ግጥም    

እውነት - ሕይወት



መራራ ነው እንጉርጉሮ
የሲኦል ጣር የእንባ ኑሮ
ሁሌ ምሬት ሁሌ ሮሮ
መንፈስ ገድሎ ልብን ቀብሮ
ጽድቅ ጠፍቶ ኃጢአት ከብሮ
የዓለም ሕይወት የዓለም ኑሮ
ያለ የሱስ ሁሌ ሮሮ፤

የህልም ዓለም የምኞት ዳር
የሞት መቅሠፍት የጭንቅ ጣር
የእምነት ውድቀት የቃል ስካር
ከዚህኸ እዚያ ከዳር እዳር
ሀ ሁ .... ቆጥሮ ሀቅ ሲሻር፡፡
አዬ - ዓለም
አዬ - ሕይወት

ያለ ኢየሱስ ምን ትርፍ አለሽ
ምን አገኘሽ ምን አስቀመጥሽ
ታሪክሽን እንዴት አሰብሽ
እንዴት አቀድሽ እንዴት አለምሽ
ባዶ አይደለሽ ! ህልም የሌለሽ ! ተስፋ ቆርጠሽ ሞት የናፈቅሽ !
እረፍት አጥተሽ የተሸነፍሽ !
ያለ የሱስ ምን ክብር አለሽ?
ምንስ ውበት ምን ወዝ አለሽ?
የአፈር ፅንስ ሙት ልጅ አለሽ
ከዚህ ውጪ ሕይወት የለሽ ሰላም የለሽ
ተስፋ የለሽ እረፍት የለሽ

ኢየሱስን ገለል አርገሽ
ለምውታን ስፍራ ሰጥተሽ
ክብር ሰጥተሽ
ይኸው እንዲህ ሆነሽ ቀረሽ
የሰቆቃ የጣር ጩኸት ታሰሚያለሽ፡፡

መስሎሽ እንጂ
ብትረጂ
ባልለወጥሽው
ባልለቀቅሽው
ባልቀየርሽው

ኢየሱስን
«ሕይወት ክብሬ» ብለሽ ባልሽው
ይሄን ታሪክ አበላሽተሽ ባልመረዝሽው

አይሞኝነት
ተረት ተረት
የመሠረት
ዱቄት በአመድ የመለወጥ
የመበለጥ
መቀላወጥ
መለማመጥ
ሕይወት ጥሎ ሞትን መምረጥ
አይ መብለጥለጥ
ግን መበለጥ
ሞትን መምረጥ፤

የኛስ ምክር የምንለው
ለዓለም ሁሉ የምንነግረው
ሰሚ ይስማ ጆሮ ያለው
የሚያድነው ኢየሱስ ነው
እረፍት ያለው ኢየሱስ ነው
መንገድ እውነት ኢየሱስ ነው
ሕይወት ያለው ኢየሱስ ነው
እኛ ያለን የምንሰጠው
የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ነው


Amharic Bible-|- The Holy Bible [King James Version]