፈጸሙም/ ፡፡
    1. እንዲህ ዓይነቱ አተረጓጐም መንፈስ ቅዱስን፣ የኢየሱስ ሌላ መገለጫ ብቻ በማድረግ የሦስትነትን/የሥላሴን/ አስተምህሮ ያፋልሳል፡፡
    2. ክርስቶስ ስለ መንፈስ ቅዱስ መምጣት በሰጠው የተስፋ ቃል ውስጥ ስለ እርሱ «ሌላ አጽናኝ» /ዮሐ14፡16/ እያለ በተለይ ተናግሮአል፤ እንዲሁም በዮሐ16፡7 ውስጥ ክርስቶስ እንዲህ ይላል፣ «... እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ፡፡»
    3. የሐዋርያት ሥራን፣ የመልእክታትንና የራእይን መጻሕፍት በመንፈስ በመነዳት የጻፉት ጸሐፍያን ስለ ጌታ ምጽአት ከጰንጠቆስጤ /በዓለ ሃምሳ/ ቀን በኋላ ከአንድ መቶ ሃምሳ ጊዜ በላይ የጠቀሱ ሲሆን፣ በሁሉም ውስጥ የተገለጠው፣ ገና ወደፊት የሚከሠት መሆኑን በሚጠቁም ሁኔታ ነው፡፡
    4. ከክርስቶስ ዳግመኛ ምጽአት ጋር አብረው እንደሚፈጸሙ ከተተነበዩት ክሥተቶች መካከል አንዳቸውም በበዓለ ሃምሳ ወቅት አልተከሠቱም፡፡ እነዚህም፡- ያንቀላፉት ቅዱሳን ትንሣኤ /1ቆሮ15፡22፣23፤ 1ተሰ4፡13-16/፤ «የተዋረደውን ሥጋችንን» «ክቡር ሥጋውን እንዲመስል» የሚለወጥበትና «የማይበሰብሰውን» የምንለብስበት በሕይወት የሚገኙ አማኞች «መለወጥ» እንዲሁም ጌታን በአየር ለመገናኘት የእነሱ መነጠቅ/1ቆሮ15፡51-53፤ 1ተሰ4፡17፤ ፊል3፡2ዐ፡21/፤ የሰው ልጅ በኃይልና በታላቅ ክብር ሆኖ በሚታይ ሁኔታ በመምጣቱ የተነሣ የሚሆነው የምድር ነገዶች ሁሉ ዋይታ/ማቴ24፡29፣30፤ ራእ1፡7/ ናቸው፡፡

    በጌታችን መመለስ ወቅት አብረው የሚከሠቱት ክሥተቶች እነዚህ ናቸው፤ እርሱም ሲመጣ እነዚህ ይኖራሉ፡፡ በበዓለ ሃምሳም ሆነ በሌላ የመንፈስ ቅዱስ መገለጥ ወቅት ከእነዚህ አንዳቸውም አልተከሠቱም፡፡

  1. የኃጢአተኛ መለወጥ/በጌታ ማመን/ የጌታ መምጣት /ምጽአት/ አይደለም፡፡ ይህንን ዓይነቱን ሐሳብ ለነዚህ በርካታ ለሆኑ ትንቢቶች ማብራሪያ አድርጐ በቁም ነገር ማቅረብ፣ በእግዚአብሔር ቃል አለመብሰል መሆኑን ማንም የሚረዳው ነው፡፡
  2. በቅዱሳት መጻሕፍት መሠረት እውነታው የዚህ ተገላቢጦሽ ነው፤ መለወጥ የኃጢአተኛ ወደ ክርስቶስ መምጣት እንጂ፣ የክርስቶስ ወደ ኃጢአተኛ መምጣት አይደለም፡፡ ማቴ11፡28፤ ዮሐ5፡4ዐ፤ 7፡37፤ 6፡37፡፡የጌታን መመለስ ተከትለው ከሚከሠቱት ከላይ ከተዘረዘሩት መካከል ማንኛቸውም በኃጢአተኛ መለወጥ ወቅት አይፈጸሙም፡፡
  3. የጌታን መመለስ ተከትለው ከሚከሠቱት ከላይ ከተዘረዘሩት መካከል ማንኛቸውም በኃጢአተኛ መለወጥ ወቅት አይፈጸሙም፡፡
    1. የክርስቲያን መሞት፣ የክርስቶስ ምጽአት /መምጣት/ አይደለም፡፡
      1. ደቀመዛሙርቱ የጌታን ንግግር ከእነርሱ አንዱ እስከ እርሱ ምጽአት ድረስ በሕይወት ይኖራል እንደሚል አድርገው ሲረዱ፣ «ያ ደቀመዝሙር አይሞትም» የሚለው ነገር በእነርሱ መካከል ተስፋፋ፡፡ ዮሐ21፡22-24፡፡
      2. በመንፈስ በመነዳት ቅዱሳት መጻሕፍትን የጻፉት ጸሐፊያን ሁል ጊዜ ስለ አማኝ ሞት የሚናገሩት የእርሱ መለየት እንደሆነ አድርገው ነው፡፡ የክርስቲያን ሞት በአንድም ስፍራ እንኳ ከጌታ ምጽአት ጋር አልተያያዘም፡፡ ፊል1፡23፤ 2ጢሞ4፡6፤ 2ቆሮ5፡8ን ተመልከት፡፡ በመሞት ላይ የነበረው እስጢፋኖስ፣ ሰማያት ተከፍተው የሰውን ልጅ ያየው «በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ» እንጂ፣ እየመጣ ሳለ አልነበረም፡፡ ሐዋ7፡55፣56፡፡

      3. 3. የጌታን ምጽአት ተከትለው እንደሚከሠቱ ከተተነበዩት ክስተቶች መካከል ማናቸውም በክርስቲያን ሞት ወቅት ተፈጽመው አያውቁም፡፡
        1. የኢየሩሳሌም በሮማዎች መፍረስ /መውደም/፣ የክርስቶስ ዳግመኛ ምጽአት አልነበረም፡፡
        የኢየሩሳሌም በሮማዎች መፍረስ /መውደም/፣ የክርስቶስ ዳግመኛ ምጽአት አልነበረም፡፡
        1. 1. በማቴ24 እና በሉቃ21 ውስጥ ሦስት ክሥተቶች ተተንብየዋል፤ የቤተመቅደሱ መፍረስ፣ የጌታ መምጣት፤ የዓለም /የዘመን/ መጨረሻ፡፡ የአንዱ መፈጸም የሁሉም መፈጸም ተደርጐ እንዲቆጠር ያስደረገው፣ እነዚህን ፍጹም የተለያዩ የሆኑ ነገሮችን በማምታታትና በማቀያየጥ ነው፡፡
        2. 2. ሐዋርያው ዮሐንስ፣ የራእይ መጽሐፍን የጻፈው ከኢየሩሳሌም መፍረስ በኋላ ነው፤ ነገር ግን እዚያው ውስጥ ምጽአቱ ገና ወደፊት እንደሚሆን አድርጐ ነው የሚናገረው /ራእ1፡4፣7፤ 2፡25፤ 3፡11፤ 22፡7፤ 12፡2ዐ/፡፡ የመጨረሻው የመጽሐፍ ቅዱስ የተስፋ ቃል፣ «አዎን፣ በቶሎ እመጣለሁ» የሚለው ሲሆን፣ የመጨረሻው ጸሎት ደግሞ፣ «አሜን፣ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፣ ና» የሚል ነው፡፡
        3. 3. ጌታ ተመልሶ ሲመጣ እንደሚከሠቱ ከተተነበዩት ነገሮች መካከል ማናቸውም በኢየሩሳሌም መፍረስ ወቅት አልተፈጸሙም፡፡ የሚከተሉትን ተመልከት፤ 1ተሰ4፡14-17፤ ማቴ24፡29-31፤ ማቴ25፡31፣32 ወዘተ ...
          1. የክርስትና መስፋፋትና መሰራጨት ቀስ በቀስ የሚሆን ሲሆን፣ ቅዱሳት መጻሕፍት ስለጌታ መምጣት የሚናገሩት፣ ድንገተኛና ያልተጠበቀ እንደሆነ አድርገው ነው፡፡ የሚከተሉትን ተመልከት፤ ማቴ24፡27፣36-42፣44፣5ዐ፤ 2ጴጥ3፡1ዐ፤ ራእ3፡3፡፡
          የክርስትና መስፋፋት የክርስቶስ ዳግመኛ ምጽአት አይደለም፡፡
          1. 1. የክርስትና መሰራጨት «ሂደት» ነው፤ ባንጻሩ ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉም ስለጌታ መመለስ /ምጽአት/ ባለመለየት የሚናገሩት «ክሥተት» እንደሆነ ነው፡፡
          2. 2. የክርስትና መሰራጨት ለኃጢአተኞች መዳንን የሚያመጣ ሲሆን፣ የክርስቶስ ምጽአት ግን እንደሚያመጣ የተነገረው መዳንን ሳይሆን፣ ለማይታዘዙት፣ «ድንገተኛ ጥፋትን» ነው፡፡ 1ተሰ5፡2፣3፤ 2ተሰ1፡7-1ዐ፤ ማቴ25፡31-46፡፡
          እነዚህ አመለካከቶችና ንድፈ ሐሳቦች /ቲዮሪዎች/ ምንም እንኳ እጅግ ተስፋፍተው የሚገኙ ቢሆኑም፣ በማንኛው ት/ቤት ወይም የሃይማኖት ድርጅት - ድጵነጸመፀነቷተፀጸነ? ውስጥ ባሉ ታዋቂ የሥነ-መለኮት /የቲዬሎጂ/ ሊቅ መጻሕፍት ውስጥ አይገኙም፤ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ዕውቅና ባላቸው በማናቸውም የቅዱሳት መጻሕፍት አጥኚዎች ወይም ተንታኞች ተቀባይነት የላቸውም፡፡ እነዚህ ሁላቸውም የሚቀበሉት በአካልና በሚታይ መልኩ የሚሆንን የክርስቶስ ምጽአት ነው፡፡

          ይሁንና ዓለም በሙሉ በወንጌል ስብከት እስካልተቀየረችና፣ እንዲሁም ደግሞ ለሺህ ዓመት ለሚሆን የክርስቶስ መንፈሳዊ መንግሥት እስካልተገዛች ድረስ፣ ይህ የክርስቶስ ምጽአት ሊፈጸም አይችልም ሲባል አልፎ አልፎ ይሰማል፡፡ ይህ አመለካከት ሙሉ በሙሉ ስሕተት ነው፤ ምክንያቱም፣

          1. በክርስቶስ መመለስ ወቅት የሚኖረው የምድር ሁኔታ በሺህ ዓመቱ መንግሥት ውስጥ የሚኖረው ዓይነት በረከት ሳይሆን፣ ነገር ግን አሠቃቂ ክፋት መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ያስረዳል፡፡ ሉቃ17፡26-32 ያለውን ከዘፍ 6፡5-7 እና ዘፍ13፡13 ጋር ተመልከት፤ ሉቃ18፡8፤ ሉቃ21፣25-27፡፡
          2. መጽሐፍ ቅዱስ አሁን ስላለንበት ዘመነ-መግቦት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ስላለው አጠቃላይ ሁኔታ የሚገልጸው ሙሉ ለሙሉ የተለወጠች ዓለም እንደማትኖር በሚያሳይ መልኩ ነው፡፡ ማቴ13፡36-43፣47፣5ዐ፤ ማቴ25፡1-1ዐ፤ 1ጢሞ4፡1፡፤ 2ጢሞ3፡1-9፤ 4፡3፣4፤ 2ጴጥ3፡3፣4፤ ይሁዳ 17-19፡፡
          3. በዚህ ዘመነ-መግቦት ውስጥ ያለው የእግዚአብሔር ዓላማ ዓለምን በሙሉ መለወጥ ሳይሆን፣ ነገር ግን «ለስሙ የሚሆንን ወገን ከአሕዛብ ይወስድ ዘንድ» ነው፡፡ ከዚህ በኋላም እርሱ «ይመለሳል»፤ ከዚህም በኋላ /ከዚህ በፊት አይደለም/፣ ዓለም ትለወጣለች፡፡ እነዚህን ተመልከት፤ ሐዋ15፡14-17፤ ማቴ24፡14 /«ምስክር እንዲሆን»/፤ ሮሜ1፡5፣6፤ ሮሜ11፡14 /«አንዳንዱን»፣ «ሁሉንም» አይልም/፤ 1ቆሮ9፡22፤ ራእ5፡9 /«ከ ... ሁሉ»፣ እንጂ «ሁሉንም» አይልም/፡፡
          4. እስከ አንድ ሺህ ዓመት ድረስ እና ምናልባትም ከዚያም በላይ ሊፈጸም እንደማይችል የምናውቀውን ክሥተት፣ «መጠንቀቅ» እና «መጠበቅ» የማይቻል ነው፡፡


1. አይሁድ፣ አሕዛብ፣ እና የእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን

ዓቢይ ምንባብ፣ 1ቆሮ.10፡32

የመጽሐፍ ቅዱስ አንባቢ የሆነ አንድ ሰው፣ ከመጽሐፉ እኩሌታ በላይ ይዘቱ የሚመለከተው አንድን ሕዝብ - ማለት እስራኤላውያንን - መሆኑን ማስተዋል አይሣነውም፡፡ ደግሞም፣ ይኸው ሰው እነርሱ በእግዚአብሔር ዕቅድና ምክር ውስጥ በጣም ለየት ያለ ስፍራ እንዳላቸው ይገነዘባል፡፡ ከብዙኃኑ የሰው ዘር ተለይተው በያህዌ ቃል ኪዳን ውስጥ እንዲገቡ ተደርገዋል፣ እርሱም ለእነርሱ ብቻ የሆኑና ሌሎችን ሕዝቦች የማይመለከቱ ተስፋዎች ሰጥቷቸዋል፡፡ በብሉይ ኪዳን ትረካዎችና ትንቢቶች ውስጥ የተነገረው የአይሁድ ታሪክ ብቻ ነው፤ ሌሎች ሕዝቦች የተጠቀሱት ከእነርሱ ጋር ባላቸው የተያያዘ ነገር አንጻር ብቻ ነው፡፡ እንዲያውም እግዚአብሔር ከእስራኤል ጋር እንደ ሕዝብ ያደረጋቸው ግንኙነቶች ምድርን ባጠቃላይ የሚመለከቱ ይመስላል፡፡ በቀደመው ኪዳን ውስጥ፣ እነሱ ታማኝና ታዛዥ ቢሆኑ፣ ምድራዊ ታላቅነት፣ ባለጠግነትና ኃይል እንደሚሆንላቸው ቃል ተገብቶላቸዋል፤ ባይታመኑና ታዛዥ ባይሆኑ ደግሞ፣ «ከምድር ዳር እሰከ ዳርቻዋ ድረስ ወዳሉ አሕዛብ ሁሉ» /ዘዳ.28፡64/ እንደሚበተኑ ተገልጾአል፡፡ እንደ ሥጋ ትውልድም ከእነርሱ ወገን እንደሚመጣ የተነገረው የመሢሑ ተስፋም ለ«ምድር ነገዶችም ሁሉ» በረከት የሚሆን ነው፡፡

የመጽሐፍ ቅዱሱ ተማሪ ምርመራውን ሲቀጥል፣ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በብዛት የተጠቀሰች ሌላ ለየት ያለች አካል ያገኛል፡- እርሷም የእግዚአብሔር ቤተ-ክርስቲያን ተብላ ተጠርታለች፡፡ ይህችም አካል ከእግዚአብሔር ጋር በዓይነቱ የተለየ ግንኙነት አላት፤ እንዲሁም እንደ እስራኤል ሁሉ፣ ለእርሷ ብቻ የሆኑ ተስፋዎችን ከእርሱ ተቀብላለች፡፡ ነገር ግን ከእስራኤል ጋር ያላቸው ተመሳሳይነት በዚሁ ብቻ ያበቃና፣ ጉልህ የሆነው ልዩነታቸው ይጀምራል፡፡ ይህች አካል ከአብርሃም የሥጋ ተወላጆች /ዝርያዎች/ ብቻ የተመሠረተች ከመሆን ይልቅ፣ እንዲያውም በእርሷ ውስጥ በአይሁድና በአሕዛብ መካከል ያለው ልዩነት አክትሟል፡፡ ግንኙነቱ በቃል ኪዳን ላይ ብቻ የተመሠረተ ሳይሆን፣ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አዳኝና ጌታ በመቀበል በሚገኘው በዳግም ልደት ላይ ነው፡፡ ቤተክርስቲያን፣ በመታዘዝ ምድራዊ ታላቅነትንና የሀብትን ብድራት ከማግኘት ይልቅ፣ ምግብና ልብስ ካገኘች ኑሮዬ ይበቃኛል እንድትልና፣ ስደትንና መጠላትን እንድትጠብቅ ትምህርት ተሰጥቹታል፤ እንዲሁም እስራኤል በልዩ ሁኔታ ከምድራዊና ጊዜያዊ ነገሮች ጋር እንደተያያዘች ሁሉ፣ ቤተክርስቲያንም እንዲሁ ከመንፈሳዊና ከሰማያዊ ነገሮች ጋር በልዩ ሁኔታ ተያይዛለች፡፡

በተጨማሪም፣ መጽሐፍ ቅዱስ እስራኤልም ሆነች ቤተክርስቲያን ከዘላለም ጀምሮ ሕልውና እንዳልነበራቸው ለአንባቢው ያሳየዋል፡፡ ሁለቱም በውል የሚታወቅ ጅማሬ አላቸው፡፡ አንባቢው መጽሐፍቅዱስን ሲያጠና የእስራኤል ሕልውና የሚጀምረው በአብርሃም መጠራት መሆኑን የሚረዳ ሲሆን፣ የቤተክርስቲያንን የልደት ቀን ሲያፈላልግ ደግሞ፣ ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ምድራዊ ሕይወት ወቅትም ሆነ ከዚያ በፊት እንዳልነበረች ይረዳል፤ ምክንያቱም ክርስቶስ ስለ ቤተክርስቲያኑ ገና ወደፊት እንደምትሆን አድርጐ ሲናገር ይገኛልና/ማቴ16፡18/፡- «በዚችም ዓለት ላይ ቤተክርስቲያኔን እሠራለሁ፡፡» ይላል፡፡

«ሠርቻለሁ፣» አሊያም «እየሠራሁ ነው፣» አይደለም የሚለው፤ ነገር ግን «እሠራለሁ፣» ነው፡፡

በመቀጠልም ከኤፌሶን 3፡5-10 ውስጥ ቤተክርስቲያን በብሉይ ኪዳን ትንቢት ውስጥ አንድም ጊዜ እንኳ እንዳልተጠቀሰች፣ ይልቁኑም በእነዚያ ዘመናት «በእግዚአብሔር ... የተሰወረች» እንደነበር ይገነዘባል፡፡ /አንዳንድ ሰዎች በተሳሳተ ሁኔታ አዳምና ሌሎቹ የብሉይ ኪዳን አበው በቤተክርስቲያን ውስጥ እንዳሉ ይናገራሉ፤ ይህ ግን ስሕተት ነው፡፡/ ከመጽሐፍ ቅዱስ አኳያም የቤተክርስቲያን ልደት በሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 2 ውስጥ /መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜ/፣ በምድር ላይ ያላትን ፍጻሜዋን ደግሞ በተሰሎንቄ መልእክት ምዕራፍ 4 ውስጥ /የመነጠቅ ጊዜን ይመለከታል/ ያገኘዋል፡፡

ደግሞም ተማሪው፣ ከመጽሐፍ ቅዱስ የሰው ዘር ክፍፍል አንጻር፣ በመጠኑ የተጠቀሰና በሁሉም መልክ ከእስራኤልም ሆነ ከቤተክርሰቲያን ልዩ የሆነ ሌላ ወገን ያገኛል - ይህም አሕዛብ ነው፡፡ የአይሁድ ፣የአሕዛብ እና የቤተክርስቲያን አንጻራዊ ስፍራ አጠር ባለ መልክ በሚከተሉት ምንባባት ውስጥ ይገኛል፡፡

  • አይሁድ - ሮሜ.9፡4-5፤ ዮሐ.4፡22፤ ሮሜ3፡1-2
  • አሕዛብ - ኤፌ.2፡11-12፤ ማር.7፡27-28
  • ቤተክርስቲያን ( ኤፌ5፡29-33፤ 1ጴጥ.2፡9

ስለ እስራኤልና ስለ ቤተክርስቲያን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተባለውን ሲያነጻጽር፣ በአጀማመር፣ በጥሪ፣ በተስፋ፣ በአምልኮ፣ በሥነ-ምግባር መመሪያ እና በወደፊት ግባቸው የተለያዩ ሆነው ያገኛቸዋል፡፡

በጥሪ

እስራኤል

  • እግዚአብሔር አብራምን አለው፡- ከአገርህ፣ ከዘመዶችም፣ ከአባትህም ቤት ተለይተህ እኔ ወደማሳይህ ምድር ውጣ፡፡ ዘፍ12፡1፡፡
  • አምላክህ እግዚአብሔር ወደ መልካም ምድር፣ ከሸለቆና ከኮረብታ የሚመነጩ የውሃ ጅረቶችና ፈሳሾች ምንጮችም ወዳሉበት ምድር ስንዴ ገብስም ወይንም በለስም ሮማንም ወይራም ማርም ወደ ሞሉባት ምድር፡-... ያገባሃል፡፡ ዘዳ.8፡7-9፡፡ እርሱም አለ፡- እኔ የአብርሃም ሎሌ ነኝ፡፡ እግዚአብሔርም ጌታዬን እጅግ ባረከው አገነነውም፤ በጎችንና፣ ላሞችን፣ ብርንም፣ ወርቅንም ወንዶች ባሪያዎችን፣ ሴቶች ባሪያዎችን፣ ግመሎችንም አህዮችንም ሰጠው፡፡ ዘፍ.24፡34-35፡፡
  • እርሱም አለ፡- እኔ የአብርሃም ሎሌ ነኝ፡፡ እግዚአብሔርም ጌታዬን እጅግ ባረከው አገነነውም፤ በጎችንና፣ ላሞችን፣ ብርንም፣ ወርቅንም ወንዶች ባሪያዎችን፣ ሴቶች ባሪያዎችን፣ ግመሎችንም አህዮችንም ሰጠው፡፡ ዘፍ.24፡34-35፡፡
  • እግዚአብሔር በላይህ የሚቆሙትን ጠላቶችህን በፊትህ የተመቱ ያደርጋቸዋል፤ በአንድ መንገድ ይመጡብሃል፣ በሰባትም መንገድ ከፊትህ ይሸሻሉ፡፡ ዘዳ.28፡7፡፡
  • እግዚአብሔር ራስ ያደርግሃል እንጂ ጅራት አያደርግህም፤ ሁል ጊዜም በላይ እንጂ በታች አትሆንም፡፡ ዘዳ.28፡13፡፡

ቤተክርስቲያን

  • ከሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች ....፡፡ ዕብ3፡1፡፡
  • እኛ አገራችን በሰማይ ነውና ...፡፡ ፊል3፡20፡፡
  • ኢየሱስም፡- ለቀበሮዎች ጉድጓድ ለሰማይም ወፎች መሳፈሪያ አላቸው ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም አለው፡፡ ማቴ8፡20፡፡
  • ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ እድፈትም ለሌለበት፡- ለማያልፍም ርስት... ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል፡፡ 1ጴጥ1፡4፡፡
  • እስከዚህ ሰዓት ድረስ እንራባለን፣ እንጠማለን፣ እንራቆታለን፣ እንጐሰማለን፣ እንከራተታለን ... ፡፡ 1ቆሮ4፡11፡፡ እግዚአብሔር በእምነት ባለጠጎች እንዲሆኑ ለሚወዱትም ተስፋ ስለ እርሱ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድሆች አልመረጠምን? ያዕ.2፡5፡፡
  • ከምኩራባቸው ያወጡአችኋል፤ ከዚህ በላይ ደግሞ የሚገድላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እንደሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል፡፡ ዮሐ16፡2፡፡
  • እንግዲህ እንደዚህ ሕፃን ራሱን የሚያዋርድ ሁሉ በመንግሥተ ሰማያት የሚበልጥ እርሱ ነው፡፡ ማቴ18፡4፡፡

በእርግጥ እንደ እግዚአብሔር ሐሳብ የሚኖር አይሁድ በሞት ሲለይ ወደ ሰማይ/ገነት አይሄድም አልተባለም፡፡ ልዩነቱ፣ እግዚአብሔርን እየመሰሉ ማለትም እንደ እግዚአብሔር ሐሳብ መኖር ለአይሁድ የነበረው ብድራት፣ ምድራዊ እንጂ ሰማያዊ ሽልማት አለመሆኑ ላይ ነው፡፡ አሁን በያዝነው የጸጋ ዘመነ-መግቦት አይሁድም ሆኑ አሕዛብ የሚድኑት፣ ዳግመኛ በሚወለዱበት /ዮሐ.3፡3-16/ እና «ቤተ-ክርስቲያን» /ኤፌ.1፡22-23/ በምትሆን በዚያች «አንድ አካል» /1ቆሮ.12፡13/ ውስጥ በሚጨመሩበት፣ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ባለ እምነት ብቻ መሆኑ የሚያጠያይቅ አይደለም፡፡ በቤተክርስቲያን ውስጥ በአይሁድና በአሕዛብ መካከል ያለው ልዩነት ይጠፋል /1ቆሮ12፡13፣ ገላ3፡28፣ ኤፌ2፡14፣ ኤፌ2፡11/፡፡ «አስቀድሞ አሕዛብ የነበራችሁ»፣ /1ቆሮ.12፡2/ «አሕዛብ ሳላችሁ ... »፣ የሚሉት አባባሎች የሚያስረዱን በትውልዳቸው አሕዛብም ሆነ አይሁድ የነበሩ ሰዎች፣ ወደ ቤተክርሰቲያን ሲመጡ፣ በመካከላቸው ያለው ልዩነት ጠፍቶ ሁለቱም በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት የሆኑ ክርስቲያኖች ብቻ እንደሚሆኑ ነው፡፡

በእስራኤልና በቤተክርስቲያን መካከል ያለው ልዩነት፤ ለእያንዳንዳቸው በተሰጣቸው የሥነ-ምግባር መመሪያዎች ውስጥም በተጨማሪ ይታያል፡፡ የሚከተለውን አነጻጽር፡-

በሥነ ምግባር

እስራኤል

  • አምላክህ እግዚአብሔር ልትወርሳት ወደምትገባባት ምድር ባመጣህ ጊዜ ከፊትህም ብዙ አሕዛብን፣... በመታሃቸውም ጊዜ፣ ፈጽመህ አጥፋቸው ከእነርሱም ጋር ቃል-ኪዳን
  • አታድርግ አትማራቸውም፡፡ ዘዳ.7፡1-2፡፡
  • ዓይን በዓይን ጥርስ በጥርስ እጅ በእጅ እግር በእግር መቃጠል በመቃጠል ቁስል በቁስል ግርፋት በግርፋት ይከፈል፡፡ ዘጸ.21፡ 24-25፡፡ እንዲሁም፣ ዘዳ21፡18-21፡፡

ቤተክርስቲያን

  • ጠላቶቻችሁን ውደዱ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፣ ለሚጠሉአቸሁም መልካም አድርጉ ስለሚያሳድዷችሁም ጸልዩ፡፡ (ማቴ5፡44)
  • ሲሰድቡን እንመርቃለን፣ ሲያሳድዱን እንታገሣለን፣ ክፋ ሲናገሩን እንማልዳለን፡፡ 1ቆሮ 4፡12፡13፡፡
  • እኔ ግን እላችኋለሁ ክፋውን አትቃወሙ ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጭህን በጥፊ ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት፡፡ ማቴ5፡39፡፡ ሉቃ15፡20-23፡፡

በአምልኮ ሁኔታዎች ውስጥም ልዩነት እናያለን፡፡ እስራኤላውያን ማምለክ የሚችሉት በአንድ ስፍራ እና ከእግዚአብሔር ራቅ ብለው ብቻ ነበር፤ ወደ እርሱ የሚቀርቡትም በካህን አማካኝነት ብቻ ነበር /ማለትም፣ ሁሉም ሕዝበ እስራኤል ካህን ስላልነበር ወደ እግዚአብሔር መቅረብ የሚችሉት በተለዩ የካህናት ወገኖች አማካኝነት ብቻ ነበር/፡፡ ቤተክርስቲያን ግን ሁለት ወይም ሦስት በሚሰበሰቡት በማንኛውም ስፍራ ማምለክ ትችላለች፤ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን የመግባት ድፍረት አላት፤ እንዲሁም ሁሉም አባላት /አማኞች/ ካህናት ናቸው፡፡

ዘሌ.17፡8-9ን
እነዚህን አነጻጻር፡-
ከማቴ.18፡20/ ጋር
ሉቃ.1፡10ንከዕብ.10፡19-20 ጋር
ዘኁ.3፡10ን ከ1ጴጥ.2፡5 ጋር

በተስፋ

የእስራኤልና የቤተክርስቲያንን የወደፊት ሁኔታዎች አስመልክቶ በተነገሩ ትንበያዎች /ትንቢቶች/ ውስጥም ያለው ልዩነት አስደናቂ ነው፡፡ ቤተክርስቲያን ሙሉ በሙሉ ከምድር ወደ ሰማይ የምትወሰድ ሲሆን፣ ወደ ቀድሞ ስፍራዋ የምትመለሰው እስራኤል ግን ገና እጅግ ታላቅ ምድራዊ ባለጠግነትና ኃይል ይጠብቃታል፡፡ ይህን ተመልከት፤

ቤተክርስቲያን

  • በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፣ እንዲህስ ባይሆን ባልኊችሁ ነበር ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኊለሁ፡፡ ዮሐ.14፡2-3፡፡
  • በጌታ ቃል የምንላችሁ ይህ ነውና እኛ ሕያዋን ሆነን ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር ያንቀላፉትን አንቀድምም፤ ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ ከዚያም በኊላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን፡፡ 1ተሰ4፡15-17፡፡
  • እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፣ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስን እንጠባበቃለን፤ እርሱም ሁሉን እንኳ ለራሱ ሊያስገዛ እንደሚችልበት አሠራር ክቡር ሥጋውን እንዲመስል የተዋረደውን ሥጋችንን ይለውጣል፡፡ ፊል3፡20-21፡፡
  • ወዳጆች ሆይ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፡- ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም፡፡ ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን፡፡ 1ዮሐ3፡2፡፡
  • የበጉ ሠርግ ስለደረሰ ሚስቱም ራስዋን ስላዘጋጀች ደስ ይበለን ሐሴትም እናድርግ ክብርንም ለእርሱ እናቅርብ ... ያጌጠና የተጣራ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ እንድትጐናጸፍ ተሰጥቶአታል፡፡ ቀጭኑ የተልባ እግር የቅዱሳን ጽድቅ ሥራ ነውና፡፡ እርሱም ወደ በጉ ሠርግ እራት የተጠሩ ብፁዓን ናቸው ብለህ ጻፍ አለኝ፡፡ ራእ19፡7-9፡፡
  • በፊተኛው ትንሣኤ ዕድል ያለው ብፁዕና ቅዱስ ነው፤ ሁለተኛው ሞት በእነርሱ ላይ ሥልጣን የለውም፡፡ ዳሩ ግን የእግዚአብሔርና የክርስቶስ ካህናት ይሆናሉ፤ ከእርሱም ጋር ይህን ሺህ ዓመት ይነግሣሉ፡፡ ራእ20፡6፡፡

እስራኤል

  • እነሆም ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፤ ስሙንም ኢየሱስ ትይዋለሽ፡፡ እርሱም ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፤ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘላለም ይነግሣል፤ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም፡፡ ሉቃ1፡31-33፡፡
    /ለማርያም ከተሰጡት ከእነዚህ ሰባት ተስፋዎች መካከል፣ የመጀመሪያዎቹ አምስቱ ቃል በቃል ተፈጽመዋል፡፡ ታዲያ ቀሪዎቹ ሁለቱ አይፈጸሙም ልንል የምንችለው፣ የትኛው የአተረጓጐም ሕግ በሚሰጠን ሥልጣን ነው᐀/
  • እግዚአብሔር ለስሙ የሚሆንን ወገን ከአሕዛብ ይወስድ ዘንድ አስቀድሞ እንዴት እንደጐበኘ ስምዖን ተርኮአል፡፡ ከዚህም ጋር የነቢያት ቃል ይስማማል እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፡ ከዚህ በኊላ ... እመለሳለሁ የወደቀችውንም የዳዊትን ድንኳን እንደገና እሠራታለሁ እንደገናም አቆማታለሁ ...» የሐዋ.ሥ.15፡14-16፡፡
  • እንግዲህ፡- እግዚአብሔር ሕዝቡን ጣላቸውን᐀ እላለሁ አይደለም እኔ ደግሞ እስራኤላዊና ከአብርሃም ዘር ከብንያምም ወገን ነኝና ... እንግዲህ፡- የተሰናከሉ እስኪወድቁ ድረስ ነውን᐀ እላለሁ፡፡ አይደለም ነገር ግን እነርሱን ያስቀናቸው ዘንድ በእነርሱ በደል መዳን ለአሕዛብ ሆነ፡፡ ... አንተ በፍጥረቱ የበረሀ ከነበረ ወይራ ተቈርጠህ እንደ ፍጥረትህ ሳትሆን በመልካም ወይራ ከገባህ ይልቁኑስ እነዚያ በፍጥረታቸው ያሉት ቅርንጫፎች በራሳቸው ወይራ እንዴት አይገቡም᐀ ወንድሞች ሆይ ልባሞች የሆናችሁ እንዳይመስላችሁ ይህን ምሥጢር ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ፤ የአሕዛብ ሙላት እስኪገባ ድረስ ድንዛዜ በእስራኤል በአንዳንድ በኩል ሆነባቸው፤ እንደዚሁም እስራኤል ሁሉ ይድናል፤ እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ፡- መድኃኒት ከጽዮን ይወጣል ከያዕቆብም ኃጢአተኛነትን ያስወግዳል፡፡ ሮሜ11፡1፣ 11፣ 24-26፡፡
  • > >በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል የቀረውን የሕዝቡን ቅሬታ ... ይመልስ ዘንድ ጌታ እንደገና እጁን ይገልጣል፡፡ ለአሕዛብም ምልክትን ያቆማል ከእስራኤልም የተጣሉትን ይሰበስባል ከይሁዳም የተበተኑትን ከአራቱም የምድር ማዕዘኖች ያከማቻል፡፡ ኢሳ11፡11፣12፡፡
  • > >እግዚአብሔርም ያዕቆብን ይምረዋል እስራኤልንም ደግሞ ይመርጠዋል በአገራቸውም ያኖራቸዋል መጻተኛም ከእርሱ ጋር ይተባበራል ከያዕቆብም ቤት ጋር ይጣበቃል፡፡ ኢሳ14፡1፡፡
  • ስለዚህ እነሆ፡- የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ ምድር ያወጣ ሕያው እግዚአብሔርን ዳግመኛ የማይባልበት ዘመን ይመጣል ይላል እግዚአብሔር፤ ነገር ግን፡- የእስራኤልን ልጆች ከሰሜን ምድር ካሳደዳቸውም ምድር ሁሉ ያወጣ ሕያው እግዚአብሔርን ይባላል፤ እኔም ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኊት ምድራቸው እመልሳቸዋለሁ፡፡ ኤር16፡14-15፡፡
  • እነሆ ለዳዊት ጻድቅ ቊጥቋጥ የማስነሣለት ዘመን ይመጣል ይላል እግዚአብሔር እርሱም እንደ ንጉሥ ይነግሣል ይከናወንለታልም በምድርም ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል፡፡ በዘመኑም ይሁዳ ይድናል እስራኤልም ተዘልሎ ይቀመጣል የሚጠራበትም ስም፡- እግዚአብሔር ጽድቃችን ተብሎ ነው፡፡ ኤር.23፡5-6፡፡
  • እነሆ በቊጣዬ በመዓቴ በታላቅም መቅሠፍቴ እነርሱን ካሳደድሁባት አገር ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ ወደዚህም ስፍራ እመልሳቸዋለሁ ተዘልለውም እንዲኖሩ አደርጋለሁ፣ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ፡፡ ኤር32፡37-38፡፡
  • የጽዮን ልጅ ሆይ ዘምሪ እስራኤል ሆይ እልል በይ፣ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ በፍጹም ልብሽ ሐሤት አድርጊ ደስም ይበልሽ፡፡ እግዚአብሔር ፍርድሽን አስወግዶአል ጠላትሽንም ጥሎአል የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር በመካከልሽ አለ ከእንግዲህ ወዲህ ክፉ ነገርን አታዪም ሶፎ3፡14-15፡፡

የቤተክርስቲያንን እድገት ከማጓተት፣ ተልዕኮዋን ከመበረዝ እንዲሁም መንፈሳዊ ነገሯን ከማጥፋት አንጻር፣ ሌሎች ምክንያቶች በአንድ ላይ ተደምረው ካደረሱባት ጥፋት ይልቅ፣ ለእርስዋ አይሁዳዊ ጠባይ መስጠቱ /የእስራኤል ምትክ አድርጎ መውሰዱ/ የከፋ ጉዳት አድርሶባታል፡፡ አሁን «ቤተ ክርስቲያን» ነን እያሉ እራሳቸውን የሚጠሩት የተለያዩ አካላት፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእውነተኛዋ ቤተክርስቲያን የተሰጣትን የመለየት /Separation/፣ የመሰደድ፣ በዓለም የመጠላት፣ የድህነት እና አፀፋን ያለመመለስ መንገድ ፈጽሞ እየተከተሉ አይደለም፤ ነገር ግን እነርሱ፣ ለአይሁድ ማለትም ለእስራኤል የተሰጡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን ለቤተክርስቲያን እንደተሰጡ አድርገው በመውሰድ፣ ዓላማቸውን ወደ ዓለም ሥልጣኔ፣ ሀብት /ንዋይ/ ወደ ማጋበስ፣ ሥርዓቶችን ወደ መደንገግ፣ ትላልቅ «የአብያተ ክርስቲያናት» ሕንጻዎችን ወደ መገንባት፣ የእግዚአብሔርን ቡራኬ በአገሮች መካከል በሚከሰቱ የጦርነት ግጭቶች ላይ ወደ መጋበዝ፣ እንዲሁም በእግዚአብሔር ፊት እኩል የሆኑ ወንድማማቾችን «ካህን» እና «ምዕመን» ብሎ ወደ መለያየት ዝቅ ለማድረግ እየተጠቀሙባቸው ይገኛሉ፡፡

5. አምስቱ የፍርድ ዓይነቶች

በበርካታ ሃይማኖታዊ ሥነ-ጽሑፎች ውስጥ በብዛት የሚታየው፣ «አጠቃላይ ፍርድ» የሚባለው አባባልም ሆነ በአባባሉ ውስጥ ሊተላለፍ የሚፈለገው ሐሳብ፣ በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ አይገኙም፡፡

ዶ/ር ፔንትኮስት የተባሉ ሰው በአንድ ወቅት እንዲህ ብለዋል፡ «ፍርድ፣ የሰው ልጆች በሙሉ ማለትም፣ ቅዱሳን እና ኃጢአተኞች፣ አይሁድ እና አሕዛብ፣ ሕያዋንና ሙታን፣ በዓለም መጨረሻ ላይ፣ «በታላቁ ነጭ ዙፋን» ፊት፣ በአንድ ላይ ተሰብስበው የሚፈጸም አንድ ታላቅ ክስተት ነው፣ ብሎ የክርስቲያኑን ዓለም እንዲያስብ ያደረገው፣ የተሳሳተ ልማድ ነው፡፡ ይህም ከቅዱሳት መጻሕፍት አስተምሮዎች በእጅጉ የራቀ ነው፡፡»

መጽሐፍ ቅዱስ አምስት ዓይነት ፍርዶች እንዳሉ ይናገራል፤ እነርሱም ደግሞ አንዱ ከሌላው በአራት ዓይነት ገፅታዎች ይለያያሉ፡-

  1. በተፈራጆቹ /ሊፈረድባቸው ባሉት ሰዎች/ ማንነት
  2. ፍርዱ በሚሰጥበት ጊዜ
  3. ፍርዱ በሚያስከትለው ወይም በፍርዱ በሚሰጥበት ቦታ
  4. ሚያሰገኘው ውጤት፡፡

ፍርዶቹም የሚከተሉት ናቸው፤፡

ማንነት ጊዜ ቦታ ዉጤት
በአማኞች ኃጢአት ላይ የተደረገ ፍርድ በ0030 ዓም፥ በቀራንዮ ለክርስቶስ ሞት፣ ለአማኙ ደግሞ ጽድቅ/የዘላለም ሕይወት/
  • ኢየሱስንም ይዘው ወሰዱት፤ መስቀልንም ተሸክሞ በዕብራይስጥ ጎልጎታ ወደተባለው የራስ ቅል ስፍራ ወደሚሉት ወጣ፡፡ በዚያም ሰቀሉት፤ ዮሐ19፡17፣18፡፡በቀራንዮ መስቀል ላይ፤
  • እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ 1ጴጥ2፡24፡፡
  • ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤ 1ጴጥ3፡18፡፡
  • በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን፤ ገላ3፡13፡፡
  • እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው፡፡ 2ቆሮ5፡21፡፡
  •  አሁን ግን በዓለም ፍጻሜ ራሱን በመሠዋት ኃጢአትን ሊሽር አንድ ጊዜ ተገልጦአል፡፡ ዕብ9፡26፡፡
  • ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ ... ዕብ1፡3፡፡
  • እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኲነኔ የለባቸውም፡፡ ሮሜ8፡1፡፡
  • እውነት እውነት እላችኋለሁ፣ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፣ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም፡፡ ዮሐ5፡24፡፡
  • በአማኙ እኔነት - (Self) ላይ የሚደረግ ፍርድ፤
  • ጊዜ በማንኛውም ጊዜ
    ቦታ በማንኛውም ቦታ
    ውጤት ግሣጼ/ተግሣጽ/
  • አማኙ በአንዳች ምክንያት ኃጢአትን ቢሠራ በራሱ ላይ በመፍረድ በንስሐ ወደ እግዚአብሔር በመናዘዝ ይቅርታን ማግኘት ይችላል፤ ይህን ባያደርግ ግን እግዚአብሔር እነደራሱ አሠራርና ሉዓላዊ ፈቃድ መሠረት በሥጋው ላይና በዚህ ዓለም በሚሆን ነገር ሊቀጣውና ሊገሥፀው ይችላል፡፡
  • ራሳችንን ብንመረምር ግን ባልተፈረደብንም ነበር፤ ነገር ግን በተፈረደብን ጊዜ፣ ከዓለም ጋር እንዳንኰነን በጌታ እንገሠጻለን፡፡ 1ቆሮ11፡31፣32፡፡
  • እግዚአብሔር እንደ ልጆች ያደርግላችኋልና፤ አባቱ የማይቀጣው -የማይገሥጸው- ልጅ ማን ነው? ዕብ12፡7፡፡ የሚከተሉትንም ተመልከት፤ 1ጴጥ4፡17፤ 1ቆሮ5፡5፤ 2ሳሙ7፡14፣15፤ 2ሳሙ12፡13፣14፤ 1ጢሞ1፡2ዐ፡፡
  • በአማኞች ሥራ ላይ የሚደረግ ፍርድ፣
  • ጊዜቦታውጤት
    ክርስቶስ ተመልሶ ሲመጣ በሰማይ ለአማኙ «ደመወዙን(ሽልማቱን)» መቀበል ወይም «መጐዳት (መክሰር)» እርሱ ራሱ ግን ይድናል»፡፡

    ምንም እንኳ ክርስቶስ በገዛ ሥጋው ኃጢአታችንን በመስቀል ላይ የተሸከመ ቢሆንም፣ እንዲሁም ደግሞ እግዚአብሔር፣ እነርሱን /ማለትም ኃጢአቶቻችንን/ «ደግሜ አላስብም» /ዕብ1ዐ፡17/ በማለት ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን የገባ ቢሆንም፣ እያንዳንዱ ሥራ የግድ ወደ ፍርድ የመቅረቡ ሐሳብ እጅግ ልብ መባል የሚገባው ነው፡፡

  • ስለዚህ ደግሞ ብናድር ወይም ተለይተን ብንሆን እርሱን ደስ የምናሰኝ ልንሆን እንቀናለን፡፡ መልካም ቢሆን ወይም ክፉ እንዳደረገ፣ እያንዳንዱ በሥጋው የተሠራውን በብድራት ይቀበል ዘንድ ሁላችን በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት ልንገለጥ ይገባናልና፡፡ 2ቆሮ5፡9፣1ዐ፡፡
  • አንተም በወንድምህ ላይ ስለ ምን ትፈርዳለህ? ወይስ አንተ ደግሞ ወንድምህን ስለ ምን ትንቃለህ? ሁላችን በክርስቶስ ፍርድ ወንበር ፊት እንቆማለንና፡፡ ሮሜ14፡1ዐ፡፡
  • እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ሁለቱም ምንባባት በአገባባቸው /በዓውደ ንባባቸው/ አማኞችን ብቻ የሚመለከቱ መሆናቸው ግልጽ ነው፡፡ በመጀመሪያው ምንባብ ውስጥ ሐዋርያው ስለ እኛ የጻፈው ከሁለቱ በአንደኛው ሁኔታ ውስጥ የምንገኝ መሆኑን ነው፡- በሕይወት ሆነን በሥጋችን ውስጥ መኖር፣ ወይም ደግሞ ከሥጋችን ተለይተን ከጌታ ጋር መሆን፡፡ እንደዚህ ዓይነቱን አባባል /ቋንቋ/ ደግሞ ለማያምኑ /ለኢ-አማንያን/ መጠቀም አይቻልም፡፡ በሁለቱም ስፍራዎች /ማለትም ከጌታ ጋር ወይም በሥጋችን/ ውስጥ ሆነን «እርሱን ደስ የምናሰኝ ልንሆን እንቀናለን -እርሱን ማስደስትን ዓላማችን እናደርጋለን- ...፣ ሁላችን በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት ልንገለጥ ይገባናልና» ወዘተ...፡፡ 2ቆሮ5፡8፣9፡፡

    በሁለተኛው ምንባብ ውስጥ ደግሞ «እኛ» እና «ወንድም...» የሚሉት ቃላት፣ ምንባቡ ለአማኞች ብቻ የተወሰነ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡ መንፈስ ቅዱስ የዳኑትንና ያልዳኑትን /የጠፉትን/ በፍጹም እንደዚህ አያቀያይጥም፡፡

    የሚከተለው ምንባብ በአማኞች ሥራ ላይ የሚደረገውን ፍርድ መሠረታዊ መርህ ይሰጠናል፤

  • ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠረት አይችልምና፣ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ማንም ግን በዚህ መሠረት ላይ በወርቅ ቢሆን በብርም በከበረ ድንጋይም በእንጨትም በሣርም ወይም በአገዳ ቢያንጽ፣ የእያንዳንዱ ሥራ ይገለጣል፤ በእሳት ስለሚገለጥ ያ ቀን ያሳያልና፣ የእያንዳንዱም ሥራ እንዴት መሆኑን እሳቱ ይፈትነዋል፡፡ ማንም በእርሱ ላይ ያነጸው ሥራ ቢጸናለት ደመወዙን -ሽልማቱን- ይቀበላል፤ የማንም ሥራ የተቃጠለበት ቢሆን ይጐዳበታል -ይከስራል-፣ እርሱ ራሱ ግን ይድናል ነገር ግን በእሳት እንደሚድን ይሆናል፡፡ 1ቆሮ3፡11-15፡፡
  • የሚከተሉት ምንባባት ደግሞ ይህ ፍርድ የሚፈጸምበትን ጊዜ ይገልጻሉ፤

  • የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣ ዘንድ አለውና፤ ያን ጊዜም ለሁሉ እንደ ሥራው ያስረክበዋል፡፡ ማቴ16፡27፡፡
  • የሚመልሱት ብድራት የላቸውምና ብፁዕ ትሆናለህ፤ በጻድቃን ትንሣዔ ይመለስልሃልና፡፡ ሉቃ14፡14፡፡ /1ቆሮ15፡22፣23ን ተመልከት/
  • ስለዚህ በጨለማ የተሰወረውን ደግሞ ወደ ብርሃን የሚያወጣ የልብንም ምክር የሚገልጥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ጊዜው ሳይደርስ አንዳች አትፍረዱ፤ በዚያን ጊዜም ለእያንዳንዱ ምስጋናው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይሆናል፡፡ 1ቆሮ4፡5፡፡
    /አይቀሬ ከሆነው የምስኪን ሥራችን መፈተን አንጻር ሲታይ፣ የዛኔ እኛን የሚያመሰግንበት አንዳች ነገር ያገኝ ዘንድ አሁን እኛን በትዕግሥቱ ፍቅር እየመራን መሆኑን ማወቅ እጅግ የሚያጽናና ነው፡፡/
  • እነሆ በቶሎ እመጣለሁ፣ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ፡፡ ራእ22፡12፡፡
  • ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፣ ይህንንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፡፡ 2ጢሞ 4፣8፡፡
  • ይህ ፍርድ ስለሚፈጸምበት ስፍራ ደግሞ 1ተሰ4፡16፣17ን ተመልከት፤ በተጨማሪም ማቴ25፡24-3ዐ ን አንብብ፡፡

  • በአሕዛብ /በሕይወት በሚገኙት አሕዛብ/ ላይ የሚደረግ ፍርድ፤ -ይህ ፍርድ የሚፈጸምባቸው ሰዎች፣ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛ ምጽአት ወቅት፣ ከታላቁ የሰባቱ ዓመት መከራ ተርፈው በምድር ላይ በሕይወት የሚገኙ፣ ነገር ግን በክርስቶስ በማመን የዘላለምን ሕይወት ያላገኙና ያልዳኑ ሰዎች ናቸው፡፡-
  • ጊዜ በክርስቶስ የክብር መገለጥ ወቅት /ማቴ25፡31፣32፤ ማቴ13፡4ዐ፣41/
    ቦታ በኢዮሣፍጥ ሸለቆ /እስራኤል አገር ውስጥ የሚገኝ/ /ኢዩኤል3፡1፣2፣12-14/
    ውጤት የአንዳንዶች መዳን፣ እንዲሁም የሌሎች መጥፋት፡፡

    ፍርዱ የሚመረኮዝበት መሠረታዊ መርህ- ክርስቶስ «ወንድሞቼ» ብሎ ለሚጠራቸው የተደረገላቸው አያያዝ፡፡ ማቴ 25፡4ዐ፣45፤ ኢዩኤል3፡3፣6፣7፡፡ እነዚህ «ወንድሞቼ» የተባሉት፣ የቤተክርስቲያንን መወሰድ /መነጠቅ/ ተከትሎ በሚመጣውና በጌታችን የክብር መገለጥ ወቅት በሚያበቃው፣ «በታላቁ መከራ» ወቅት ኢየሱስን እንደ መሢሐቸው የሚቀበሉት የአይሁድ ቅሬታዎች ናቸው፣ ተብሎ ይታመናል፡፡ ማቴ.24፡21፣22፤ ራእ.7፡14፤ 2ተሰ.2፡3-9፡፡ የዚህ ማስረጃ በጣም ሰፊ ስለሆነ አሁን እዚህ መጥቀስ አይቻልም፡፡ ይሁንና እነዚህ ወንድሞቼ የተባሉት የዚህ ዘመነ - መግቦት አማኞች ሊሆኑ እንደማይችሉ ግልጥ ነው፤ ምክንያቱም ለአማኞች የሚያደርጉት የርኅራኄ ተግባር ለኢየሱስ ለራሱ የሚደረግ አገልግሎት መሆኑን የማያውቁ እንደዚህ በርካታ ቁጥር ያላቸው ክርስቲያኖች ማግኘት አይቻልምና፡፡

    ውጤት፤ ማቴ. 25፡46፡፡

    ይህ በዚያን ጊዜ በሕይወት በሚገኙ ሕዝቦች /ሰዎች/ ላይ የሚደረግ ፍርድ፣ አንዳንድ ጊዜ በራእ2ዐ፡11 ውስጥ ካለው «ከታላቁ የነጭ ዙፋን ፍርድ» ጋር ስለሚምታታ፣ ቀጥለው የተቀመጡትን በሁለቱ ትእይንቶች መካከል ያሉ ልዩነቶችን ማጤኑ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል፡፡

    የሕያዋን ሕዝቦች ፍርድ የታላቁ ነጭ ዙፋን ፍርድ
    ትንሣኤ የለም ትንሣኤ ይደረጋል /አለ/
    ሕያዋን ሕዝቦች ይፈረድባቸዋል «ሙታን» ይፈረድባቸዋል
    የሚፈጸመው በምድር ላይ ነው ሰማይና ምድር ይሸሻሉ
    መጻሕፍት አይከፈቱም «መጻሕፍትም ተከፈቱ»
    ሦስት ክፍሎች አሉ፤
    በጐች፣ፍየሎችና«ወንድሞች»
    አንድ ክፍል ብቻ፤
    «ሙታን»
    ጊዜው- ክርስቶስ ሲገለጥ /ሲመለስ/ አንድ ሺህ ዓመታት ያህል ከነገሠ በኋላ

    በዚህ ፍርድ ጊዜ ቅዱሳን ከክርስቶስ ጋር ይተባበራሉ፤ በመሆኑም ፍርዱ በእነርሱ ላይ የሚፈጸም ሊሆን አይችልም፡፡ 1ቆሮ6፣2ን ከዳን7፡22 እና ይሁዳ14፣15 ጋር ተመልከት፤ ፡፡

    በሕያዋን ሕዝቦች ላይ የሚደረገው ፍርድ፣ ከታላቁ ነጭ ዙፋን ፍርድ ጋር የሚጋራው አንድ ነገር ብቻ ነው - ፈራጁ፡፡

  • ባልዳኑ ሙታን ላይ የሚደረግ ፍርድ፣
  • ጊዜ ከሺህ ዓመቱ መንግሥት በኋላ በተቀጠረ አንድ ቀን፤ ሐዋ17፡31፤ ራእ2ዐ፡5፡7፡፡
    ቦታ በታላቁ ነጭ ዙፋን ፊት፡፡ ራእ2ዐ፡11፡፡
    ውጤት ራእ2ዐ፡15፡፡

    አንዳንዶች እንደ ሐዋ17፡31 እና ሮሜ 2፡16 ባሉ ምንባቦች ውስጥ በሚገኘው «ቀን» በሚለው ቃል ሊቸገሩ ወይም ግራ ሊጋቡ ይችላሉ፡፡ «ቀን» ማለት የተራዘመ የጊዜ ስፍር መሆኑ የተገለጸባቸውን የሚከተሉትን ምንባባት መመልከት ነገሩን ለመረዳት ቀላል ያደርገዋል፤ 2ጴጥ3፡8፤ 2ቆሮ6፡2፤ ዮሐ8፡56፡፡

    በዮሐ5፡25 ውስጥ ያለው «ሰዓት» እስከ አሁን ድረስ ከሁለት ሺህ ዓመታት በላይ አሳልፎአል፡፡

    ማስታወሻ፡- ቅዱሳት መጻሕፍት ስለ መላእክት ፍርድም ይናገራሉ፡፡ ምናልባትም በ1ቆሮ6፡3፤ ይሁዳ6፤ 2ጴጥ2፡4 እና በሉቃ22፡3ዐ ውስጥ የሚገኙት ፈራጆች የሚያመለክቱት በእስራኤል ንጉሥ ከመኖሩ በፊት እንደነበሩት ዓይነት አስተዳዳሪ ፈራጆች ሐጽደመፀነፀሰተረቷተፀቨጵ ቕፈፈፀቸጵሐ እንጂ፣ እንደ ፍርድ ቤት ዓይነት ፍትሕ ሰጪ አካላትን /ጅጭደፀቸፀቷለ/ አይደለም/ኢሳ.1፡26 ተመልከት/፡፡

    6. ሕግ እና ጸጋ

    በሕግ እና በጸጋ መካከል ያለው ልዩነት የእውነትን ቃል /ማለትም መጽሐፍ ቅዱስን/ በጣም ግልጥ በሆነ ሁኔታ በተለያዩ ባሕርያቱ ይከፍለዋል፡፡ በእርግጥም እነዚህ የተለያዩ መርሆዎች፣ ማለትም ሕግና ጸጋ፣ የሁለቱ እጅግ ጠቃሚ የሆኑ ዘመናተ-መግቦት /የአይሁድና የክርስቲያን/ መለያ ጠባያት ናቸው፡፡

    • ሕግ በሙሴ ተሰጥቶ ነበርና፤ ጸጋና እውነት ግን በኢየሱስ ክርስቶስ ሆነ፡፡ ዮሐ1፡17፡፡

    ንና መጽሐፍ ቅዱስ በየትኛውም ዘመነ-መግቦት እነዚህን ሁለት መርሆዎች እንደማይቀያይጣቸው ማስተዋሉ እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ ሕግ ሁልጊዜ በቦታውም ሆነ በሥራው ከጸጋ ሙሉ በሙሉ የተለየ ነው፡፡ ሕግ እግዚአብሔር ሰውን የሆነ ነገር እንዳያደርግ መከልከሉንና ሌላ ነገር ደግሞ እንዲያደርግ መጠየቁን የሚያሳይ ሲሆን፣ ጸጋ ደግሞ እግዚአብሔር ሰውን ሲለምንና ለሰው እንዲሁ ማለትም በነጻ ሲሰጥ የሚያሳይ ነው፡፡ ሕግ የየኲነኔ /የፍርድ/ አገልግሎት ሲሆን፣ ጸጋ ደግሞ የይቅርታ አገልግሎት ነው፡፡ ሕግ የሚገድል ሲሆን፣ ጸጋ ደግሞ ሕይወት ይሰጣል፡፡ ሕግ በእግዚአብሔር ፊት አፍን ሁሉ ዝም ሲያሰኝ፣ ጸጋ ግን እግዚአብሔርን ያመሰግን ዘንደ አንደበትን ሁሉ ይከፍታል፡፡ ሕግ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ታላቅ የሆነ የበደል ርቀትን ሲያስቀምጥ፣ ጸጋ ደግሞ በደለኛ የሆነውን ሰው ወደ እግዚአብሔር እንዲቀርብ ያደርጋል፡፡ ሕግ «ዓይን ለዓይን፤ ጥርስ ለጥርስ» ሲል፣ ጸጋ ደግሞ «ክፉውን አትቃወሙ፣ ዳሩ ግን ቀኝ ጉንጭህን ለሚመታህ ሁሉ ሁለተኛውን ደግሞ አዙርለት፣» ይላል/ማቴ.5፡38-40/፡፡ ሕግ «ጠላትህን ጥላ» ሲል፣ ጸጋ ደግሞ «ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፣» ይላል/ማቴ43-46/፡፡ ሕግ ምንም ዓይነት መልእክተኛ /ምፀሰሰፀጸነቷረየ/ ኖሮት አያውቅም፤ ጸጋ ግን ለፍጥረት ሁሉ ይሰበካል፡፡ ሕግ ምርጥ የሚባለውን ሰው እንኳ የሚኰንን ሲሆን፣ ጸጋ ደግሞ እጅግ ክፉ የሚባለውን ሰው በነጻ ጻድቅ ያደርጋል /ሉቃ23፡43፤ ሮሜ5፡5፤ 1ጢሞ1፡15፤ 1ቆሮ6፡9-11/፡፡ ሕግ የፈተና ሥርዓት ሲሆን፣ ጸጋ ደግሞ የስጦታ ሥርዓት ነው፡፡ ሕግ አመንዝራይቱን የሚወግር ሲሆን ጸጋ ግን፣ «እኔም አልፈርድብሽም፣» የሚል ነው/ዮሐ.8፡1-11/፡፡ በሕግ ሥር፣ በጉ በእረኛው ፈንታ የሚሞት ሲሆን፣ በጸጋ ግን እረኛው በበጉ ፈንታ ይሞታል፡፡

    በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በሁሉም ስፍራ ሕግና ጸጋ የተቀመጡት በንጽጽር ነው፡፡ አሁን ባለንበት ዘመን እነርሱን በመደባለቅ የሚሰጠው ትምህርት፣ ሁለቱንም የሚያዛባ ነው፤ ምክንያቱም፣ የሕግን አስፈሪነት፣ እንዲሁም በጸጋ ውስጥ የተገለጠውን አርነት የሚሸፍን ወይም የሚያሳጣ ነውና፡፡

    በአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ «ሕግ» የሚለው ቃል የሚያመለክተው በሙሴ የተሰጠውን ሕግ መሆኑን አንባቢው ልብ ማለት አለበት /ከዚህ ልዩ የሆነ ሮሜ7፡23 ብቻ ነው/፤ ይሁንና አልፎ አልፎ አጠቃላዩን ሕግ ማለትም የሥነ-ምግባር ሕጎች /አሠርቱን ትዕዛዛት/ እና የሥነ-ሥርዓት ሕጐችንም በሚያመለክት ሁኔታ ተጠቅሷል፤ እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ ትእዛዛትን ብቻ ሌላ ጊዜ ደግሞ የሥርዓታቱን ሕግ ብቻ በሚመለከት ተጠቅሷል፡፡ ሮሜ6፡14፤ ገላ2፡16 እና 3፡2 ለመጀመሪያው ምሳሌ መሆን ይችላሉ፤ ሮሜ3፡19 እና 7፡7-12 ለሁለተኛው እንዲሁም ቈላ2፡14-17 ደግሞ ለሦስተኛው ምሳሌ ናቸው፡፡

    የጌታ ኢየሱስን ማንነትና ሥራ እንደ ካህንና መሥዋዕት የሚያሳዩት ውብ ጥላዎች፣ በሥነ-ሥርዓት ሕጉ ውስጥ ድንቅ በሆኑ ምሳሌዎች መመሰላቸው ሊታወስ ይገባል፤ ይህም ደግሞ መንፈሳዊ አእምሮ ላለው ሁሉ መደነቅንና ሐሴትን የሚፈጥር ነው፡፡ አንዳንድ የመዝሙረ ዳዊት አባባሎችን፣ «በፊደላት በድንጋዮች ላይ የተቀረጸ የሞት አገልግሎት...»/2ቆሮ3፡7/ በሚለው ሐሳብ ብቻ ከተገነዘብናቸው ወይም ከተረዳናቸው ለማብራራት አስቸጋሪ ይሆናሉ፤ ነገር ግን እነሱ ውብ የጸጋ ሥዕሎች የሆኑ ምሳሌዎች መሆናቸውን ስንረዳ፣ መልእክታቸው እንዲሁም የቅዱሳት መጻሕፍት የእርስበእርስ ስምምነት እና አለመፋለስ ግልጽ ይሆንልናል፡፡ ለምሳሌ እነዚህን ሦስት ጥቅሶች ተመልከት፡

    የሕግንና የጸጋን ትክክለኛ ግንኙነትን በተመለከተ ቤተክርስቲያንን ሦስት የስሕተት ትምህርቶች ሲያስቸግሩዋት ይገኛሉ፡፡

    • ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፣ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል፡፡ መዝ1፡2፡፡
    • ሕግህ ተድላዬ ናትና ቸርነትህ ትምጣልኝ፣ በሕይወትም ልኑር፡፡ መዝ119፡77፡፡
    • አቤቱ ሕግህን እንደምን እጅግ ወደድሁ፣ ቀኑን ሁሉ እርሱ ትዝታዬ ነው፡፡ መዝ119፡97፡፡

    የሕግንና የጸጋን ትክክለኛ ግንኙነትን በተመለከተ ቤተክርስቲያንን ሦስት የስሕተት ትምህርቶች ሲያስቸግሩዋት ይገኛሉ፡፡

    1. 1.ሕግ አልባነት (Antinomianism)፣ ወይም በአማኞች ሕይወት ውስጥ ምንም ዓይነት የሕግ መርህ ወይም ለሕግ መታዘዝ አያስፈልግም ማለት፤ ይህ አመለካከት ሰዎች የማይገባቸው ሆነው ሳሉ፣ በእግዚአብሔር ነጻ ጸጋ መዳንን /ደኅንነትን/ ለዘላለም ያገኙ በመሆኑ፣ ቅድስና ያለው ሕይወት/ከኃጢአት የራቀ ሕይወት/ እንዲኖሩ አይገደዱም፣ የሚል ነው፤ በሌላ አባበል ይህ የስሕተት አመለካከት፣ ሰው አንድ ጊዜ በጸጋ ከዳነ በኋላ፣ ምንም ዓይነት ኃጢአት ቢሠራ ችግር የለውም የሚል ነው፡፡
      • እግዚአብሔርን እንዲያውቁ በግልጥ ይናገራሉ፣ ዳሩ ግን የሚያስጸይፉና የማይታዘዙ ለበጎ ሥራም የማይበቁ ስለሆኑ፣ በሥራቸው ይክዱታል፡፡ ቲቶ1፡16፡፡
      • ከብዙ ጊዜ በፊት ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና ኃጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ በሴሰኝነት ይለውጣሉ፣ ንጉሣችንንና ጌታችንንም ብቻውን ያለውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ፡፡ይሁዳ 4፡፡
    2. 2. ሥርዓታዊነት (ceremonialism)
      የዚህ ኑፋቄ የመጀመሪያ /የቀድሞ/ ገፅታው፣ አማኞች የሌዋውያንን ሥርዓቶች በቀድሞ መልኩ መፈጸም አለባቸው የሚል ነበር፡፡
      • አንዳንዶችም ከይሁዳ ወረዱና እንደ ሙሴ ሥርዓት ካልተገረዛችሁ ትድኑ ዘንድ አትችሉም ብለው ወንድሞችን ያስተምሩ ነበር፡፡ ሐዋ15፡1፡፡

      የዚህ ስሕተት ትምህርት የአሁን ዘመን /ዘመናዊ/ ገፅታው ደግሞ፣ የክርስቲያን ሥርዓቶችን /ማለትም፣ ጥምቀትና የጌታ እራትን/ መፈጸም፣ መዳንን /ደኅንነትን/ ለማግኘት አስፈላጊ /ወሳቃ/ ነው የሚል ነው፡፡

    3. 3. ገላትያውያንነት (Galatianism)፣ ወይም ሕግንና ጸጋን ማደባለቅ፤ ይህ ትምህርት ደግሞ፣ ጽድቅ በከፊል በጸጋ፣ በከፊል ደግሞ በሕግ የሚገኝ ነው፣ ብሎ የሚያስተምር ነው፤ ወይም በሌላ አባባልም ይህ ትምህርት ጸጋ የሚሰጠው፣ ረዳት አልባ /ደካማ/ የሆነን ኃጢአተኛ፣ ሕግን ለመፈጸም እንዲችል ለማድርግ ነው ብሎ ያስተምራል፡፡
    4. ይህ ስሕተት ከሁሉም በይበልጥ ተስፋፍቶ የሚገኘ ሲሆን፣ ለእሱም ማስጠንቀቂያና በቂ መልስ የሚሆነው በገላትያ መልእክት ውስጥ የተሰጠው የእግዚአብሔር መልስ ነው፡፡

      • ይህን ብቻ ከእናንተ እንድማር እወዳለሁ፤ በሕግ ሥራ ወይም ከእምነት ጋር በሆነ መስማት መንፈስን ተቀበላችሁን? እንዲህን የማታስተውሉ ናችሁ? በመንፈስ ጀምራችሁ አሁን በሥጋ ትፈጸማላችሁን? -በመንፈስ ከጀመራችሁ በኋላ ፍጹማን /ፕጵረፈጵቸተ/ የምትሆኑት በሥጋ ነውን?- ገላ3፡2፣3፡፡
      • በክርስቶስ ጸጋ እናንተን ከጠራችሁ ከእርሱ ወደ ልዩ ወንጌል እንዲህ ፈጠናችሁ እንዴት እንዳለፋችሁ እደነቃለሁ፤ እርሱ ግን ሌላ ወንጌል አይደለም፤ የሚያናውጡአችሁ የክርስቶስንም ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ አንዳንዶች አሉ እንጂ፡፡ ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፣ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፣ የተረገመ ይሁን፡፡ ገላ1፡6-8፡፡

      ይህን ዓቢይ ርእሰ ጉዳይ በተመለከተ፣ ቀጥሎ የተዘረዘሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች ጠቃሚ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

    1. የሕግ ምንነት
      • ስለዚህ ሕጉ ቅዱስ ነው ትእዛዚቱም ቅድስትና ጻድቅት በጎም ናት፡፡ ሮሜ7፡12፡፡
      • ሕግ መንፈሳዊ እንደሆነ እናውቃለንና፤ እኔ ግን ከኃጢአት በታች ልሆን የተሸጠሁ የሥጋ ነኝ፡፡ ሮሜ7፡14፡፡
      • በውስጡ ሰውነቴ በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለኛል፡፡ ሮሜ 7፡22
      • ነገር ግን ሰው እንደሚገባ ቢሠራበት ሕግ መልካም እንደ ሆነ እናውቃለን፡፡ ገላ3፡12
    2. የሕግ ሕጋዊ አገልግሎት
      • እንግዲህ ምን እንላለን? ሕግ ኃጢአት ነውን? አይደለም ነገር ግን በሕግ ባይሆን ኃጢአትን ባላወቅሁም ነበር ሕጉ አትመኝ ባላለ ምኞትን ባላወቅሁም ነበርና፡፡ ሮሜ7፡7፡፡ ቊጥር 13ንም ተመልከት፡፡
      • ይህም የሕግን ሥራ በመሥራት ሥጋን የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት ስለማይጸድቅ ነው፣ ኃጢአት በሕግ ይታወቃልና፡፡ ሮሜ3፡2ዐ፡፡
      • እንግዲህ ሕግ ምንድነው? ተስፋው የተሰጠው ዘር እስኪመጣ ድረስ በመካከለኛ እጅ በመላእክት በኩል ስለ ሕግ መተላለፍ ተጨመረ፡፡ ገላ3፡19፡፡
      • አፍም ሁሉ ይዘጋ ዘንድ ዓለምም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ሕግ የሚናገረው ሁሉ ከሕግ በታች ላሉት እንዲናገር እናውቃለን፡፡ ሮሜ3፡19፡፡
      • ሕግ አንድ ቋንቋ ብቻ ነው ያለው - «የሚናገረው ሁሉ፡፡» እርሱ ስለ ፍርድ ብቻ የሚናገር ነው፡፡

      • ከሕግ ሥር የሆኑቱ ሁሉ ከእርግማን በታች ናቸውና በሕግ መጽሐፍ በተጻፉት ሁሉ ጸንቶ የማይኖር የማያደርግም ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና፡፡ ገላ3፡1ዐ፡፡
      • ሕግን ሁሉ የሚጠብቅ ነገር ግን በአንዱ የሚሰናከል ማንም ቢኖር በሁሉ በደለኛ ይሆናል፡፡ ያዕ.2፡1ዐ
      • ዳሩ ግን የእስራኤል ልጆች ስለዚያ ስለ ተሻገረው ስለ ፊቱ ክብር የሙሴን ፊት ትኲር ብለው መመልከት እስኪሳናቸው ድረስ ያ በፊደላት በድንጋዮች ላይ የተቀረጸ የሞት አገልግሎት በክብር ከሆነ የመንፈስ አገልግሎት እንዴት ይልቅ በክብር አይሆንም? 2ቆሮ3፡7፡፡
      • የኲነኔ አገልግሎት በክብር ከሆነ ይልቅ የጽድቅ አገልግሎት በክብር አብዝቶ ይበልጣል፡፡ 2ቆሮ3፡9
      • እኔ ድሮ ያለሕግ ሕያው ነበርሁ ትእዛዝ በመጣች ጊዜ ግን ኃጢአት ሕያው ሆነ እኔም ሞትሁ፤ ሮሜ7፡9፡፡
      • የሞት መውጊያ ኃጢአት ነው የኃጢአትም ኃይል ሕግ ነው፡፡ 1ቆሮ15፡56፡፡

    3. ሕግ ማድረግ የማይቻለው
      • ይህም የሕግን ሥራ በመሥራት ሥጋ የለበሰ ሁሉ በእርሱ ፊት ስለማይጸድቅ ነው ኃጢአት በሕግ ይታወቃልና፡፡ ሮሜ 3፡2ዐ፡፡
      • የእግዚአብሔርን ጸጋ አልጥልም ጽድቅስ በሕግ በኩል ከሆነ እንኪያስ ክርስቶስ በከንቱ ሞተ፡፡ ገላ2፡21፡፡
      • ነገር ግን ሰው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እንዲጸድቅ እንጂ በሕግ ሥራ እንዳይሆን አውቀን ሥጋን የለበሰ ሁሉ በሕግ ሥራ ስለማይጸድቅ እኛ ራሳችን በሕግ ሥራ ሳይሆን በክርስቶስ እምነት እንጸድቅ ዘንድ በክርስቶስ ኢየሱስ አምነናል፡፡ ገላ2፡16፡፡
      • ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎአልና ማንም በእግዚብሔር ፊት በሕግ እንዳይጸድቅ ግልጥ ነው፡፡ ገላ3፡11፡፡
      • ከሥጋ የተነሣ ስለ ደከመ ለሕግ ያልተቻለውን እግዚአብሔር የገዛ ልጁን በኃጢአተኛ ሥጋ ምሳሌ በኃጢአትም ምክንያት ልኮ አድርጓልና፡፡ ሮሜ8፡3፡፡
      • እንግዲህ ወንድሞች ሆይ በእርሱ በኩል የኃጢአት ስርየት እንዲነገርላችሁ በሙሴም ሕግ ትጸድቁበት ዘንድ ከማይቻላችሁ ሁሉ ያመነ ሁሉ በእርሱ እንዲጸድቅ በእናንተ ዘንድ የታወቀ ይሁን፡፡ ሐዋ13፡39፡፡
      • ሕጉ ምንም ፍጹም አላደረገምና ስለዚህም የምትደክም የማትጠቅምም ስለሆነች የቀደመች ትእዛዝ ተሽራለች ወደ እግዚአብሔርም የምንቀርብበት የሚሻል ተስፋ ገብቶአል፡፡ ዕብ7፡19፡፡
    4. አማኝ ከሕግ በታች አይደለም

      በሮሜ6 ውስጥ አማኞች ከክርስቶስ ጋር በሞቱ አንድ የመሆናቸው /ለዚህም ጥምቀት ምሳሌው ነው፣ ቁጥር 1-1ዐ/ አስተምህሮ ከተገለፀ በኋላ፣ ከቁጥር 11 ጀምሮ ደግሞ የአማኙን የሕይወት ምልልስ ሊገዙ የሚገባቸው መርሆዎች ማለትም የሕይወቱ መመሪያዎች ተገልጸዋል፡፡ የተቀሩት የአስራ ሁለቱ ቁጥሮች ርእሰ ጉዳይም ይህ ነው፤ ቁጥር 14 አማኙ ከኃጢአት ነጻ የወጣበትን ሳይሆን /ይህ በክርስቶስ ደም የተፈጸመ ነው/፣ ከኃጢአት አገዛዝ ወይም ጭቆና ወይም እስራት ነጻ የወጣበትን ታላቅ መርህ ይሰጠዋል፡፡

      «ኃጢአት አይገዛችሁምና፤ ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች አይደላችሁምና፡፡»

      ይህን ተከትሎ ክፉ የሆነው የሕግ አልባነት ትምህርት የቅድስና ሕይወት አያስፈልግም እንዳይል፣ መንፈስ ቅዱስ የሚከተለውን በመቀጠል አስፍሮአል፤

      «እንግዲህ ምን ይሁን? ከጸጋ በታች እንጂ ከሕግ በታች ስላይደለን ኃጢአትን እንሥራን? አይደለም» /ሮሜ6፡15/፡፡

      እያንዳንዱ የታደሰ /የተለወጠ/ ልብ ለዚህ አሜን- አሜን- እያለ መመለሱ የማያጠራጥር ነው፡፡

      ከዚያም ሮሜ7 ከሕግ አርነት የሚገኝበትን ሌላ መመሪያ ያሳየናል፡

      • እንዲሁ ወንድሞቼ ሆይ እናንተ ደግሞ በክርስቶስ ሥጋ ለሕግ ተገድላችኋል ለእግዚአብሔር ፍሬ ሊያፈራ በብልቶቻችን ይሠራ ነበርና አሁን ግን ለእርሱ ለታሰርንበት ስለ ሞትን ከሕግ ተፈትተናል፤ ስለዚህም በአዲሱ በመንፈስ ኑሮ እንገዛለን እንጂ በአሮጌው በፊደል ኑሮ አይደለም፡፡ ሮሜ7፡4-6፡፡ /ይህ የሥነ ሥርዓት ሕጐችን የማይመለከት መሆኑ ልብ ይባል፤ ቁጥር7ን ተመልከት/
      • እኔ ለእግዚአብሔር ሕያው ሆኜ እኖር ዘንድ በሕግ በኩል ለሕግ ሞቼ ነበርና፡፡ ገላ2፡19፡፡
      • እምነትም ሳይመጣ ሊገለጥ ላለው እምነት ተዘግተን ከሕግ በታች እንጠበቅ ነበር፡፡ እንደዚህ በእምነት እንጸድቅ ዘንድ ሕግ ወደ ክርስቶስ የሚያመጣ ሞግዚታችን ሆኖአል፤ እምነት ግን መጥቶአልና ከእንግዲህ ወዲህ ከሞግዚት በታች አይደለንም፡፡ ገላ3፡23-25፡፡
      • ነገር ግን ሰው እንደሚገባ ቢሠራበት ሕግ መልካም እንደ ሆነ እናውቃለን፤ ... የቡሩክ እግዚአብሔርንም ክብር እንደሚገልጥ ለእኔ አደራ እንደተሰጠኝ ወንጌል የሆነን ደኅና ትምህርት ለሚቃወም ለሌላ ነገር ሁሉ ሕግ እንደተሠራ እንጂ ለጻድቅ እንዳልተሠራ -እናውቃለን-...፡፡ 1ጢሞ1፡8፣9፡፡
    5. የአማኙ የሕይወት ሕግ ምንድነው?
      • በእርሱ እኖራለሁ የሚል እርሱ እንደተመላለሰ ራሱ ደግሞ ሊመላለስ ይገባዋል፡፡ 1ዮሐ2፡6፡፡
      • እርሱ ስለ እኛ ነፍሱን አሳልፎ ሰጥቶአልና በዚህ ፍቅርን አውቀናል እኛም ስለ ወንድሞቻችን ነፍሳችንን አሳልፈን እንድንሰጥ ይገባናል፡፡ 1ዮሐ3፡16፡፡
      • ወዳጆች ሆይ ነፍስን ከሚወጋ ሥጋዊ ምኞት ትርቁ ዘንድ እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ እለምናችኋለሁ፡፡ 1ጴጥ2፡11 /ቁጥር 12-23ተመልከት/፡፡
      • እንግዲህ በጌታ እስር የሆንሁ እኔ በተጠራችሁበት መጠራታችሁ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እለምናችኋለሁ፤ በትሕትና ሁሉና በየዋህነት በትዕግሥትም እርስ በእርሳችሁ በፍቅር ታገሡ፡፡ ኤፌ4፡1፣2፡፡
      • ቀድሞ በጨለማ ነበራችሁና አሁን ግን በጌታ ብርሃን ናችሁ፡፡ ኤፌ5፡8፡፡
      • እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጂ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንዴት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ፤ ቀኖc ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ፡፡ ኤፌ5፡15፣16፡፡
      • ነገር ግን እላለሁ በመንፈስ ተመላለሱ፣ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ፡፡ ገላ5፡16፡፡
      • እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና፡፡ ዮሐ13፡15፡፡
      • እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደ ጠበቅሁ በፍቅሩም እንደምኖር ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ፡፡ ዮሐ15፡1ዐ፡፡
      • እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በእርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ ትእዛዜ ይህች ናት፡፡ ዮሐ15፡12፡፡
      • ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትም የሚወደኝ እርሱ ነው የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል እኔም እወደዋለሁ፡፡ ዮሐ14፡21፡፡
      • ትእዛዙንም የምንጠብቅና በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን የምናደርግ ስለሆንን የምንለምነውን ሁሉ ከእርሱ እናገኛለን፡፡ 1ዮሐ3፡22፣23፡፡
      • ከዚያ ወራት በኋላ ከእነርሱ ጋር የምገባው ኪዳን ይህ ነው ይላል ጌታ በልባቸው ሕጌን አኖራለሁ በልቡናቸውም እጽፈዋለሁ፡፡ ዕብ1ዐ፡16፡፡

      የዚህ መርህ ድንቅ ማብራሪያ ወይም ምሳሌ በእናት ፍቅር ውስጥ ይታያል፤ የጋራ ብልፅግና ሀገሮች ማኅበር ወላጆች ለልጆቻቸው እንክብካቤ እንዲያደርጉና ሆነ ብለው ቸል በሚሉት ላይ ቅጣት እንዲደረግ ደንግጐአል፤ ነገር ግን ምድሪቱ ስለዚህ ሕግ መኖር ፈጽሞ ምንም ሳያውቁ ልጆቻቸውን በከፍተኛ ፍቅር በሚንከባከቡ እናቶች የተሞላች ናት፡፡ ምክንያቱም ሕጉ በልባቸው ውስጥ ስለሆነ ነው፡፡

      ከዚህ ጋር በተያያዘ፣ እግዚአብሔር የሕጉ ጽላቶች እንዲቀመጡ የወሰነበት ቦታ በምስክሩ ታቦት ውስጥ መሆኑን ማስታወስ ትምህርት የሚሰጥ ነው፡፡ የማስተስረያው ደም በተረጨበት በወርቃማው የስርየት መክደኛ ከእይታ የተሸፈኑ ቢሆንም፣ ከእነርሱ ጋር «መና ያለባት የወርቅ መሶብና የበቀለች የአሮን በትር» /አንደኛው የክርስቶስ ማለትም የምድረበዳው እንጀራችን ሌላው ደግሞ የትንሣኤ ምሳሌ ነው፤ ሁለቱም ስለ ጸጋ የሚናገሩ ናቸው/ አብረው አሉ፡፡ የእግዚአብሔር ዓይን የተጣሰውን ሕጉን ሊመለከት የሚችለው ጽድቁን ሙሉ በሙሉ በተበቀለውና ቊጣውን ባበረደው ደም ውስጥ ብቻ ነው፡፡ ዕብ9፡4፣5፡፡

      እነዚህን ቅዱስና ጻድቅ ነገር ግን ደግሞ፣ «ይገድላል» የተባለውን የፊደል ሕግ የያዙ ጽላቶች ከምሕረት መክደኛውና ከማስተስረያው ደም ለይቶ በመውሰድ፣ የክርስቲያን የሕይወት ሕግ እንዲሆኑ በክርስቲያን አብያተ-ክርስቲያናት ውስጥ ማስቀመጥ ለዘመናዊዎቹ የሕግ አምላኪዎች (Nomolaters) የተተወ ጉዳይ ነው፡፡

    6. ጸጋ ምንድነው?
      • ነገር ግን የመድኃኒታችን የእግዚአብሔር ቸርነትና ሰውን መውደድ (ተገለጠ) ...፡፡ ቲቶ3፡4፡፡
      • ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለጠግነት ያሳይ ዘንድ ከእርሱ ጋር አስነሣን፣ በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን፡፡ ኤፌ2፡7፡፡
    7. እግዚአብሔር በጸጋ ውስጥ ያለው ዓላማ ምንድነው?
      • ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም፡፡ ኤፌ2፡8፣9፡፡
      • ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና ይህም ጸጋ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን የተባረከውን ተስፋችንን እርሱ የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፡፡ ቲቶ2፡11-13፡፡
      • ያን መንፈስም በጸጋው ጸድቀን በዘላለም ሕይወት ተስፋ ወራሾች እንድንሆን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በእኛ ላይ አትርፎ አፈሰሰው፡፡ ቲቶ3፡7፡፡
      • በኢየሱስ ክርስቶስም በሆነው ቤዛነት በኩል እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ፡፡ ሮሜ3፡24፡፡
      • በእርሱም ደግሞ ወደ ቆምንበት ወደዚህ ጸጋ በእምነት መግባትን አግኝተናል በእግዚአብሔር ክብርም ተስፋ እንመካለን፡፡ ሮሜ5፡2፡፡
      • አሁንም ለእግዚአብሔርና ያንጻችሁ ዘንድ በቅዱሳንም ሁሉ መካከል ርስትን ይሰጣችሁ ዘንድ ለሚችል ለጸጋው ቃል አደራ ሰጥቻችኋለሁ፡፡ ሐዋ2ዐ፡32፡፡
      • በውድ ልጁም እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት፡፡ ኤፌ1፡6፣7፡፡
      • እንግዲህ ምሕረትን እንድንቀበል በሚያስፈልገንም ጊዜ የሚረዳንን ጸጋ እንድናገኝ ወደ ጸጋው ዙፋን በእምነት እንቅረብ፡፡ ዕብ4፡16፡፡ ምንኛ የተሟላና ሁሉን አቀፍ ነው- ጸጋ ያድናል፣ ያጸድቃል፣ ያንጻል፣ ተቀባይነትን ያስገኛል፣ ይቤዣል፣ ይቅር ይላል፣ ርስት ይሰጣል፣ አቋም ይሰጣል፣ ለምሕረትና ለእርዳታ በድፍረት የምንቀርብበትን ዙፋን ይሰጣል፣ እንዴት መኖር እንዳለብን ያስተምረናል፣ እንዲሁም የተባረከ ተስፋን ይሰጠናል፡፡
      • እነዚህ የተለያዩ መርሆዎች ሊደባለቁ የማይችሉ መሆኑን ማስተዋሉ ከእኛ ይጠበቃል፡፡

      • በጸጋ ከሆነ ግን ከሥራ መሆኑ ቀርቶአል ጸጋ ያለዚያ ጸጋ መሆኑ ቀርቶአል፡፡ ሮሜ11፡6፡፡
      • ለሚሠራ ደመወዝ እንደ ዕዳ ነው እንጂ እንደ ጸጋ አይቈጠርም ነገር ግን ለማይሠራ ኃጢአተኛውንም በሚያጸድቅ ለሚያምን ሰው እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቈጠርለታል፡፡ ሮሜ4፡4፣5፡፡ /ገላ3፡16-18፤ 4፡21-31 በተጨማሪ ተመልከት/
    በመጨረሻም፣
    • «ስለዚህ ወንድሞች ሆይ የጨዋይቱ ልጆች ነን እንጂ የባሪያይቱ አይደለንም፡፡ ገላ4፡31፡፡
    • ሊዳሰስ ወደሚችል ወደሚቃጠልም እሳት ወደ ጭጋግም ወደ ጨለማም ወደ ዐውሎ ነፋስም ወደ መለከት ድምፅም ወደ ቃሎችም ነገር አልደረሳችሁምና፣ ያንም ነገር የሰሙት ሌላ ቃል እንዳይጨመርባቸው ለመኑ እንስሳ እንኳ ተራራውን ቢነካ ተወግሮ ይሙት የምትለውን ትእዛዝ ሊታገሡ አልቻሉምና፤ ሙሴም እጅግ እፈራለሁ እንቀጠቀጥማለሁ እስኪል ድረስ የሚታየው እጅግ የሚያስፈራ ነበረ ነገር ግን ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ ደርሳችኋል፤ ወደሰማያዊቱም ኢየሩሳሌም፣ በደስታም ወደ ተሰበሰቡ ወደ አእላፋት መላእክት፣ በሰማያትም ወደ ተጻፉ ወደ በኲራት ማኅበር፣ የሁሉም ዳኛ ወደሚሆን ወደ እግዚአብሔር፣ ፍጹማን ወደሆኑት ወደ ጻድቃን መንፈሶች፣ የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፣ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል፡፡ ዕብ12፡18-24፡፡

    እናም ጥያቄው እግዚአብሔር ከሲና ተራራ ላይ ሆኖ የተናገረውን «የሥነ-ምግባር» እና «የሥነ ሥርዓት» ብሎ መክፈል ሳይሆን፣ እንዲያውም አማኙ ከነጭራሹ ወደ ተራራው የማይቀርብ/ የማይሄድ/ መሆኑ ነው፡፡

    ቡንያን የሚባል አዛውንት በአንድ ወቅት እንዲህ ብሎአል፡ «አሁን አማኙ ፍጹምና የተባረከ በሆነ ጽድቅ ተሸፍኖ በእምነት በኢየሱስ ክርስቶስ ውስጥ በመሆኑ፣ ነጐድጓዳዊው የሲና ሕግ አንዳች ትንሽ የሆነ ስሕተት እንኳን ሊያገኝበት አይችልም፡፡ ያለሕግ የሆነ የእግዚአብሔር ጽድቅ የሚባለው ይህ ነው፡፡»

    ምናልባት የአንድ ኢ-አማኒ ዓይኖች ይህን እያነበቡ ከሆነ፣ ያን ቅዱስና ጻድቅ የሆነ ሕግ በመተላለፍ ምክንያት የተፈረደበትን እውነተኛ ፍርድ እንዲቀበል በፍቅር እንመክረዋለን፤ ምክንያቱም «ልዩነት የለምና፤ ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጐድሎአቸዋል፤» ከዚህም በመቀጠል «የሚያምኑ ሁሉ ይጸድቁ ዘንድ... የሕግ ፍጻሜ...» /ሮሜ1ዐ፡4/ የሆነውን ክርስቶስን በልብ በማመንና በአፍ በመመስከር ፍጹምና ዘላለማዊ የሆነውን ደኅንነት እንዲያገኝ እናሳስበዋለን፡፡

    7.ሁለቱ የአማኝ ባሕርያት

    የሕያው እግዚአብሔር ዘላለማዊ ልጅ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አዳኙና ጌታው አድርጎ በማመን ዳግመኛ የተወለደ ማንኛውም ሰው፣ ሁለት ባሕርያት እንዳሉት ቅዱሳት መጻሕፍት ያስተምራሉ፤ አንደኛው በተፈጥሮ ልደት የተገኘና ፍጹም ተስፋ ቢስ በሆነ ሁኔታ መጥፎና የተበላሸ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ በአዲስ ልደት በኩል የተገኘ አዲስ ተፈጥሮ ሲሆን ሙሉ በሙሉም የእግዚአብሔር ባሕርይ በመሆኑ፣ ሙሉ በሙሉ መልካም የሆነ ነው፡፡

    አሮጌውን ወይም አዳማዊውን ባሕርይ በተመለከተ ያለውን የእግዚአብሔር አሳብ የሚከተሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባባት በደንብ ይገልጡልናል፡፡

    • እነሆ በዓመፃ ተፀነስሁ እናቴም በኃጢአት ወለደችኝ፡፡ መዝ51፡5፡፡
    • የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ እጅግም ክፉ ነው፤ ማንስ ያውቀዋል? ኤር17፡9፡፡
    • ጻድቅ የለም አንድ ስንኳ አስተዋይም የለም እግዚአብሔርንም የሚፈልግ የለም ሁሉ ተሳስተዋል በአንድነትም የማይጠቀሙ ሆነዋል፤ ቸርነት የሚያደርግ የለም አንድ ስንኳ የለም፡፡ ሮሜ3፡1ዐ-12፡፡

    እግዚአብሔር በቃሉ፣ «ዳግመኛ ያልተወለዱት ሰዎች በሙሉ ያልተገሩ ወይም፣ ችሎታ የሌላቸው፣ ወይም መልካም ባሕርይ የሌላቸው፣ ወይም ንፉጐች፣ ወይም ደግሞ ሃይማኖተኛ ያልሆኑ፣ ናቸው» እያለ አይደለም፤ ነገር ግን እርሱ የሚለው፣ «ሁሉም ጻድቅ/የጸደቁ/ አይደሉም፣ እግዚአብሔርን አያውቁም ወይም ደግሞ እግዚአብሔርን አይፈልጉም፣» ነው፡፡

    ከባድ ከሆኑት የእምነት ፈተናዎች መካከል አንዱ፣ በመለኮት ዘንድ ስለ ሰው ባሕርይ የሚሰጠውን ግምት መቀበል ነው፤ እያንዳንዱን የዕለት ተግባራት በመፈጸም ረገድ እጅግ ጠንቃቃ የሆኑ፣ ስለ ሰው ልጆች ችግሮች በጣም የሚያዝኑ፣ ስለ ሰብአዊ መብቶች መከበር በጣም የሚደክሙ፣ ጤናማ ሥነ-ምግባር ያላቸው ወዳጆቻችን፣ የእግዚአብሔርን መብቶች እጅግ የሚንቁ፣ በልጁም መሥዋዕት ምንም ያልተነኩ፣ መለኮታዊነቱንም ሊነገር በማይችል ስድብ የሚክዱ፣ እንዲሁም የእርሱን ቃል በንቀት የማይቀበሉ መሆናቸውን አምኖ መቀበል ከባድ ሊሆን ይችላል፡፡ ለሌላ ሰው ውሸትን መናገር እጅግ የሚዘገንናት አንዲት ጨዋ ሥነ-ምግባር ያላት ሴት፣ እርሱ ስለ ልጁ የሰጠውን ምስክርነት ያልተቀበለች ከሆነ፣ እግዚአብሔርን በየቀኑ ሐሰተኛ ታደርገዋለች፡፡ 1ዮሐ1፡1ዐ፤ 5፡1ዐ፡፡

    በዚህ ዘመን ደግሞ ብዙዎች ከአትሮኖስ /ፑልፒት/ ላይ የሚያስተጋቡአቸው «ምስጋናዎች»፣ ለብዙ ሺዎች ይህን ችግር አክብደውታል፡፡ ከጥፋት ውሃው አስቀድሞ በነበረው ጊዜ መስሎ በሚታየውና በእውነታው መካከል የነበረው ልዩነት አስገራሚ ነው፡፡

    •  በእነዚያ ወራት ኔፊሊም በምድር ላይ ነበሩ፤ ደግሞም ከዚያ በኋላ የእግዚአብሔር ልጆች የሰውን ሴቶች ልጆች ባገቡ ጊዜ ልጆችን ወለዱላቸው እነርሱም በድሮ ዘመን ስማቸው የታወቀ ኃያላን ሆኑ፡፡ ዘፍ6፡4፡፡ ዓለም እያደገችና እየተሻሻለች የሄደች ትመስል ነበር፤ እናም የእግዚአብሔር ወገን የሆኑት ከዓለማውያን ጋር ያደረጉት ቅዱስ ያልሆነ ጋብቻ ውጤትም የሰውን ተፈጥሮ ወደ በለጠ ከፍታ ያደረሰ ነበር፡፡ ነገር ግን ልክ ይህ ሲሆን፡-
    • እግዚአብሔርም የሰው ክፋት በምድር ላይ እንደ በዛ የልቡ አሳብ ምኞትም ሁልጊዜ ፈጽሞ ክፉ እንደ ሆነ አየ፡፡ ዘፍ.6፡5፡፡ በተጨማሪም ይህን ተመልከት፣
    • ከውስጥ ከሰው ልብ የሚወጣ ክፉ አሳብ፣ ዝሙት፣ መስረቅ፣ መግደል፣ ምንዝርነት፣ መጐምጀት፣ ክፋት፣ ተንኮል፣ መዳራት፣ ምቀኝነት፣ ስድብ፣ ትዕቢት፣ ስንፍና ናቸውና፤ ይህ ክፉው ሁሉ ከውስጥ ይወጣል ሰውንም ያረክሰዋል፡፡ ማር7፡21-23፡፡
    • ለፍጥረታዊ ሰው የእግዚአብሔር መንፈስ ነገር ሞኝነት ነውና አይቀበለውም በመንፈስም የሚመረመር ስለሆነ ሊያውቀው አይችልም፡፡ 1ቆሮ2፡14፡፡
    •  ስለ ሥጋ ማሰብ በእግዚአብሔር ዘንድ ጥል ነውና ለእግዚአብሔር ሕግ አይገዛምና መገዛትም ተስኖታል፤ በሥጋ ያሉትም እግዚአብሔርን ደስ ሊያሰኙት አይችሉም፡፡ ሮሜ8፡7፣8፡፡
    • በእነዚህም ልጆች መካከል እኛ ሁላችን ደግሞ የሥጋችንና የልቡናችንን ፈቃድ እያደረግን በሥጋችን ምኞት በፊት እንኖር ነበርን እንደ ሌሎቹም ደግሞ ከፍጥረታችን የቊጣ ልጆች ነበርን፡፡ ኤፌ2፡3፡፡

    በነዚህም፣ ያልተለወጠ /ያልዳነ/ ሰው ሦስት እጥፍ ችግር ያለበት ይመስላል፡፡ ተሰጥኦ ያለው፣ የሠለጠነ፣ ተወዳጅ፣ ቸር፣ ወይም ሃይማኖተኛ ሊሆን ይችላል፡፡ ዕዳውን የሚከፍል፣ ታታሪ፣ ጥሩ ባልና አባት የሚሆን ሊሆን ይችላል - ነገር ግን እርሱ ለእግዚአብሔር መታዘዝም ሆነ እግዚአብሔርን ማስደሰት እንዲሁም እርሱን ማወቅ /መረዳት/ አይችልም፡፡

    ባንጻሩ ደግሞ አማኝ የሆነ ሰው ያልተለወጠና ሊለወጥ የማይችል አሮጌ ባሕርይ እያለው፣ ነገር ግን «ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረ...» አዲስ ባሕርይ ተቀብሎአል፡፡

    ዳግመኛ ልደት መፈጠር እንጂ መታደስ አይደለም፤ አዲስን ነገር ማስገባት እንጂ አሮጌውን መለወጥ አይደለም፡፡ በተፈጥሮ ልደታችን የሰው ባሕርይ እንደተቀበልን ሁሉ፣ በዳግመኛ ልደትም መለኮታዊ የሆነ ባሕርይን እንቀበላለን፡፡

    የሚከተሉት ምንባባት የአዲሱን ሰው ምንጭና ጠባያት ይገልጡልናል፡፡

    • ኢየሱስም መልሶ እውነት እውነት እልሃለሁ ሰው ዳግመኛ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊያይ አይችልም አለው፡፡ ዮሐ3፡3፡፡
    • ለተቀበሉት ሁሉ ግን፣ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ እነርሱም ከእግዚአብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አልተወለዱም፡፡ ዮሐ1፡12፣13፡፡
    • በእምነት በኩል ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጆች ናችሁና፡፡ ገላ3፡26

    -እነዚህ ምንባባት፣ ከላዩ ሲታይ መልካም የሚመስለውንና በዘመናችንም እጅግ የተስፋፋውን፣ ነገር ግን በፍጹም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነውን፣ «የእግዚአብሔር ዓለም አቀፍ አባትነትና የሰው ልጆች ዓለም አቀፍ ወንድማማችነት» አስተሳሰብ ላይ ያላቸውን ተፅዕኖ እንገነዘባለን፡- ይህም አባባል የመጨረሻው ሐረግ ባዘለው ግማሽ እውነታ የተነሣ እጅግ አደገኛ ነው፡፡ የተወለዱ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች አይደሉም፣ ዳግመኛ የተወለዱ ብቻ እንጂ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ አዳም የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ቢነግረንም፣ ሴት የአዳም ልጅ እንደሆነም በጥንቃቄ ያስረዳናል፡፡- /ሉቃ3፡38/

    • ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ፡፡ ኤፌ4፡24፡፡
    • ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው አሮጌው ነገር አልፎአል እነሆ ሁሉም አዲስ ሆኗል፡፡ 2ቆሮ5፡17፡፡

    ይህም «አዲሱ ሰው» ከክርስቶስ ጋር የተያያዘ ነው፡፡

    • ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ እኔም ሕያው ሆኜ አልኖርም፣ ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል አሁንም በሥጋ የምኖርበት ኑሮ በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ ባለ እምነት የምኖረው ነው፡፡ ገላ2፡2ዐ፡፡
    • ለእነርሱም እግዚአብሔር በአሕዛብ ዘንድ ያለው የዚህ ምሥጢር ክብር ባለ ጠግነት ምን እንደ ሆነ ሊያስታውቅ ወደደ ምሥጢሩም የክብር ተስፋ ያለው ክርስቶስ በእናንተ ዘንድ መሆኑ ነው፡፡ ቈላ1፡27፡፡
    • ሞታችኋልና ሕይወታችሁም በእግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር ተሰውሮአልና ሕይወታችሁ የሆነ ክርስቶስ በሚገለጥበት በዚያን ጊዜ እናንተ ደግሞ ከእርሱ ጋር በክብር ትገለጣላችሁ፡፡ ቈላ3፡3፣4፡፡
    • ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ሞትም ጥቅም ነውና፡፡ ፊልጵ1፡21፡፡
    • ስለ ክፉ ምኞት በዓለም ካለው ጥፋት አምልጣችሁ ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች በተስፋ ቃል እንድትሆኑ በእነዚያ ክብርና በጎነት የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋን ሰጠን፡፡ 2ጴጥ1፡4፡፡
    • ክርስቶስ በእናንተ ውስጥ ቢሆን ሰውነታችሁ በኃጢአት ምክንያት የሞተ ነው፣ መንፈሳችሁ ግን በጽድቅ ምክንያት ሕያው ነው፡፡ ሮሜ8፡1ዐ፡፡
    • እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው፡፡ ልጁ ያለው ሕይወት አለው የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም፡፡ 1ዮሐ5፡11፣12፡፡

    ነገር ግን ይህ የክርስቶስ የራሱ የሆነው አዲሱ መለኮታዊ ባሕርይ በአማኙ ውስጥ ከአሮጌው ባሕርይ ጋር አንድ ላይ ነው የሚኖረው፡፡ «እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፣» ብሎ ማለት የተቻለው ያው ጳውሎስ ነው ደግሞ፣ «በእኔ ማለት በሥጋዬ በጎ ነገር እንዳይኖር አውቃለሁና» /ሮሜ7፡18/ የሚለው፡፡ ደግሞም እንዲህ ይላል «እንግዲያስ መልካሙን አደርግ ዘንድ ስወድ በእኔ ክፉ እንዲያድርብኝ ሕግን አገኛለሁ» /ሮሜ7፡21/፡፡ «ፍጹምና ቅን» ሰው የሆነው ኢዮብ ነው «ራሴን እንቃለሁ» የሚለው፡፡

    በእነዚህ ሁለት ባሕርያት /ተፈጥሮዎች/ መካከል ግጭት አለ፡፡ በሁለቱ «እኔዎች» /በሮሜ7፡14-25 ውስጥ ያሉት አሮጌው ሳውልና አዲሱ ጳውሎስ/ መካከል ያለውን ትግል/ውጊያ በጥንቃቄ ማጥናት ጠቃሚ ነው፡፡ ወጣንያን አማኞችን ተስፋ የሚያስቆርጠውና ግራ የሚያጋባው እንዲህ ዓይነቱ ልምምድ ነው፡፡ በዚህም ወቅት በመለወጥ ሰሞን ያለው የመጀመሪያው ደስታና ሐሴት ይቀዘቅዛል፤ አካሄድም ጥንቃቄ አልባ መሆን ይጀምራል፤ እናም ሥጋ ከቀድሞ ልማድና መሻቱ ጋር ራሱን ሲያነሳሳ ወደ ተስፋ መቁረጥ መሄድና በእግዚአብሔር ዘንድም ተቀባይነት ማግኘቱን ወደ መጠራጠር ይሄዳል፡፡ ይህ ወቅት ታላቅ አደጋ ያለበት ነው፡፡ በዚህ ዓይነት አስቸጋሪ ወቅት ጳውሎስ አሮጌው ባሕርይውን «ለሞት የተሰጠ ሰውነት» ብሎ እየጠራ አርነትን ለማግኘት ተማፅኖ አቅርቦአል፡፡ ምንም እንኳ የተለወጠ /የዳነ/ ሰው ቢሆንም፣ «ከሥጋ» አርነትን ያገኘው በጥረቱ ወይም ሕጉን ለመጠበቅ በመሞከሩ አይደለም - «በኢየሱስ ክርስቶስ በጌታችን» እንጂ/ሮሜ7፡24፣25/፡፡

    ይሁንና የሥጋ መኖር እንደእርሱ /ማለት እንደ ሥጋ/ ፈቃድ ለመሄድ ወይም ለመመላለስ ምክንያት መሆን አይችልም፡፡ አሮጌው ሰዋችን ከክርስቶስ ጋር እንደተሰቀለ፣ በዚህም ሁኔታ እኛ እንደሞትን፣ እኛም በምድር ያሉ ብልቶቻችንን ዕለት ዕለት በመግደል ይህን ቋሚ/መደበኛ/ ልምምዳችን ማድረግ እንደሚገባን ተምረናል፡፡

    ይህንንም የምናደርግበትን ኃይል የምናገኘው በእያንዳንዱ አማኝ ውስጥ ከሚኖረው ከመንፈስ ቅዱስ ነው /1ቆሮ6፡19/፤ የእርሱም የተባረከ ሥራው ሥጋን ማስገዛት ነው፡፡

    •  ነገር ግን እላለሁ በመንፈስ ተመላለሱ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ፡፡ ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በሥጋ ላይ ይመኛልና እነዚህም እርስ በርሳቸው ይቀዋወማሉ ስለዚህም የምትወዱትን ልታደርጉ አትችሉም፡፡ ገላ5፡16፣17፡፡
    •  እንደ ሥጋ ፈቃድ ብትኖሩ ትሞቱ ዘንድ አላችሁና በመንፈስ ግን የሰውነትን ሥራ ብትገድሉ በሕይወት ትኖራላችሁ፡፡ ሮሜ8፡13፡፡

    ስለዚህ የአሮጌውን ባሕርይ ጉትጐታ በፈቃድ ኃይል ወይም በጥሩ ውሳኔ ለመጋፈጥ ከመሞከር ይልቅ፣ ግጭቱን በውስጣችን ለሚኖረው የእግዚአብሔር መንፈስ ማስረከብ አስፈላጊ ነው፡፡

    በሮሜ7 ውስጥ የሚገኘው ደግሞ፣ ዳግም የተወለደ ሰው ከአሮጌው ባሕርዩ ጋር ያለው ትግል ነው፤ እናም በእጅጉ የግል /ፕጵረሰጸነቷለ/ የሆነ ጉዳይ ነው፡፡

    «የምጠላውን ... አደርጋለሁ፣» «የምወደውን አላደርገውም» የሚሉት አባባሎች በብዙ ክርስቲያኖች ልብ ውስጥም የሚያስተጋቡ አሳዛኝ የሽንፈት ኑዛዜዎች ናቸው፡፡ በስምንተኛው ምዕራፍ ውስጥ ትግሉ የቀጠለ ቢሆንም፣ ግለሰባዊ ጉዳይ መሆኑ በተባረከ ሁኔታ ያቆማል፡፡ በዚያ ምንም ዓይነት ሥቃይና ጭንቀት የለም፤ ምክንያቱም ጳውሎስ ከግጭቱ/ከትግሉ ውጭ ሆኖአል፤ አሁን ግጭቱ/ትግሉ «በሥጋና /በጠርሴሱ ሳውልና/»፣ በመንፈስ ቅዱስ መካከል ሲሆን፣ ጳውሎስ ግን በሰላምና በድል ውስጥ ነው፡፡

    -ይህ ድል የሚያመለክተው በሥጋ ላይ ማለትም ውስጣዊ የሆኑ የዝሙት ምኞት፣ ትዕቢት፣ ቊጣ ወዘተ ጉትጐታዎች ላይ የሚገኘውን ድል መሆኑ ልብ ይባል፤ ውጫዊ የሆኑ ማለትም ከውጭ የሚመጡ ፈተናዎቻችን ግን መፍትሔ የሚያገኙት ወደ ታላቁ ሊቀ ካህናችን ወደ ክርስቶስ በማቅረብ ነው፡፡-

    የሚከተሉትን ምንባባት በጥሞና እናጢናቸው፤

    • ከእንግዲህስ ወዲያ በኃጢአት እንዳንገዛ የኃጢአት ሥጋ ይሻር ዘንድ አሮጌው ሰዋችን ከእርሱ ጋር እንደ ተሰቀለ እናውቃለን የሞተስ ከኃጢአቱ ጸድቆአልና፡፡ ሮሜ6፡6፡፡
    • እኛ በመንፈስ እግዚአብሔርን የምናመልክ በክርስቶስ ኢየሱስም የምንመካ በሥጋም የማንታመን እኛ የተገረዝን ነንና፡፡ ፊል3፡3፡፡
    • እንዲሁም እናንተ ደግሞ በኃጢአት እንደሞታችሁ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ሆናችሁ ለእግዚአብሔር ሕያዋን እንደ ሆናችሁ ራሳችሁን ቊጠሩ፡፡ ሮሜ6፡11፡፡
    • ነገር ግን ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን ልብሱት፤ ምኞቱንም እንዲፈጽም ለሥጋ አታስቡ፡፡ ሮሜ13፡14፡፡
    • እንግዲህ ወንድሞች ሆይ ዕዳ አለብን እንደ ሥጋ ፈቃድ ግን እንኖር ዘንድ ለሥጋ አይደለም፡፡ ሮሜ8፡12፡፡

    8.የአማኝ ስፍራ እና ገሀዳዊ ሁኔታው

    ቅዱሳት መጻሕፍትን ይልቁንም ደግሞ መልእክታትን በትክክል ለመረዳት፣ በአማኙ በክርስቶስ ሥራ አማካኝነት ከእግዚአብሔር ዘንድ በተሰጠው ስፍራ እና በገሀዳዊ ሁኔታው ወይም ምልልሱ መካከል ያለውን ልዩነት ማወቅ ትልቅ ፋይዳ አለው፡፡ የመጀመሪያው ማለትም ስፍራው ሙሉ በሙሉ የክርስቶስ ሥራ ውጤት ሲሆን፣ ክርስቶስን በእምነት ከተቀበልንበት ጊዜ ጀምሮ ፍጹም የሆነና የተሟላ ነው፤ በአማኙ የኋላ/ቀጣይ/ ሕይወት ውስጥ የሚሆን ማናቸውም ነገር አማኙ በእግዚአብሔር ዘንድ ላለው ተቀባይነትም ሆነ ለዘላለማዊ ዋስትናው የሚጨምረው አንዳችም ነገር የለውም፡፡ በእግዚአብሔር ፊት የተቀባይነት ስፍራን የሚያስገኘው እምነት ብቻ ነው፤ እናም በምድር ላይ ካሉት አማኞች ሁሉ እጅግ ደካማ፣ እውቀተ-ቢስ፣ ፅናት የሌለውና በቀላሉ የሚወድቅ አማኝ፣ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እውነተኛ እምነት ያለው ከሆነ፣ በእግዚአብሔር ፊት ያለው የተቀባይነት ስፍራ እጅግ ብርቱ ከሆነ አማኝ ጋር ፍጹም አንድ ዓይነት ነው፡፡

    ይህ አማኙ በእግዚአብሔር ፊት ያለው ስፍራ ምን እንደሆነ ከሚከተሉት ምንባባት በአጭሩ ማየት ይቻላል፡፡

    • ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልንን ሰጣቸው፡፡ ዮሐ1፡12፡፡
    • ክርስቶስ ነው ብሎ በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር ተወልዷል፡፡ 1ዮሐ5፡1፡፡
    • ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን ማለት የእግዚአብሔር ወራሾች ነን፡፡ ሮሜ8፡17፡፡
    • ለማያልፍ ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል፡፡ 1ጴጥ1፡4፣5፡፡
    • እንደ ፈቃዱ ምክር ሁሉን የሚሠራ እንደ እርሱ አሳብ አስቀድመን የተወሰንን በክርስቶስ ደግሞ ርስትን ተቀበልን፡፡ ኤፌ1፡11፡፡
    • ወዳጆች ሆይ፣ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፣ ምንም እንደምንሆን ገና አልተገለጠም፡፡ ዳሩ ግን ቢገለጥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና እርሱን እንድንመስል እናውቃለን፡፡ 1ዮሐ3፡2፡፡
    • እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ የንጉሥ ካህናት፣ ቅዱስ ሕዝብ፣ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፡፡ 1ጴጥ2፡9፡፡
    • ለወደደን ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን መንግሥትም ለአምላኩና ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገን ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁን አሜን፡፡ ራእ1፡5፣6፡፡
    • ለአለቅነትና ለሥልጣንም ሁሉ ራስ በሆነ በእርሱ ሆናችሁ ተሞልታችኋል-የተሟሉ ሆናችኋል-፡፡ ቈላ2፡1ዐ፡፡
    • እንግዲህ በእምነት ከጸደቅን በእግዚአብሔር ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እንያዝ በእርሱም ደግሞ ወደ ቆምንበት ወደዚህ ጸጋ በእምነት መግባት አግኝተናል በእግዚአብሔር ክብርም ተስፋ እንመካለን፡፡ ሮሜ5፡1፣2፡፡
    • በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና፡፡ ዮሐ3፡16፡፡
    • የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ፡፡ 1ዮሐ5፡13፡፡
    • እንግዲህ ወንድሞች ሆይ በመረቀልን በአዲስና በሕያው መንገድ ወደ ቅድስት በኢየሱስ ደም በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል እንድንገባ ድፍረት ስላለን፤.... ዕብ1ዐ፡19፡፡
    • በውድ ልጁም እንዲያው የሰጠን የጸጋው ክብር ይመሰገን ዘንድ ይህን አደረገ፡፡ ኤፌ1፡6፡፡
    • ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለሆነ ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወትን ሰጠን በጸጋ ድናችኋልና፡፡ ኤፌ2፡4-6፡፡
    • አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል፡፡ ኤፌ2፡13፡፡
    • አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን ባሪያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና፡፡ ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል፡፡ 1ቆሮ12፡13፡፡
    • ማንም የገዛ ሥጋውን የሚጠላ ከቶ የለምና ነገር ግን የአካሉ ብልቶች ስለሆንን ክርስቶስ ደግሞ ለቤተክርስቲያን እንዳደረገላት ይመግበዋል ይከባከበውማል፡፡ ኤፌ5፡3ዐ፡፡
    • ወይስ ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደሆነ አታውቁምን? 1ቆሮ6፡19፡፡

    እነዚህ አስደናቂ የሆኑ ነገሮች በሙሉ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሚያምኑ አማኞች በጠቅላላ እውነት ናቸው፡፡ ከእነዚህ ድንቅ ከሆኑት ዝርዝሮች መካከል አንድም እንኳ በጸሎት ወይም በአገልግሎት ትጋት፣ ወይም ቤተክርስቲያን በመሄድ ወይም ምጽዋት በመስጠት፣ ወይም በሕይወት ቅድስና ወይም በማናቸውም ዓይነት የበጐ ሥራዎች መገለጫ እንደሚገኙ አልተነገረም፡፡ ሁሉም በክርስቶስ በኩል በሚሆን እምነት ከእግዚአብሔር የተሰጡ ስጦታዎች ናቸው፤ ስለሆነም ለሁሉም አማኞች እኩል ናቸው፡፡ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ ያለው ጨካኙ የፊልጵስዩስ ወህኒ ጠባቂ፣ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንዳመነ ወዲያውኑ፣ የእግዚአብሔር ልጅ፣ ከክርስቶስ ጋር አብሮ ወራሽ፣ ንጉሥና ካህን እንዲሁም የማይበሰብስ፣ የማይበላሽና የማይጠፋ ርስት ባለቤት ሆኖአል፡፡ ኢየሱስ ጌታ መሆኑን በልቡ አምኖ በአፉም በመሰከረበት በዚያ ቅጽበት፣ እርሱ ከሁሉም ነገሮች የጸደቀ ሆኖአል-ከእግዚአብሔር ጋር ሰላምን አግኝቶአል፤ በጸጋውም ስፍራን አግኝቶአል እንዲሁም የተረጋገጠ የክብር ተስፋን ተቀብሎአል፡፡ እርሱ የዘላለም ሕይወትን ስጦታ ተቀብሏል፤ ክርስቶስ ራሱ ባለው የተቀባይነት መጠን ልክ ተቀባይነትን አግኝቶአል፤ በመንፈስ ቅዱስ ታትሞአል፤ መንፈስ ቅዱስ በውስጡ መኖር ጀምሮአል፤ እንዲሁም ወደ ምጢራዊው የክርስቶስ አካል ውስጥ ተጠምቆአል፤ ወዲያውኑም የእግዚአብሔርን ጽድቅ ለብሷል /ሮሜ3፡22/፤ ከክርስቶስም ጋር ሕይወት አግኝቶአል /ማለትም ከሞት/፤ ከእርሱ ጋር ከሞት ተነሥቶአል፤ እንዲሁም ከእርሱ ጋር በሰማያዊ ስፍራ ተቀምጦአል፡፡

    አሁን ያለበት ገሀዳዊው ሁኔታ ምን ይመስላል የሚለው ሌላ ጉዳይ /ነገር/ ነው፤ በእርግጥ ያ በእግዚአብሔር ፊት ካለው ከከበረ ስፍራው አንጻር በጣም ዝቅ ያለና የወረደ ነው፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ እንዳለው ስፍራ፣ በምልልሱ በአንድ ጊዜ ወዲያውኑ፣ ንጉሣዊ፣ ካህናዊና ሰማያዊ ይዘት አይኖረውም፡፡ የሚከተሉት ምንባቦች እነዚህ ሁለት ነገሮች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዴት ተነጻጽረው እንደሚገኙ ያሳዩናል፡፡

    በእግዚአብሔር ዘንድ ያለ ስፍራ
    • በቆሮንቶስ ላለች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ኢየሱስ ለተቀደሱት የእነርሱና የእኛ ጌታ የሆነውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ስም በየስፍራው ከሚጠሩት ሁሉ ጋር ቅዱሳን ለመሆን ለተጠሩት ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን፡፡ በክርስቶስ ኢየሱስ ስላመናችሁ በተሰጣችሁ በእግዚአብሔር ጸጋ ምክንያት ሁልጊዜ ስለ እናንተ አምላክን አመሰግናለሁ ለክርስቶስ መመስከሬ በእናንተ ዘንድ እንደጸና በነገር ሁሉ በቃልም ሁሉ በእውቀትም ሁሉ በእርሱ ባለጠጎች እንድትሆኑ ተደርጋችኋልና፡፡ እንደዚህ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ ስትጠባበቁ አንድም የጸጋ ስጦታ እንኳ አይጐድልባችሁም እርሱም ደግሞ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ያለ ነቀፋ እንድትሆኑ እስከ ፍጻሜ ድረስ ያጸናችኋል፡፡ ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው፡፡ 1ቆሮ1፡2-9፡፡
    • ከእናንተም አንዳንዶቹ እንደ እነዚህ ነበራችሁ ነገር ግን በጌታ በኢየሱስ ስም በአምላካችን መንፈስ ታጥባችኋል ተቀድሳችኋል ጸድቃችኋል፡፡ 1ቆሮ6፡11፡፡
    • ሥጋችሁ የክርሰቶስ ብልቶች እንደሆነ አታውቁምን? 1ቆሮ6፡15፡፡
    • ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፡-
    ገሃዳዊ ሁኔታ
    • ወንድሞች ሆይ በመካከላችሁ ክርክር እንዳለ ስለ እናንተ የቀሎዔ ቤተ ሰዎች አስታውቀውኛልና፡፡ 1ቆሮ1፡11፡፡
    • እኔም ወንድሞች ሆይ የሥጋ እንደመሆናችሁ በክርስቶስም ሕፃናት እንደ መሆናችሁ እንጂ መንፈሳውያን እንደ መሆናችሁ ልናገራችሁ አልቻልሁም፡፡ ገና ጹኑ መብል ለመብላት አትችሉም ነበርና ወተት ጋትኋችሁ ገና ሥጋውያን ናችሁና እስከ አሁን ድረስ ገና አትችሉም፡፡ ቅናትና ክርክር ስለሚገኝባችሁ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደላችሁምን? እንደ ሰው ልማድስ አትመላለሱምን? 1ቆሮ3፡1-3፡፡
    • አንዳንዱ ግን ወደ እናንተ የማልመጣ እየመሰላቸው የታበዩ አሉ፡፡ 1ቆሮ4፡18፡፡
    • እናንተም ታብያችኋል ይልቅስ እንድታዝኑ አይገባችሁምን? ይህን ሥራ የሠራው ከመካከላችሁ ይወገድ፡፡ 1ቆሮ5፡2፡፡
    • እንግዲህ ፈጽሞ የእርስ በርስ ሙግት እንዳለባችሁ በእናንተ ጉድለት ነው፡፡ ብትበደሉ አይሻልምን? ብትታለሉስ አይሻልምን? 1ቆሮ6፡7፡፡ እንግዲህ የክርስቶስ ብልቶችን ወስጄ የጋለሞታ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ፡፡ ማቴ16፡17፡፡
    • በእግዚአብሔር እውቀት እያደጋችሁ ከደስታም ጋር በሁሉ ለመጽናትና ለመታገሥ እንደ ክብሩ ጉልበት መጠን በኃይል ሁሉ እየበረታችሁ በቅዱሳንም ርስት በብርሃን እንድንካፈል ያበቃንን አብን እያመሰገናችሁ በነገር ሁሉ ደስ ልታሰኙ ለጌታ እንደሚገባ ትመላለሱ ዘንድ እንለምናለን፡፡ እርሱንም ከጨለማ ሥልጣን አዳነን ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን፡፡ ቈላ1፡12፣13፡፡ ብልቶች ላድርጋቸውን? አይገባም፡፡ 1ቆሮ6፡15፡፡
    • እርሱ ግን ዘወር ብሎ ጴጥሮስንም ወደ ኋላዬ ሂድ አንተ ሰይጣን የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል አለው፡፡ ማቴ16፡23፡፡

    አሁን ግን እናንተ ደግሞ ቊጣንና ንዴትን ክፋትንም ከአፋችሁም ስድብን የሚያሳፍርንም ንግግር አስወግዱ እርስ በርሳችሁ ውሸት አትነጋገሩ አሮጌውን ሰው ከሥራው ጋር ገፋችሁታልና፡፡ ቈላ3፡8፣9፡፡

    በጸጋ ያለው መለኮታዊው የአሠራር ሥርዓት፣ በመጀመሪያ ከፍተኛ የሆነውን ስፍራ መስጠት፣ በመቀጠልም አማኙ ከዚህ ስፍራ ጋር የሚሄድ ገሀዳዊ ሁኔታን እንዲጠብቅ መምከር መሆኑን አንባቢው ማስተዋል አይሳነውም፡፡ ከሕዝቡ መኳንንት /መሳፍንት/ ጋር ያስቀምጠው ዘንድ ... ምስኪኑን ከጉድፍ ያስነሣል /1ሳሙ2፡8/፤ ከዚያ በኋላም እንደ መሳፍንት እንዲኖር ይመክራል፡፡ እንደ ምሳሌ የሚከተሉትን እንመልከት፡፡

    ስፍራ

    • ከእንግዲህስ ወዲያ ለኃጢአት እንዳንገዛ ከእርሱ ጋር እንደተሰቀልን እናውቃለን፣ የሞተስ ከኃጢአቱ ጸድቆአልና፡፡ ሮሜ6፡6፡፡
    • እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ፡፡ ማቴ5፡14፡፡
    • ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነውና፣ ይህም እንደ ራሱ አሳብና ጸጋ መጠን ነው እንጂ እንደ ሥራችን መጠን አይደለም፤ ይህም ጸጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን፡፡ 2ጢሞ1፡9፡
    • በሚመጡ ዘመናትም ክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ ከእርሱ ጋር አስነሣን፡፡ ኤፌ2፡6፡፡
    • ሕይወታችሁ የሆነ ክርስቶስ በሚገለጥበት በዚያን ጊዜ እናንተ ደግሞ ከእርሱ ጋር በክብር ትገለጣላችሁ፡፡ ቈላ3፡4፡፡
    • ቀድሞ በጨለማ ነበራችሁና አሁን ግን በጌታ ብርሃን ናችሁ፡፡ ኤፌ5፡8፡፡
    • ሁላችሁ የብርሃን ልጆች የቀንም ልጆች ናችሁና፡፡ እኛ ከሌሊት ወይም ከጨለማ አይደለንም፡፡ 1ተሰ5፡5፡፡
    • እግዚአብሔር ለቁጣ አልመረጠንምና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ መዳንን ለማግኘት ነው እንጂ፡፡ የምንነቃም ብንሆን የምናንቀላፋም ብንሆን ከእርሱ ጋር አብረን በሕይወት እንኖር ዘንድ ስለ እኛ ሞተ፡፡ 1ተሰ5፡9፣1ዐ፡፡
    • በዚህም ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋ አንድ ጊዜ ፈጽሞ በማቅረብ ተቀድሰናል፡፡ ዕብ1ዐ፡1ዐ፡፡
    • ... ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበብና ጽድቅ ቅድስናም ቤዛነትም በተደረገልን በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው፡፡ 1ቆሮ1፡3ዐ፡፡
    • አንድ ጊዜ በማቅረብ የሚቀደሱትን የዘላለም ፍጹማን አድርጎአቸዋልና፡፡ ዕብ1ዐ፡14፡Ý
    • እንግዲህ ፍጹማን የሆንን ሁላችን ይህን እናስብ፡፡ ፊል3፡15፡Ý
    • በፍርድ ቀን ድፍረት ይሆንልን ዘንድ ፍቅር በዚህ ከእኛ ጋር ተፈጽሞአል፤ እርሱ እንዳለ እኛ ደግሞ እንዲሁ በዚህ ዓለም ነንና፡፡ 1ዮሐ4፡17፡Ý
    • ከዓለማዊ ከመጀመሪያ ትምህርት ርቃችሁ ከክርስቶስ ጋር ከሞታችሁ እንደ ሰው ሥርዓትና ትምህርት በዓለም እንደምትኖሩ ስለምን ትገዛላችሁ? ቈላ2፡2ዐ፡፡
    • መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ፡፡ ማቴ5፡16፡፡
    • ስለዚህ ወዳጆች ሆይ ሁልጊዜ እንደ ታዘዛችሁ በእናንተ ዘንድ በመኖሬ ብቻ ሳይሆን ይልቁን አሁን ስርቅ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ፡፡ ፊል2፡12፡፡
    • ከእንግዲህ ከክርስቶስ ጋር ከተነሣችሁ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጦ ባለበት በላይ ያለውን እሹ፡፡ ቈላ3፡1፡፡
    • እንግዲህ በምድር ያሉቱን ብልቶቻችሁን ግደሉ፤ እነዚህም ዝሙትና ርኲሰት ፍትወትም ክፉ ምኞትም ጣዖትንም ማምለክ የሆነ መጐምጀት ነው፡፡ ቈላ3፡5፡፡
    • ቀድሞ ጨለማ ነበራችሁና አሁን ግን በጌታ ብርሃን ናችሁ፡፡ ኤፌ5፡8፡፡
    • እንግዲያስ እንንቃ በመጠንም እንኑር እንጂ እንደ ሌሎች አናንቀላፋ፡፡ 1ተሰ5፡6፡፡
    • ስለዚህ እናንተ ደግሞ እንደምታደርጉ እርስ በእርሳችሁ ተመካከሩ አንዱም አንዱም ሌላውን ያንጸው፡፡ 1ተሰ5፡11፡፡
    • በእውነትህ ቀድሳቸው፤ ቃልህ እውነት ነው፡፡ ዮሐ17፡17፡፡
    • የሰላምም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ፤ 1ተሰ5፡23፡፡
    • አሁን እንዳገኘሁ ወይም አሁን ፍጹም እንደ ሆንሁ አይደለም፤ ፊል3፡12፡Ý
    • ስለዚህ የክርስቶስን ነገር መጀመሪያ የሚናገረውን ቃል ትተን ወደ ፍጻሜ -ፍጹምነት- እንሂድ፡፡ ዕብ6፡1፡Ý

    በእርሱ እኖራለሁ የሚል እርሱ እንደ ተመላለሰ ራሱ ደግሞ ሊመላለስ ይገባዋል፡፡ 1ዮሐ2፡6፡Ý

    አንባቢው በእግዚአብሔር ዘንድ ባለው ስፍራና በገሃዳዊው እውነታ /ሁኔታ/ መካከል ያለውን ልዩነት በግልጽ የሚያሳዩ ምንባባትን ከላይ ከተዘረዘሩት በተጨማሪ ብዙ ማከል ይችላል፡፡ ፍጹም ሊታሰብ ለማይቻል ለከበረ ስፍራ የሚገባ መሆን አለመሆኑን ለማወቅ፣ ገና በፈተና ውስጥ እያለፈ/እየተፈተነ/ አለመሆኑ ግልጽ ነው፤ ይልቁንም ፍጹም ለዚያ ክብር የማይገባ መሆኑን በመመስከር /በመናገር/ ሙሉ በሙሉ የክርስቶስ ሥራ ውጤት የሆነን ስፍራ ያገኛል፡፡ ከስፍራ አንጻር (positionally) «የዘላለም ፍጹም» /ዕብ1ዐ፡14/ ነው፤ ነገር ግን አሁን ካለበት ገሃዳዊ ሁኔታ (state) አንጻር ራሱን ሲመለከት እንዲህ ሊል ይችላል፣ «አሁን እንዳገኘሁ ወይም አሁን ፍጹም እንደ ሆንሁ አይደለም፣» /ፊል3፡12/፡፡

    ካመነ በኋላ እግዚአብሔር ስለ እርሱ የሚሠራቸው ሥራዎች በሙሉ፣ ማለትም፣ በአካሄዱና በሕሊናው ላይ ቃሉን መጠቀም /ዮሐ17፡17፤ ኤፌ5፡26/ በአብ እጆች መቀጣት /ዕብ12፡1ዐ፣ 1ቆሮ11፡32/፣ የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት /ኤፌ4፡11፡12/ የምድረ በዳው ጉዞ ችግሮችና ፈተናዎች /1ጴጥ4፡12-14/፣ እርሱ /ኢየሱስ/ ሲገለጥ የሚሆነው የመጨረሻው መለወጥ /1ዮሐ3፡2/ እነዚህ ሁሉ የአማኙን ባሕርይ ልክ ባመነ ጊዜ ካገኘው ስፍራ ጋር ፍጹም እንዲስተካከል /እንዲመሳሰል/ ለማድረግ የታሰቡ ናቸው፡፡ በእርግጥ አማኝ በጸጋ ያድጋል እንጂ ወደ ጸጋ አያድግም፡፡

    በዕድሜው ልጅ የሆነ የአንድን አገር ንጉሥ እንደ ምሳሌ እንውሰድ፤ ይህ ሰው እንደማንኛውም ሕፃን የራሱን ፍላጐት ብቻ የሚከተልና እውቀት የሌለው እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ በጣም ታዛዥ፣ የሚሉትን የሚሰማ፣ እንዲሁም ተወዳጅ ስለሚሆን፣ ደስተኛና ጐሽታን የሚያገኝ ይሆናል፡፡ በሌላ ጊዜ ደግሞ አዋኪ፣ እምቢተኛና የማይታዘዝ ይሆናል፤ በዚህም ምክንያት ደስተኛ አይሆንም እናም ምናልባት ሊገሠጽም ይችላል - ነገር ግን በሁለተኛውም ሁኔታ /ጊዜ/ እንደመጀመሪያው ሁሉ ያው ንጉሥ ነው፡፡ ጊዜ በጨመረ ቁጥር ራሱን ማሻሻልና ለትክክለኛው መንገድ በፈቃደኝነት መገዛትን እየተማረ ይሄዳል ተብሎ ተስፋ ሊደረግ ይችላል፤ በዚህም የተነሣ ንጉሣዊ ባሕርይው እያደገ ይሄዳል ነገር ግን ንጉሥነቱ ሁሌም ያው ነው፤ ንጉሥ ሆኖ ተወልዶአልና፡፡

    የነገሥታት ንጉሥ እና የጌቶች ጌታ የሆነው የእርሱ እውነተኛ ልጅ የሆነ ሁሉ፣ ወደዚህ ወደ ንጉሣዊ ባሕርይ እያደገ የሚሄድ መሆኑ የተረጋገጠ ነው፤ በመጨረሻም ላይ ስፍራና ገሃዳዊ ሁኔታ /እውነታ/ እኩል ይሆናሉ፡፡ ነገር ግን ስፍራው ፍጹም ለሆነው ባሕርይ ብድራት አይደለም፤ ይልቁንም ባሕርይው ከስፍራው ላይ የሚያድግ ነው፡፡

    9.ደኅንነት እና ሽልማት /ዋጋ/

    የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት፣ ለጠፉት ሰዎች በጌታ ኢየሱስ በክርስቶስ ላይ በሚኖር እምነት በኩል መዳን/ደኅንነት/፣ ለዳኑት ደግሞ ስለ ታማኝ አገልግሎታቸው ሽልማት ወይም ዋጋ እንዳለ የሚያስረዱ ትምህርቶችን ይዘዋል፤ እናም ለአንባቢው በእነዚሀ በሁለቱ መካከል ያለውን ልዩነት በትክክል ለይቶ መረዳት ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ ይህንንም ልዩነት የሚከተሉትን ንጽጽሮች በጥንቃቄ በማጠናት ማየት ይቻላል፡፡

    1. ደኅንነት ነጻ ስጦታ ነው፡
    • ኢየሱስ መልሶ፣ የእግዚአብሔርን ስጦታና፣ ውሃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን መሆኑንስ ብታውቂ፣ አንቺ ትለምኝው ነበርሽ የሕይወትም ውሃ ይሰጥሽ ነበር አላት፡፡ ዮሐ4፡1ዐ፡፡
    • እናንተ የተጠማችሁ ሁሉ፣ ወደ ውኃ ኑ፣ ገንዘብም የሌላችሁ ኑና ግዙ ብሉም ኑ ያለ ገንዘብም ያለ ዋጋም የወይን ጠጅና ወተት ግዙ፡፡ ኢሳ55፡1፡፡
    •  መንፈሱና ሙሽራይቱም፡- ና ይላሉ የሚሰማም፡- ና ይበል፡፡ የተጠማም ይምጣ የወደደም የሕይወትን ውኃ እንዲያው -በነጻ- ይውሰድ፡፡ ራእ22፡17፡፡
    •  የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው፡፡ ሮሜ6፡23፡፡
    • ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም፡፡ ኤፌ2፡8፣9፡፡

    ከደኅንነት ነጻ ስጦታ መሆን አንጻር ደግሞ የሚከተለውን ልብ በል፤

    ሽልማት /ዋጋ/ በሥራ የሚገኝ ነው፡
    • ማንም ከእነዚህ ከታናናሾች አንድ ቀዝቃዛ ጽዋ ውሃ ብቻ በደቀመዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላችኋለሁ ዋጋው አይጠፋበትም፡፡ ማቴ.1ዐ፡42፡፡
    • መልካሙን ገድል ተጋድዬአለሁ ሩጫውን ጨርሼአለሁ ሃይማኖትን -እምነትን- ጠብቄአለሁ ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፤ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም፡፡ 2ጢሞ 4፡7፣8፡፡
    • እነሆ በቶሎ እመጣለሁ ለእያንዳንዱም ዋጋዬ -ሽልማቱ- ከእኔ ጋር አለ፡፡ ራእ 22፡12፡፡
    • እሽቅድምድም ስፍራ የሚሮጡት ሁሉ እንዲሮጡ ነገር ግን አንዱ ብቻ ዋጋውን -ሽልማቱን- እንዲቀበል አታውቁምን? እንዲሁም ታገኙ ዘንድ ሩጡ፡፡ የሚታገል ሁሉ በነገር ሁሉ ሰውነቱን ይገዛል፤ እነዚያም የሚጠፋውን አክሊል ሊያገኙ ነው እኛ ግን የማይጠፋውን፡፡ 1ቆሮ9፡24፣25፡፡
    • እርሱም፣ መልካም አንተ በጎ ባርያ በጥቂት የታመንህ ስለሆንህ በአሥር ከተማዎች ላይ ሥልጣን ይሁንልህ አለው፡፡ ሉቃ19፣17፡፡
    • ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና፣ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ማንም ግን በዚህ መሠረት ላይ በወርቅ ቢሆን በብርም በከበረ ድንጋይም በእንጨትም በሣርም ወይም በአገዳ ቢያንጽ፣ የእያንዳንዱ ሥራ ይገለጣል፣ በእሳትም ስለሚገለጥ ያ ቀን ያሳያልና የእያንዳንዱም ሥራ እንዴት መሆኑን እሳቱ ይፈትነዋል፡፡ ማንም በእርሱ ላይ ያነጸው ሥራ ቢጸናለት ደመወዙን -ሽልማቱን- ይቀበላል፣ የማንም ሥራ የተቃጠለበት ቢሆን ይጐዳበታል -ይከስራል-፤ እርሱ ራሱ ግን ይድናል፣ ነገር ግን በእሳት እንደሚድን ይሆናል፡፡ 1ቆሮ3፡11-15፡፡
    • ልትቀበለው ያለህን መከራ አትፍራ፡፡ እነሆ እንድትፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ ሊያገባችሁ አለው፤ አሥር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ፤ እስከ ሞት ድረስ የታመንህ ሁን፣ የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ፡፡ ራእ2፡1ዐ፡፡
    • (በዚህ ምንባብ መሠረት ለሰምርኔስ ቅዱሳን ሊሰጣቸው ያለው፣ «የሕይወት አክሊል» እንጂ፣ «ሕይወት» አይደለም፣ ምክንያቱም እነሱ የዘላለም ሕይወትን አስቀድመው በክርስቶስ በኩል አግኝተዋልና፤ ነገር ግን፣ አክሊሎች የሽልማቶች ምልክት ናቸው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አራት የአክሊል ዓይነቶች ተጠቅሰዋል፤ «የደስታ አክሊል» - የአገልግሎት ብድራት /ፊል4፡1፤ 1ተሰ2፡19/፤ «የጽድቅ አክሊል» - ለምስክርነት ታማኝ የመሆን ብድራት /2ጢሞ9፡8/፤ «የሕይወት አክሊል» - በፈተና ታማኝ የመሆን ብድራት /ያዕቆ1፡12፤ ራእ.2፡1ዐ/፤ «የክብር አክሊል» - በመከራ ታማኝ የመሆን ብድራት /1ጴጥ5፡4፤ ዕብ2፡9/)
    2. ደኅንነት አሁን የተያዘ /የአሁን ጊዜ/ ነው -፡
    • በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፣ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቁጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም፡፡ ዮሐ3፡36፡፡
    • እውነት እውነት እላችኋለሁ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፣ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም፡፡ ዮሐ5፡24፡፡
    • እውነት እውነት እላችኋለሁ በእኔ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፡፡ ዮሐ6፡47፡፡
    • ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነውና፤ ይህም እንደ ራሱ ሐሳብና ጸጋ መጠን ነው እንጂ እንደ ሥራችን መጠን አይደለም፣ ይህም ጸጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን፡፡ 2ጢሞ1፡9፡፡
    • ሴቲቱንም እምነትሽ አድኖሻል በሰላም ሂጂ አላት፡፡ ሉቃ7፡5ዐ፡፡
    • እንደምሕረቱ መጠን ለአዲስ ልደት በሚሆነው መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በመታደስ አዳነን እንጂ እኛ ስላደረግነው በጽድቅ ስለነበረው ሥራ አይደለም፡፡ ቲቶ3፡5፡፡
    • እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው፡፡ 1ዮሐ5፡11፡፡

    ነገር ግን፣

    ሸልማት ወደፊት የሚገኝ ነው፡
    • የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣ ዘንድ አለውና፤ ያን ጊዜ ለሁሉ እንደሥራው ያስረክበዋል፡፡ ማቴ፡16፣27፡፡
    • አንካሶችንም ዕውሮችንም ጥራ፣ የሚመልሱት ብድራት የላቸውምና ብፁዕ ትሆናለህ በጻድቃን ትንሣዔ ይመለስልሃልና፡፡ ሉቃ14፡14፡፡
    • እነሆ በቶሎ እመጣለሁ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ፡፡ ራእ22፡12፡፡
    • የእረኞች አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ፡፡ 1ጴጥ5፡4፡፡
    • ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፤ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም፡፡ 2ጢሞ4፡8፡፡
    • ከብዙ ዘመን በኋላ የእነዚያ ባሮች ጌታ መጣና ተቈጣጠራቸው፡፡ ማቴ25፡19፡፡

    እግዚአብሔር ሰማያዊና ዘላለማዊ በሆኑ ክብሮች የቅዱሳኑን ታማኝ አገልግሎት ለመሸለም ቃል የገባበት ዓላማ፣ እነርሱ ምድራዊ የሆነ ባለጠግነትንና ደስታን ከማሳደድ እንዲመለሱ፣ በመከራም እሳት ውስጥ እንዲጸኑ፣ እንዲሁም ክርስቲያናዊ የሆኑ መልካም ባሕርያትን በማሳየት እንዲበረታቱ ለማድረግ ነው፡፡ እነዚህን ተመልከት፤ ዕብ11፡8-10፣24-27፤ 12፡2፣3፤ ሉቃ14፡12፣14፤ ማቴ1ዐ፣41፣42፤ ዕብ6፡1ዐ፤ ቈላ3፡22-24፤ ማቴ5፡11፣12፤ ዮሐ4፡35፣36፤ ዳን12፡3፤ ሉቃ12፡35-37፤ እና 2ጢሞ4፡8፡፡

    በመጨረሻም፣ በራእ3፡11 የተገለጠውን ማስጠንቀቂያ ልብ እንበል፡፡፡

    1ዐ. አማኞች እና የአፍ-አማኞች

    ለእግዚአብሔር የተለየ /የእግዚአብሐር የሆነ/ ሕዝብ በዚህ ምድር ላይ መኖር ከጀመረበት ጊዜ አንሥቶ እነሱ በመካከላቸው ባሉ፣ ነገር ግን የእነርሱ ወገን ባልሆኑ፣ ግን ደግሞ በአፋቸው የእነርሱ እንደሆኑ በሚናገሩ ሰዎች በእጅጉ እየተቸገሩ አሉ፡፡ ከኤደን በር መግቢያ ጀምሮ፣ «የሰው ልጅ መላእክቱን -ልኮ- ከመንግሥቱም እንቅፋትን ሁሉ ዓመፃንም የሚያደርጉትን -ለቅመው-... ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ -እስኪያበሩ-» /ማቴ13፡41-43/ ድረስ ይህ ሁኔታ ይቀጥላል፡፡

    በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ የእነዚህ የእንክርዳድና ስንዴዎች ማለትም የአፍ-አማኞች እና የእውነተኛ አማኞች ተቀላቅሎ መገኘት፣ ብዙ የቃሉን ተማሪዎች ግራ ሲያጋባ ይገኛል፤ ይህም የሆነው፣ ራሳቸውን ለሚያስቱ ወይም ለግብዞች የተሰጡትን ማስጠንቀቂያዎች፣ ለእግዚአብሔር ልጆች የተሰጡ አድርገው በመወሰደቸው ነው፡፡

    የእነዚህ የሁለቱ ተቀላቅለው መገኘት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ቦታ ተገልጾአል፡፡ እነዚህን ተመልከት፤ ዘፍ4፡3-5፤ ዘጸ12፡38፤ ዘኁል11፡4-6፤ ነህ13፡1-3፤ 7፡63-65፤ ማቴ13፡24-3ዐ፣37-43፤ 2ቆሮ11፡13-15፤ ገላ2፡4፤ እና 2ጴጥ2፡1፣2፡፡

    እውነተኛ አማኞችን፣ የሃይማኖት መልክ ብቻ ይዘው ከተቀመጡ ግብዞች እንዲሁም በነጻ የተሰጠውን ደኅንነት ተቀብሎ ከመፈጸም ይልቅ የራሳቸውን ደኅንነት ለመሥራት ከሚፍጨረጨሩ ሕግ-አክራሪዎች የሚለዩ ምንባባትን በሙሉ በዚህ አጭር ጥናት ውስጥ መዘርዘር አስቸጋሪ ነው፡፡ ፊል2፡12፣13ን ከኤፌ8፣9 ጋር ተመልከት፡፡

    ይሁንና የሚከተሉት ምንባባት በሁለቱ መካከል ያለውን ልዩነት በግልጽ ያስቀምጣሉ፡፡

    እነዚህን አነጻጽር፡

    1.አማኞች ድነዋል
    • እምነትሽ አድኖሻል በሰላም ሂጂ አላት፡፡ ሉቃ7፡5ዐ፡፡
    • በሐዋርያትም ትምህርትና በኅብረት እንጀራውንም በመቁረስ በየጸሎቱም ይተጉ ነበር፡፡ ሐዋ2፡42፡፡
    • በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል፤ እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ ለዘላለምም አይጠፉም፤ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም፡፡ ዮሐ1ዐ፡27-29፡፡
    • አብ የሚሰጠኝ ሁሉ ወደ እኔ ይመጣል፤ ወደ እኔም የሚመጣውን ከቶ ወደ ውጭ አላወጣውም፤ ፈቃዴን ለማድረግ አይደለም እንጂ የላከኝን ፈቃድ ለማድረግ ከሰማይ ወርጃለሁና፡፡ ከሰጠኝም ሁሉ አንድን ስንኳ እንዳላጠፋ በመጨረሻው ቀን እንዳስነሣው እንጂ የላከኝ የአብ ፈቃድ ይህ ነው፡፡ ዮሐ6፡37፣39፡፡
    • ሊገዙም በሄዱ ጊዜ ሙሽራው መጣ ተዘጋጅተው የነበሩትም ከእርሱ ጋር ወደ ሰርግ ገቡ ደጁም ተዘጋ፡፡ ማቴ25፡1ዐ፡፡
    • ... ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚአብሔር ጽድቅ ነው፤ ሮሜ3፡22፡፡
    • የበጉ ሰርግ ስለደረሰ ሚስቱም ራስዋን ስላዘጋጀች ደስ ይበለን፣ ሐሤትም እናድርግ ክብርንም ለእርሱ እናቅርብ፡፡ ራእ19፡7፡፡
    • እናድርግ ክብርንም ለእርሱ እናቅርብ፡፡ ራእ19፡7፡፡ መልካም እረኛ እኔ ነኝ አብም እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ፤ የራሴም በጎች ያውቁኛል ነፍሴንም ስለበጎች አኖራለሁ፡፡ ዮሐ1ዐ፡14፡፡
    • ሲሞንም ደግሞ ራሱ አመነ ተጠምቆም ከፊልጶስ ጋር ይተባበር ነበር፤ የሚደረገውንም ምልክትና ታላቅ ተአምራት ባየ ጊዜ ተገረመ ... ሲሞንም በሐዋርያት እጅ መጫን መንፈስ ቅዱስ እንዲሰጥ ባየ ጊዜ ገንዘብ አመጣላቸውና እጄን የምጭንበት ሁሉ መንፈስ ቅዱስን
    • ይቀበል ዘንድ ለእኔ ደግሞ ይህን ሥልጣን ስጡኝ አለ፡፡ ጴጥሮስ ግን እንዲህ አለው የእግዚአብሔርን ስጦታ በገንዘብ እንድታገኝ አስበሃልና ብርህ ከአንተ ጋር ይጥፋ፡፡ ልብህ በእግዚአብሔር ፊት የቀና አይደለምና ከዚህ ነገር ዕድል ወይም ፈንታ የለህም፡፡ ሐዋ8፡13፣18-21፡፡
    • ከእኛ ዘንድ ወጡ፣ ዳሩ ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ከእኛ ጋር ጸንተው በኖሩ ነበር ነገር ግን ሁሉ ከእኛ ወገን እንዳልሆኑ ይገለጡ ዘንድ ወጡ፡፡ 1ዮሐ2፡19፡፡
    • ርኲስ መንፈስ ግን ከሰው በወጣ ጊዜ ዕረፍት እየፈለገ ውኃ በሌለበት ቦታ ያልፋል አያገኝምም፡፡ በዚያን ጊዜም፣ ወደወጣሁበት ቤቴ እመለሳለሁ ይላል፤ ቢመጣም ባዶ ሆኖ ተጠርጎና አጊጦ ያገኘዋል፡፡ ከዚያ ወዲያ ይሄድና ከእርሱ የከፉትን ሰባት ሌሎችን አጋንንት ከእርሱ ጋር ይወስዳል፣ ገብተውም በዚያ ይኖራሉ፤ ለዚያም ሰው ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛው ይብስበታል፡፡ ማቴ12፡43-45፡፡
    • ርኲስ መንፈስ ግን ከሰው በወጣ ጊዜ ዕረፍት እየፈለገ ውኃ በሌለበት ቦታ ያልፋል አያገኝምም፡፡ በዚያን ጊዜም፣ ወደወጣሁበት ቤቴ እመለሳለሁ ይላል፤ ቢመጣም ባዶ ሆኖ ተጠርጎና አጊጦ ያገኘዋል፡፡ ከዚያ ወዲያ ይሄድና ከእርሱ የከፉትን ሰባት ሌሎችን አጋንንት ከእርሱ ጋር ይወስዳል፣ ገብተውም በዚያ ይኖራሉ፤ ለዚያም ሰው ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛው ይብስበታል፡፡ ማቴ12፡43-45፡፡
    • ኢየሱስ የማያምኑት እነማን እንደ ሆኑ አሳልፎ የሚሰጠውም ማን እንደ ሆነ ከመጀመሪያ ያውቅ ነበርና፡፡ ደግሞ ስለዚህ አልኋችሁ ከአብ የተሰጠው ካልሆነ ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም አለ፡፡ ከዚህ የተነሣ ከደቀ መዛሙርቱ ብዙዎች ወደ ኋላ ተመለሱ ወደ ፊትም ከእርሱ ጋር አልሄዱም፡፡ ዮሐ6፡64-66፡፡
    • በኋላም ደግሞ የቀሩቱ ቈነጃጅት መጡና ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ ክፈትልን አሉ እርሱ ግን መልሶ እውነት እላችኋለሁ አላውቃችሁም አለ፡፡ ማቴ25፡11፣12፡፡

    እንዲሁ እናንተ ደግሞ በውጪ ለሰው እንደ ጻድቃን ትታያላችሁ በውስጣችሁ ግን ግብዝነትና ዓመፀኝነት ሞልቶባችኋል፡፡... እናንተ እባቦች የእፉኝት ልጆች ከገሃነም ፍርድ እንዴት ታመልጣላችሁ? ማቴ23፡28፣33፡፡

    • ንጉሡም የተቀመጡትን ለማየት በገባ ጊዜ በዚያ የሰርግ ልብስ ያለበሰ አንድ ሰው አየና ወዳጄ ሆይ የሰርግ ልብስ ሳትለብስ እንዴት ወደዚህ ገባህ? አለው እርሱም ዝም አለ፡፡ በዚያን ጊዜ ንገሡ
    • ጌታ ለእርሱ የሆኑትን ያውቃል ደግሞም የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ከዓመፅ ይራቅ የሚለው ማኅተም ያለበት የተደላደለ የእግዚአብሔር መሠረት ቆሞአል፡፡ 2ጢሞ2፡19፡፡
    • እውነት እውነት እላችኋለሁ በእኔ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፡፡ ዮሐ6፡47፡፡
    • አባት ሆይ ዓለም ሳይፈጠር ስለ ወደድኸኝ የሰጠኸኝን ክብሬን እንዲያዩ እኔ ባለሁበት የሰጠኸኝ እነርሱ ደግሞ ከእኔ ጋር ይሆኑ ዘንድ እወዳለሁ፡፡ ዮሐ17፡24፡፡
    • በእናንተ መልካምን ሥራ የጀመረው እስከ ኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ድረስ እንዲፈጽመው ይህን ተረድቼአለሁና፡፡ ፊል1፡6፡፡ እኛ ግን ነፍሳቸውን ሊያድኑ ከሚያምኑቱ ነን እንጂ ወደ ጥፋት ከሚያፈገፈጉት አይደለንም፡፡ ዕብ1ዐ፡39፡፡

    አገልጋዮቹን እጅንና እግሩን አስራችሁ በውጪ ወዳለው ጨለማ አውጡት በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል አለ፡፡ የተጠሩ ብዙዎች የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና፡፡ ማቴ22፡11፣13፡፡

    • ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን በስምህስ ብዙ ተአምራት አላደረግንምን? ይሉኛል፡፡ የዚያን ጊዜም ከቶ አላወቅኋችሁም§ እናንተ ዓመፀኞች ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ፡፡ ማቴ7፡22፣23፡፡
    • ወንድሞች ሆይ እምነት አለኝ የሚል ሥራ ግን የሌለው ሰው ቢኖር ምን ይጠቅመዋል እምነቱስ ሊያድነው ይችላልን? ያዕ.2፡14፡፡
    • አንድ ጊዜ ብርሃን የበራላቸውን ሰማያዊውንም ስጦታ የቀመሱትን ከመንፈስ ቅዱስም ተካፋዮች ሆነው የነበሩት መልካሙንም የእግዚአብሔርን ቃልና ሊመጣ ያለውን የዓለም ኃይል የቀመሱትን በኋላም የካዱትን እንደገና ለንስሐ እነርሱን ማደስ የማይቻል ነው ለራሳቸው የእግዚአብሔርን ልጅ ይሰቅሉታልና ያወርዱትማልና፡፡ ዕብ6፡4-6፡፡
    • ጻድቅ ግን በእምነት ይኖራል ወደ ኋላም ቢያፈገፍግ ነፍሴ በእርሱ ደስ አይላትም፡፡ ዕብ1ዐ፡38፡፡
    2.አማኞች ይሸለማሉ፣ የአፍ-አማኞች ደግሞ ተፈርዶባቸዋል

    እነዚህን አነጻጽር፤
    ማቴ25፡19-23ን ከማቴ25፡24-3ዐ ጋር፤
    ሉቃ12፡42-44ን ከሉቃ12፡45-47 ጋር፤
    ቈላ3፡24ን ከማቴ7፡22፣23 ጋር፡፡

    አንዳንድ ምንባባት ለመረዳት ትንሽ የሚያስቸግሩ ሊሆኑ ይችላሉ፤ ነገር ግን በጸሎትና ጥንቃቄ በተሞላበት ጥናት እንዲሁም አሻሚ ወይም ግልጽ ያልሆኑ ምንባባትን ቀጥተኛና ግልጽ የሆኑትን ምንባባት ለመቃረን/ለመቃወም/ አለመጠቀም፣ የሚለውን ጠቃሚ የሆነ ሕግ በመከተል፣ የመረዳት ብርሃን በእርግጥ መምጣቱ አይቀርም፡፡ «እንዲህ ቢሆን» በሚል መንፈስ የተነገሩ ምንባባትን «እውነት እውነት እላችኋለሁ...» በሚል የተጻፉትን ለመቃረን አንጠቀምባቸው፤ /ለምሳሌ፣ ዕብ6፡6ን ዮሐ5፡24ን ለመቃወም ወይም ለመቃረን አትጠቀም/፡፡

    የአስቆሮቱ ይሁዳና የጴጥሮስ ጉዳይም ምንም ችግር ሊፈጥርብን አይገባም፡፡ ይሁዳ ፈጽሞ አማኝ አልነበረም፡፡ ዮሐ6፡68-71 ያለውን ተመልከት፡፡ ጴጥሮስ ግን ሁሌም አማኝ ነበር፡፡ ሉቃ22፡31፣32 ተመልከት፡፡

    በመጨረሻም፡ እነዚህ መርሆዎች የእውነትን ቃል /በአግባቡ/ በትክክል ለመለየት እንዲረዱን እንጂ በሕይወት ያለ ሰው ላይ ልንጠቀመባቸው ፈጽሞ የማይገባ መሆኑ ሁልጊዜ መታወስ አለበት፡፡ የአፍ-አማኞች ላይ መፍረድ ለእኛ አልተሰጠንም፤ ያ ለሰው ልጅ /ለኢየሱስ/ የተተወ ነው፡፡

    ማቴ13፡28፣29 እና 1ቆሮ4፡5 ን በጥንቃቄ አጥና፡፡

    ተፈጸመ