ትምህርት  

2. በኅብረት መትጋት (የሐ.ሥ.2፡42)

አማኞች በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በሚገኘውና አንድ ጊዜ ለቅዱሳን የተሰጠውን ሃይማኖት (እውነት) በሚናገረው በሐዋርያት ትምህርት የሚተጉ ከሆነ ይህ የሐዋርያት ትምህርት በታሪክ ውስጥ ከተፈጠሩ እና በዘመናችንም ካሉ የስህተት አስተምህሮዎች ተጠብቀው ከቀደሙት ሐዋርያት ጋር ኅብረት እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡ በመሆኑም አማኞች በሐዋርያት ትምህርት ሊተጉ እንደሚገባቸው ሁሉ በዚያ ትምህርት ላይ በተመሠረተው ኅብረትም ሊተጉ ይገባቸዋል፡፡

ኅብረት ማለት በሁለት ወገኖች መካከል ያለ ውስጣዊና ውጫዊ አንድነት ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል በሚናገራቸው እውነቶን በመቀበልም ሆነ እውነቶቹ የሚጠይቁትን ተግባራዊ ምልልስ በመፈጸም አንድ መሆንን ያካትታል፡፡ ኅብረቱም በቅድሚያ አማኞች የቃሉ እውነት መገኛ ከሆነው ከራሱ ከእግዚአብሔር ጋር ሊያደርጉት የሚገባ ኅብረት ሲሆን፣ በመቀጠል ደግሞ ያንን እውነት ከተቀበሉት ሁሉ ጋር የሚያደርጉት ኅብረት ነው፡፡

በእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ኅብረትን በተመለከተ ከሌላ ስፍራ ይልቅ በዝርዝር የምናገኘው በ1ዮሐ.1፡1-10 ባለው ክፍል ነው፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ ኅብረታችን ስለተመሠረተበት የሕይወት ቃል፣ ኅብረት የምናደርገው ከማን ጋር እንደሆነ እና የኅብረታችን መገለጫ ስለሆነው በብርሃን ስለመመላለስ እንዲሁም ኅብረታችን ሲበላሽ (ሲቋረጥ) እንዴት እንደሚታደስ የሚገልጽ መርህን እናገኛለን፡፡ ይህንንም ቀጥሎ እንመለከታለን፡፡

የሕይወት ቃል

“ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን፤ ሕይወትም ተገለጠ አይተንማል እንመሰክርማለን፥ ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን” (ዮሐ.1፡1-2)

“የሕይወት ቃል” ተብሎ በዚህ ስፍራ የተጠቀሰው “ከአብ ዘንድ የነበረውንና ለእኛ የተገለጠውን የዘላለም ሕይወት” በተመለከተ በሐዋርያት የተሰበከውን ቃል የሚያመለክት ነው፡፡ በዚህ ንባብ ውስጥ ሐዋርያው ዮሐንስ “እናወራለን”፣ “እንመሰክራለን” በማለት የሚናገረው ራሱን ከሌሎቹ ሐዋርያት ወንድሞቹ ጋር በማድረግ ነው፡፡ ስለሆነም የሕይወት ቃል ከሐዋርያት ትምህርት ሁሉ ዋነኛውና ቀዳሚው ትምህርት መሆኑን ልንገነዘብ ያስፈልጋል፡፡

ሕይወት ማለትም ራሱ ከሰጪው ማንነት ጋር በተጣጣመ ኅብረት መኖር ነው፡፡ ሆኖም ይህ ሕይወት “ከመጀመሪያው የነበረ” ስለተባለ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት የነበረ ነው፡፡ በመሆኑም ሕይወት በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ዘንድ ከዘላለም የነበረ ፍጹም የሆነ የእርስ በእርስ መለኮታዊ ግንኙነት ነው፡፡ እግዚአብሔር ሰውን በመልኩ እንደ ምሳሌው በፈጠረ ጊዜ የሕይወት እስትንፋስን እፍ እንዳለበት እናነባለን (ዘፍ.2፡7)፡፡ ኃጢአት ወደ ዓለም እስኪገባ ድረስ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ደስ የሚያሰኝ ኅብረት ነበረው፡፡ ኃጢአት ወደ ሰው ውስጥ ሲገባ ግን ሞት ወደ ዓለም ገባ፤ “ከእርስዋ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና” (ዘፍ.2፡17) ተብሎ የተነገረው ተፈጸመ፡፡ ሆኖም ሰው መልካምንና ክፉውን ከምታስታውቀው ዛፍ ከበላ በኋላ እስከ 930 ዓመቱ ድረስ አዳም በሥጋ ስለኖረ (ዘፍ.5፡5) የሞተው ሞት በሥጋ መሞቱን ሳይሆን ከእግዚአብሔር ጋር የነበረው ኅብረት መበላሸቱን የሚያሳይ ነበር፡፡ ይህ ለዘመናት ተበላሽቶ የነበረው ኅብረት እንደገና መልሶ የታደሰው ከመጀመሪያው በአብ ዘንድ የነበረው ሕይወት በክርስቶስ ከተገለጠ በኋላ ነበር፡፡ ሐዋርያው ይህን ሲያበስር “ስለ ሕይወት ቃል ከመጀመሪያው የነበረውንና የሰማነውን በዓይኖቻችንም ያየነውን የተመለከትነውንም እጆቻችንም የዳሰሱትን እናወራለን (1ዮሐ.1:1)” ብሏል፡፡ ይህ ሕይወት የተገለጠውም ለሰው ልጆች ሁሉ ሲሆን በክርስቶስ ኢየሱስ ያመኑ ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር እና እርስ በእርሳቸው ኅብረት የሚያደርጉበት ሕይወት ነው፡፡

ሐዋርያት ስለዚህ ሕይወት ለመመስከር የሚያበቃቸው የተሟላ ማስረጃዎች አሏቸው፡፡ ይህንን ሕይወት በክርስቶስ ኢየሱስ ማንነት በጆሮአቸው ሰምተውታል፣ በዓይኖቻቸው አይተውታል፣ በእጆቻቸውም ዳስሰውታል፡፡ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ “እኔ ትንሣኤና ሕይወት ነኝ” (ዮሐ.11፡25)፣ እንዲሁም “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ” (ዮሐ.14፡6) ብሏል፡፡ ታዲያ ከእርሱ መስማት፣ እርሱን ማየትና እርሱን መዳሰስ ሕይወትን እንደ መስማትና ማየት፣ እንደ መዳሰስም ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡ ሐዋርያትን የእርሱ ምስክር ለመሆን ያበቋቸውም እነዚህ ማስረጃዎች ናቸው፡፡

ጌታ ኢየሱስ ወደዚህ ዓለም የመጣው በበደላቸውና በኃጢታቸው ሙታን ለሆኑ ሰዎች ሕይወትን ለመስጠት ነው፡፡ “እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ” (ዮሐ.10፡) ብሎ የተናገረው ቃል ይህንኑ ያስረዳል፡፡ ሆኖም ጌታ ኢየሱስ በሥጋ ከተገለጠ በኋላ ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት ማድረግ የሚያስችል ይህን ሕይወት እየሰጠ ያለው ከሙታን ተነሥቶ በእግዚአብሔር ቀኝ ከሚገኝበት ከዚያ ከክብር ስፍራው ሆኖ ነው፡፡ “ለሰጠኸው ሁሉ የዘላለምን ሕይወት ይሰጣቸው ዘንድ ልጅህን አክብረው” በማለት ወደ አባቱ ያቀረበው ጸሎትም ይህን የሚያረጋግጥ ነው (ዮሐ.17፡1-2) በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዳለው ሐዋርያት የመሰከሩት ይህ ቃልም የሕይወት ቃል ተብሏል፡፡

ኅብረት የምናደርገው ከማን ጋር ነው?

“እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንደኖራችሁ ያየነውንና የሰማነውን ለእናንተ ደግሞ እናወራላችኋለን። ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው፤ ደስታችሁም እንዲፈጸም ይህን እንጽፍላችኋለን” (1ዮሐ.1፡2)፡፡

ሐዋርያት ክርስቶስ በምድር ሳለ ያደረገውን አይተዋል፤ ያስተማረውን ሰምተዋል፡፡ እንዲሁም ከሙታን ከተነሣ በኋላ እርሱን አይተውታል፤ ሰምተውታልም፣ ከመካከከላቸውም ተለይቶ ወደ ሰማይ በክብር ሲያርግ አይተውታል፡፡ ይህን ያዩትንና የሰሙትን ሁሉ በቃልም ሆነ በጽሑፍ የመሰከሩበት ዋነኛ ዓላማም ምስክርነቱን የተቀበሉት ሁሉ ከእነርሱ ጋር ኅብረት እንዲያደርጉ ለማስቻል መሆኑን ዮሐንስ ሲገልጽ “እናንተ ደግሞ ከእኛ ጋር ኅብረት እንዲኖራችሁ” በማለት ይጽፋል፡፡ በመሆኑም በመጀመሪያ ኅብረት የምናደርገው ከሐዋርያት ጋር ነው ማለት ነው፡፡ በእርግጥም ሐዋርያት ያስተማሩትን ትምህርት ስንቀበል ሐዋርያት ያመኑትና እኛ ያመንነው አንድ ስለሚሆን ልባችንም ከሐዋርያ ልብ ጋር አንድ ይሆናል፤ በዚህም ከሐዋርያት ጋር በሕይወት ቃል ላይ የተመሠረተ ኅብረት ይኖረናል፡፡ “በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል” ተብሎ በተጻፈው መሠረት (1ቆሮ.3፡11) እኛ በዚህ ዘመን መጨረሻ ያለነውን ጨምሮ ከዘመነ ሐዋርያት እስከ ጌታ መምጣት ድረስ የሚገኙ አማኞች በሙሉ ሐዋርያት በጣሉት መሠረት ላይ የተመሠረቱና የታነጹ ናቸው፡፡ ይህም መሠረት ሐዋርያት ባስተማሩት ትምህርት የተገለጸ ስለሆነ በአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ተጽፎ ለእኛ የደረሰንን ትምህርታቸውን ስንቀበል እነሱ በጣሉት መሠረት ላይ እንታነጻለን፡፡ ከእነርሱ ጋር ኅብረት የምናደርገውም ያን ጊዜ ነው፡፡ ይህም በየትኛውም ዘመን ያሉ አማኞች በዙሪያቸው ልዩ ልዩ አስተምህሮዎችና ሥርዓቶች ቢኖሩም እነርሱ ግን በአዲስ ኪዳን መጻሕፍት የተጻፉትን የሐዋርያትን ትምህርት በትክክል በመረዳት መሠረቱን ከጣሉት ከመጀመሪያዎቹ የቃሉ አገልጋዮች ከሐዋርያት ጋር ኅብረት ሊያደርጉና በዚህ ኅብረትም ሊተጉ እንደሚገባ ያስገነዝበናል፡፡

የሐዋርያትን ትመህርት ስንቀበል በቅድሚያ ከሐዋርያት ጋር ኅብረት እናደርጋለን ሲባል ግን እነርሱስ ቢሆኑ እንደ እኛው ሰው አይደሉም እንዴ? ከእነርሱ ጋር የሚደረግ ይህ ኅብረት ምን ያህል ደስታን ይሰጣል? ተብሎ ሊጠየቅ ይችላል፡፡ እነርሱ እንደ እኛው ሰው መሆናቸው እርግጥ ቢሆንም የተገለጠውን የሕይወት ቃል በቀጥታ እንዲቀበሉ በራሱ በጌታ የተመረጡ ሰዎች መሆናቸውን ግን መዘንጋት የለብንም፡፡ ከእነርሱ ጋር ኅብረት እንድናደርግ ያደረገን ማንነታቸው ሳይሆን ያስተማሩት የሕይወት ቃል መሆኑን ልብ እንበል፡፡ በዚያ ቃል የሰበኩት “የዘላለም ሕይወት” ደግሞ ከእነርሱ አእምሮ የፈለቀ በሥጋና በደም ውስጥ የነበረ ሳይሆን “ከአብ ዘንድ የነበረ ለእኛም የተገለጠ” ብለው የገለጹት ሕይወት ነው፡፡ እንዲሁም ወልድ በሥጋ ተገልጦ ያስተማረውን “የዘላለም ሕይወት ቃል” በቀጥታ ከእርሱ ተቀብለዋል (ዮሐ.6፡68)፤ ያን ጊዜ ሊሸከሙት ያልቻሉትን እውነት ደግሞ መንፈስ ቅዱስ ወደ እውነት ሁሉ እንደሚመራቸው በተነገራቸው መሠረት በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ተገልጦላቸዋል (ዮሐ.16፡12-13፤ 1ቆሮ.2፡10)፡፡ በመሆኑም የሐዋርያትን ትምህርት ተቀበልን ማለት ሐዋርያት ከአብ ከወልድና ከመንፈስ ቅዱስ የተቀበሉትን እውነት ተቀበልን ማለት ነው፡፡

የሐዋርያትን ትምህርት ተቀብለን ከአብ ዘንድ የነበረውን የዘላለም ሕይወት ስናገኝ ኅብረታችን ከሐዋርያት ጋር ብቻ ሳይሆን ይህ የዘላለም ሕይወት ከተገኘበት ከአብና ከወልድ ጋርም ይሆናል፤ ይህንን ማወቅም ደስታችንን ፍጹም ያደርገዋል፡፡ ሐዋርያው ዮሐንስ “ኅብረታችንም ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ነው፤ ደስታችሁም እንዲፈጸም ይህን እንጽፍላችኋለን” ብሎ የተናገረውም ለዚህ ነው (1ዮሐ.1፡3)፡፡ ስለዚህ ትምህርቱን ከሐዋርያት ስለተቀበልን በመጀመሪያ ከእነርሱ ጋር ኅብረት ብናደርግም በዋናነት ኅብረት የምናደርገው ግን እነርሱ ራሳቸው ኅብረት ካደረጉበት ከአብና ከወልድ ጋር ነው፡፡ ዮሐንስ “ኅብረታችንም” ሲል እኛን ከእነርሱ ጋር በአንድ ላይ አድርጎ እየተናገረ መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ በዚህ ስፍራ ኅብረቱን የምናደርገው “ከአባት ጋር ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር” እንደሆነ ሲገለጽ መንፈስ ቅዱስ ያልተጠቀሰው በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ንባቦች እንደምናየው ሁሉ መንፈስ ቅዱስ ምንም እንኳ በባሕርዩ ከአብና ከወልድ ጋር ያለ ቢሆንም እርሱ በዚህ በጸጋው ዘመን በምድር ካሉ አማኞች ጋር የሚኖር በመሆኑና ራሱንም የሚቆጥረው ከእነርሱ ጋር እንዳለ አድርጎ ስለሆነ ነው፡፡ እርሱ ከእኛ ጋር ሆኖ ከአባት ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ኅብረት እንድናደርግ መሥራቱ ደግሞ ኅብረታችንን ፍጹም ያደርገዋል፤ በዚህ የሚገኘውን ደስታችንንም ፍጹም ያደርገዋል፡፡

በኅብረት የምንተጋው እንዴት ነው?

ከአብ ዘንድ የነበረውን የዘላለም ሕይወት ተቀብለን በየግላችን ከአብና ከወልድ ጋር ኅብረት ያደረግን ሁላችን በአንዲት ቤተክርስቲያን ውስጥ ካሉ ከሐዋርያትና ከነቢያት ብሎም ከቀደሙ ቅዱሳን ጋር ብቻ ሳይሆን በዘመናችን ካሉ እውነተኛ አማኞች ሁሉ ጋር ኅብረት እናደርጋለን፤ ወደ ላይ ከእግዚአብሔር ጋር ወደ ጎን ደግሞ እርስ በእርሳችን ያለንን ይህን ኅብረት በጌታ በኢየሱስ ስም በየስፍራው በመሰብሰብ እንገልጠዋለን፡፡ ይህ በየስፍራው የሚሰበሰብ ኅብረት የማንም ሳይሆን የራሱ የኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት ሲሆን እርሱ ተመልሶ እስኪመጣ ድረስ ያለነቀፋ በመኖር የምንተጋበት ኅብረት ነው፤ “እርሱም ደግሞ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ያለ ነቀፋ እንድትሆኑ እስከ ፍጻሜ ድረስ ያጸናችኋል። ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው” (1ቆሮ.1:8-9) የሚለው ቃልም ይህንኑ ያስረዳል፡፡ እንዲሁም ኅብረቱ ያለነቀፋ በመኖር በተግባር መገለጥ ያለበት ኅብረት መሆኑንም ከዚህ ቃል እናስተውላለን፡፡

በኅብረት የምንተጋው ከሐዋርያት የተቀበልነውን መለኮታዊ ትምህርት በአንድ ልብ ይዞ በመገኘት ብቻ ሳይሆን በተግባርም በብርሃን በመመላለስ እና በኃጢአት ምክንያት የሚበላሸውን ኅብረት ለማደስ ኃጢአትን በመናዘዝ መሆኑን በ1ዮሐ.1፡5-10 ባለው ንባብ እንማራለን፡፡ እነዚህን ሁለት በኅብረት የመትጊያ መንገዶች እንደሚከተለው እናቀርባለን፡፡

1. በብርሃን በመመላለስ

“በብርሃን መመላለስ” አማኞች ሁል ጊዜም በእግዚአብሔር ሐሳብና ፈቃድ መሠረት ሊኖራቸው የሚገባውን ተግባራዊ ምልልስ የሚያመለክት ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት አደርጋለሁ የሚል አማኝ እግዚአብሔር የገለጠውን እውነት የሚያምን ብቻ ሳይሆን በእርሱ ሐሳብና ፈቃድ መሠረት የሚመላለስም ሊሆን ይገባል፡፡ ኅብረቱ እውነተኛ የሚሆነው በተግባር ሲገለጥ ብቻ ነው፡፡

አንዳንድ ሰዎች የጨለማ ሥራዎችን ለመሥራት እግዚአብሔር ለሰው ያለውን ፍቅር ሽፋን ለማድረግ ሲሞክሩ ይታያል፤ “እግዚአብሔር ፍቅር ስለሆነ እንደሰው አይፈርድብንም” የሚል መንፈሳዊ የሚመስል ሐሳብን በመያዝ በዓመፃ ተግባር ይቀጥላሉ፤ ሆኖም እግዚአብሔር “ፍቅር” የሆነውን ያህል (1ዮሐ.4፡8፣16)፣ እግዚአብሔር “ብርሃን” መሆኑም ተነግሮናል፡፡ “ከእርሱም የሰማናት ለእናንተም የምናወራላችሁ መልእክት እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም የምትል ይህች ናት” ይላል (1ዮሐ.1:5)፡፡ ይህም እግዚአብሔር ብርሃን መሆኑ ከእርሱ ጋር ላለን ኅብረት መገለጫ ሆኖ ቀርቦልናል፡፡ እግዚአብሔር በባሕርዩ ብርሃን ከሆነ ኅብረት ሊኖረው የሚችለው በእርሱ ብርሃን ከሚመላለሱ ጋር ነው፡፡ በዚያው ልክ ደግሞ ጨለማ በእርሱ ዘንድ ከቶ ስለሌለ በጨለማ ከሚመላለሱ ጋር ምንም ኅብረት ሊኖረው አይችልም፡፡

አማኞች የእግዚአብሔር ብርሃን የበራላቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ይህም ብርሃን ሌላ ምንም ሳይሆን ገና በጌታ በኢየሱስ ባመኑ ጊዜ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተቀበሉት የሕይወት ብርሃን ነው፡፡ ጌታ ኢየሱስ ራሱ ሲናገር “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም” ብሏል (ዮሐ.8፡12)፡፡ ይህም ሕይወት አብንና ወልድን ማወቅ ነው (ዮሐ.17፡3)፡፡

ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ዘንድ ብቻ የነበረው ይህ ሕይወት ወልድ በሥጋ ወደዚህ ዓለም በመምጣቱ በሞት ጨለማ ውስጥ ለነበረው ለሰው የበራ ብርሃን ሆኖ ተገለጠ፡፡ ብርሃኑ “የሕይወት ብርሃን” ተብሎ መጠራቱም ለዚህ ነው፡፡ ይህ የሕይወት ብርሃን ለሰው ሲያበራም በሰው ዘንድ የነበረውን የሞት ጨለማ አሸንፎ የተገለጠ ነው፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ይህን ሲገልጥ “በእርሱ ሕይወት ነበረች፤ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች ብርሃንም በጨለማ ይበራል ጨለማም አላሸነፈውም” (ዮሐ.1፡4-5) ይላል፡፡ በፍጥረት መጀመሪያ ላይ ጨለማ በጥልቁ ላይ ሰፍፎ በነበረ ጊዜ እግዚአብሔር “ብርሃን ይሁን” ብሎ ሲናገር ብርሃኑ ጨለማውን እንዳሸነፈው እንጂ ጨለማው ብርሃኑን እንዳላሸነፈው ሁሉ ለእኛም “የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን” በበራልን ጊዜ እኛ የነበርንበት ተግባራዊ ጨለማ ብርሃኑን ሊያሸንፈው አልቻለም፡፡ ይህ ብርሃን ሌላ ማንም ሳይሆን ራሱ እግዚአብሔር እንደሆነ ሐዋርያው ጳውሎስ ሲገልጥ “በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት ብርሃን እንዲሰጥ በልባችን ውስጥ የበራ፦ በጨለማ ብርሃን ይብራ ያለ እግዚአብሔር ነውና” ብሏል (2ቆሮ.4:6)፡፡

ስለሆነም ብርሃን የሆነው እግዚአብሔር በልባችን ካለ የምንመላለሰውም በእግዚአብሔር ብርሃን መሠረት ይሆናል፡፡ እርሱ የሚወደውን እናደርጋለን፤ እርሱ የሚጠላውን ደግሞ አናደርግም፡፡ ነገሮችን ሁሉ እግዚአብሔር እንደሚያያቸው እንደዚያው በማየት እንመላለሳለን፡፡ በየትኛውም ቦታና በየትኛውም ጊዜ እንደ እግዚአብሔር ሐሳብና ፈቃድ እንመላለሳለን፤ እንዲህ ስናደርግም ከእርሱ ጋር ኅብረት ይኖረናል፡፡ በተቃራኒው ግን በብርሃን አለሁ እያልን በጨለማ ብንመላለስ ከእርሱ ጋር ኅብረት አይኖረንም፡፡

“በጨለማ መመላለስ” እንደ እግዚአብሔር ቃል ያልሆነ ነገርን ከሰው ተሰውሮ መሥራትን የሚገልጽ እንጂ ከእግዚአብሔር ተሰውሮ መሥራት የሚቻል ነገር እንዳለ የሚገልጽ አይደለም፤ ምክንያቱም በ1ዮሐ.1፡5 እንደተገለጸው ጨለማ በእግዚአብሔር ዘንድ ከቶ የለምና፡፡ በሌላ ንባብም “በውኑ ጨለማ ትሸፍነኛለች ብል፥ ሌሊት በዙሪያዬ ብርሃን ትሆናለች፤ ጨለማ በአንተ ዘንድ አይጨልምምና ሌሊትም እንደ ቀን ታበራለችና” ተብሎ ተጽፏል፡፡ (መዝ.138(139)፡11-12)፡፡ በመሆኑም በጨለማ መሰወር የሚቻለው ከሰው እንጂ ከእግዚአብሔር አይደለም፡፡

ሐዋርያው የጨለማ ሥራዎችን በመዘርዘር ከእኛ እንድናርቃቸው ሲመክር እንዲህ ይላል፤ “ሌሊቱ አልፎአል፥ ቀኑም ቀርቦአል። እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን ጋሻ ጦር እንልበስ። በቀን እንደምንሆን በአገባብ እንመላለስ፤ በዘፈንና በስካር አይሁን፥ በዝሙትና በመዳራት አይሁን፥ በክርክርና በቅናት አይሁን” ይላል (ሮሜ.13:12-13)፡፡ ስለሆነም ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት አለን እያልን እነዚህን የጨለማ ሥራዎች የምንሠራ ከሆነ በተግባር እየዋሸን ነው ማለት ነው፡፡ ሐዋርያው ዮሐንስ ይህን በተመለከተ ሲናገር “ከእርሱ ጋር ኅብረት አለን ብንል በጨለማም ብንመላለስ እንዋሻለን እውነትንም አናደርግም” ብሏል (1ዮሐ.1:6)፡፡ ይህም አፍኣዊነትን የሚያመለክት ነው፡፡ እንዲህ ሲሆን ኅብረት አለን የምንለው በአፍ ብቻ እንጂ በተግባር አይደለምና፡፡ እውነተኛ አማኝ ግን ከእግዚአብሔር ጋር ባለ ኅብረት የሚተጋው በአፍ ብቻ ሳይሆን በተግባርም በብርሃን በመመላለስ ነው፡፡ “እንግዲህ ከእነርሱ ጋር ተካፋዮች አትሁኑ፤ ቀድሞ ጨለማ ነበራችሁና፥ አሁን ግን በጌታ ብርሃን ናችሁ፤ የብርሃኑ ፍሬ በበጎነትና በጽድቅ በእውነትም ሁሉ ነውና ለጌታ ደስ የሚያሰኘውን እየመረመራችሁ፥ እንደ ብርሃን ልጆች ተመላለሱ፤ ፍሬም ከሌለው ከጨለማ ሥራ ጋር አትተባበሩ፥ ይልቁን ግለጡት እንጂ፥ እነርሱ በስውር ስለሚያደርጉት መናገር እንኳ ነውር ነውና፤ ሁሉ ግን በብርሃን ሲገለጥ ይታያል፤ የሚታየው ሁሉ ብርሃን ነውና” እንዳለ (ኤፌ.5፡7-13)።

2. ኃጢአትን በመናዘዝ

ከእግዚአብሔርም ሆነ ከቅዱሳን ጋር ባለን ኅብረት የምንተጋበት ቀጣዩ መንገድ ደግሞ ኃጢአትን መናዘዝ ነው፡፡ እውነተኛ አማኝ በተግባር ከጨለማ ሥራዎች ተለይቶ በብርሃን የሚመላለስ ነው ሲባል በምንም ዓይነት ኃጢአት ሊሰናከል አይችልም ማለት አይደለም፡፡ አማኝ ወዶና ፈቅዶ ኃጢአት ባያደርግም ከለበሰው ሥጋ ድካም የተነሳ ተሰናክሎ ኃጢአትን ሊያደርግ ይችላል፡፡ ነገር ግን ኃጢአቱን በእግዚአብሔር ብርሃን በግልጥ ስለሚያይ ምንም ሳይሸፋፍን ይናዘዘዋል፤ ይፈርድበታል፡፡ ይህም በብርሃን የመመላለሱ ዋነኛ መገለጫ ነው፡፡ ይህንንም የምንማረው በሚከተለው ቃል ነው፡፡ “ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል። ኃጢአት የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም። በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው” ይላል (1ዮሐ.1:7-9)፡፡

በዚህ ክፍል “በብርሃን መመላለስ” ተብሎ የተጠቀሰው የራስን ማንነት በእግዚአብሔር ብርሃን ማየት ነው፡፡ ይህም በእግዚአብሔር ቃልና በእግዚአብሔር መንፈስ ራስን በመመርመር ያለንበትን ሁኔታ ማወቅ ነው፡፡ እንዲህ ስናደርግ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የሠራናቸውን ኃጢአቶች በግልጽ እናያቸዋለን፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ኅብረትም በእነዚህ ኃጢአቶች ምክንያት እንደተቋረጠ እናስተውላለን፡፡ ነገር ግን በዚህ ምክንያት ለደነገጠውና ላዘነው ልባችን ቃሉ “የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል” በማለት የሚያጽናና ተስፋን ይሰጠዋል፡፡ ይህም ማለት ኃጢአታችን በክርስቶስ ደም ነጽቶ ከእግዚአብሔር ጋር የነበረው ኅብረታችን የሚታደስበት ዕድል አለ ማለት ነው፡፡ ከእኛ የሚጠበቀው በእግዚአብሔር ብርሃን ያየንውን ኃጢአታችንን በግልጽ መናዘዝ ነው፤ ምንም እንዳላደረገ ሰው ለመሰወር ብንሞክር ግን እንዋሻለን፤ “ኃጢአትን አላደረግንም ብንል ሐሰተኛ እናደርገዋለን፤ ቃሉም በእኛ ውስጥ የለም። ይላል (1ዮሐ.1:10)፡፡

የእግዚአብሔር ቃል በእኛ ውስጥ ሲኖር ኃጢአታችንን ያሳየናል፤ ይህንንም የሚያደርገው እንድናነዘዘው ነው እንጂ እንድንሰውረው አይደለም፡፡ መናዘዝም በቀጥታ ወደ እግዚአብሔር በጸሎት ቀርቦ የሠሩትን ኃጢአት ምንም ሳይሸፋፍኑ በግልጽ መናገር ነው፡፡ በመዝሙር መጽሐፍ ውስጥ “ኃጢአቴን ለአንተ አስታወቅሁ በደሌንም አልሸፈንሁም፤ ለእግዚአብሔር መተላለፌን እነግራለሁ አልሁ፤ አንተም የልቤን ኃጢአት ተውህልኝ።” የሚል ቃል እናነባለን (መዝ.32:5)፡፡ በመሆኑም “በእግዚአብሔር ዓይኖች ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ እንደሆነ እንጂ የተሰወረ ፍጥረት” እንደሌለ (ዕብ.4፡13) በማወቅ በታላቅ ጸጸት ሆነን በራሳችን እየፈረድን ኃጢአታችንን በግልጽ መናዘዝ ይገባናል፡፡ “ኃጢአቱን የሚሰውር አይለማም፤ የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል” ይላል (ምሳ.28:13)፡፡

ኃጢአታችንን ከተናዘዝን በኋላ እግዚአብሔር ይቅር እንደሚለን ልናምን ወይም እርግጠኞች ልንሆን ይገባናል፡፡ “በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው” በማለት ቃሉ አረጋጦልናልና (1ዮሐ.1:9)፡፡ እግዚአብሔር ይቅር ሊለንና ሊያነጻን የታመነ ከሆነ እኛም ይቅር እንዳለንና እንዳነጻን ልናምነው ይገባናል፡፡ ይህ ይቅርታና መንጻት ግን ከዘላለም ፍርድ ለማዳን የተደረገልን አይደለም፡፡ ያንንማ ገና በጌታ ያመንን ጊዜ አግኝተን ለዘላለም ድነናል፡፡ አሁን ግን ካመንን በኋላ በሥጋ ድካም የተነሣ በሠራንው ኃጢአት፣ ልጅ አባቱን እንደሚበድል በመበደላችን የተነሣ ከእርሱ ጋር ተቋርጦ የነበረው ኅብረት ይታደስልናል፡፡ ይቅር የሚለን ለዚህ የኅብረት መታደስ መሆኑን እንጂ ለመዳን እንዳልሆነ ልብ ልንል ይገባናል፡፡ ከእርሱ ጋር ያለን ኅብረት ሲታደስ በኃጢአት የተነሣ ከቅዱሳንም ጋር ተበላሽቶ፣ ብሎም ተቋርጦ የቆየው ኅብረትም እንደገና ይመለሳል፡፡ ይህ ሁሉ የሚሆነው በእግዚአብሔር ብርሃን ራሳችንን አይተን ኃጢአታችንን ስንናዘዝ ነው፡፡ በዚህ መልኩ ኃጢአትን በመናዘዝ ይቅርታን ተቀብለን በኢየሱስ ደምም ከዓመጻ ሁሉ ነጽተን ኅብረትን በማደስ አሁን እግዚአብሔር እኛን ባስቀመጠበት ኅብረት ልንተጋ ይገባናል፡፡

  • እንጀራውን በመቁረስ መትጋትና
  • 
    Amharic Bible-|- The Holy Bible [King James Version]